በኢፌድሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሳምንታዊ አቋም መግለጫ

Wednesday, 13 January 2016 14:43

 

 

 

                    ታህሳስ 29/2008

ለልማትና ለመልካም አስተዳደርዕቅድ ስኬት የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያዎች ድርሻ ወሳኝ ነው!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ ህዝብና መንግስት በመታገል ላይ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ ያስመዘገቡት ውጤት አበረታች ነው። አሁንም ሁለተኛ ዙር የአምስት ዓመት ዕቅድ አዘጋጅተው መረባረብ ጀምረዋል።

ይህ ትግላቸው ለልማት ባላቸው አቅም በመትጋት ብቻ የተወሰነ አይደለም። የልማት ግስጋሴያቸውን የሚጎዱ የመልካም አስተዳደር አሰጣጥ ችግሮችን መታገልንም ይጨምራል። በያዝነው በጀት ዓመት ህዝብና መንግስት በገቡት ቃል መሠረት ይህንኑ ትግል በመጀመር ላይ ይገኛሉ።

ይህ ትግል ከውስብስብ የግል ተጠቃሚነት ተንኮል ጋር የሚደረግ ፍልሚያ በመሆኑ ቀላል አይሆንም። ግን ደግሞ አጥፊዎች በህዝብና በመንግስት ውስጥ የተደበቁ በመሆናቸው ህዝብና መንግስት ቆርጠው በጋራ ከተነሱ መሸሸጊያ አይኖራቸውም። በእንደዚህ ዓይነት ወቅት የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያዎች ሚና ደግሞ ከፍተኛ ነው። ምክንያቱም  የህዝብና የመንግስት የመልማት ፍላጎትን በመደገፍ የሚቆሙ ናቸው።

የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያዎች የተዛቡ አሠራሮችን ፈልፍለው በማውጣት መወያያ ለማድረግ የሚያስችል አቅም አላቸው፡፡ ዋና ድርሻቸውም መሬት ላይ ያለውን ዕውነት ለህዝብ በማድረሰ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር፣ ቅሬታዎች እንዲፈቱ የህዝብ አንደበት ሆነው ማገልገል ነው። ይህ ደግሞ አየተለወጠች ባለች ሀገር ውስጥ በሚሰሩት ይህን መሰል ስራ ሙያቸው የማይተካ የህዝብ ጉልበት ሆኖ እንዲያገለግል ያግዛል። ምክንያቱም ሚዲያውና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው እየተመጋገቡ ከህዝብና ከመንግስት ጎን መቆም ሁሉ ጊዜ ዋና ስራቸው ነው፡፡ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ በሚመራው ተቋም ውስጥ ለህዝብ ጥቅም የሚሠራ መሆን አለበት፡፡ በተቋሙ ውስጥ ያሉ አካላት የሚሰሯቸውን ጥፋቶች የሚደብቅ ሳይሆን ከተገልጋዮች ጎን ቆሞ የሚያርም ሊሆን ይገባል። የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያ ለህሊናው የሚቆም፣ ለህዝብና ለተቋሙ ጥቅም የሚታገል የልማት አርበኛ ነው።

ስለሆነም የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያ ከድህነት ለመውጣት ህዝብና መንግስት በጀመሩት ጉዞ ላይ ወገንተኝነቱን ማሳየት፣  በተለይም ብልሹ አሠራሮችን ለመታገል የተጀመረውን ዘመቻ በሙያው ማገዝ ይጠበቅበታል።

መልካም አስተዳደርን የማስፈንና ልማት የማረጋገጥ ትግል የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያውን የነቃ ተሳትፎ የሚፈለግበት ወሳኝ ወቅትም አሁን ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
628 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 923 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us