የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል

Wednesday, 13 January 2016 14:51

 

የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የባህል እሴቶችና መገለጫዎች በማበልጸግ አንድነትና ትስስር ይበልጥ እንዲጠናከር እየሰራ በለውጥ ጎዳና ላይ ያለ ተቋም!

ከማዕከሉ

ባለፉት ሁለት ተከታታይ ህትመቶች በዚሁ አምድ ስር ማዕከላችንን የተመለከቱ ሀሳቦች መነሳታቸውን ተመልክተናል። በመሆኑም ዝም ከማለት እውነቱን ማሳየት ፈለግን።

በ2000 ዓ.ም አዲስ አመራር ሲመደብ ሁለት አማራጮች ነበሩት። አንደኛው በማዕከሉ ተንሰራፍቶ የነበረውን የኪራይ ሰብሳቢነት መረብን በመበጣጠስ ብልሹ አሰራርን መታገል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ አዳራሽ ብቻ በማከራየት ካለ ሥራ ተቀምጠው በኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር ተዘፍቀው የብልሹ አሰራር ምንጭ ከሆኑ አካላት ጋር ተቀላቅሎና ተመሳስሎ በአድርባይነት መቀመጥ። እናም መንግሥት የሚሾመውን ስለሚያውቅ እና ኃላፊም በዋነኝነት ኪራይ ሰብሳቢነትን ታግሎ ብልሹ አሰራርን ማስወገድ ቁልፍ ተግባሩ በመሆኑ የመጀመሪያው አማራጭ ተወስዶ በቁርጠኝነት ወደ ተግባር ተገብቷል። በዚህም በተወሰደው እርምጃ ከፍተኛ እመርታ ተመዝግቧል። ዝርዝሩን ወደ ኋላ አነሳዋለሁ።

በዚህ ወቅት የማዕከሉን እና የኃላፊውን ስም ጥላሸት መቀባት የተፈለገው በማዕከሉ የተጀመረውን የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል እና አሰራርን ለማዳከም የታሰበ እንጂ ሀቅን መሰረት ያደረገ አይደለም። በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህል ላይ መስራት ሲገባው አልሰራም ሲል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የዳውሮ፣ የቤንችማጂና የሸካ ዞን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የባሕል እሴቶችን ለማበልፀግ የሰራነውን ይኮንናል። ከእነዚህ ብሔረሰቦች ጋር መስራት ያስገኘውን ጥቅም ብሔረሰቦቹ ቢናገሩ ስለሚሻል እኛ ግን ተልዕኮአችንን ያሳካንበት የማዕከላችን ተግባር በመሆኑ ደስተኞች ነን። ወደፊትም እስከ ታች ወርደን ከክልሎች ከዞኖች ከወረዳዎች ጋር በመሆን መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

§  በእርግጥ ፀሐፊው ወደ ማዕከሉ ሲመጡ የብሔረሰቦችን ሉዓላዊነት አምኖና አክብሮ በዚሁ ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባሮችን ከመፈፀም ይልቅ በጥናት ስም የመንግሥት እና የህዝብን ገንዘብ ያለአግባብ ለመጠቀም አስበው ከሆነ የተሳሳቱ ስለሆነ ሲቀጠሩ የተሰጣቸውን የስራ ዝርዝር በአግባቡ ተረድተው ወደ ሥራ ቢገቡ የተሻለ ሲሆን በሂደትም የዚህን ዓይነት አመል ያለባቸውን በትግል የማስተካከል ሥራ የሚሰራ ይሆናል።

§  የማዕከሉን የሰራተኞች ክበብ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ እንዲዘጋ የተደረገው ምክንያት እየተፈለገ መንግሥት በማያውቀው ሁኔታ በእያንዳንዱ ኪስ ገንዘብ ሲያስገባ የነበረ ሲሆን አዳራሽ በነፃ ሲሰጥ እንኳን ደንበኞቻችንን የኮርኬጅ እና ቲፕ ካልከፈላችሁ አዳራሹን አትጠቀሙም የሚል ጽንፍ ሲራመድበት የቆየ ነበር። ይህንኑ ለማስቀረት የመንግስትን ህግና ደንብ በመከተል እንዲሰራ በተወሰደው እልህ አስጨራሽ የማስተካከያ እርምጃ ብዙዎች ተከፍተዋል። እነዚህን አካላት ለማስደሰት ተብሎ የሚሰራ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ የሆኑትን ማስወገድ የማይቀርና ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ነገር ግን ከዚህ በፀዳ ሁኔታ እንዲሰራ የሰራተኛ ክበቡ በህጋዊ መንገድ ተከራይቶ አገልግሎት እየሠጠ የሚገኝ ሲሆን ክበብ የሌለው ተቋም ነው በሚል የተፃፈው ከእውነት የራቀ ነው።

§  ከሚዲያ ጋር በማያያዝ ለተነሳው የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት አክብረው በባህል ላይ ከሚሰሩት በጋራ እየሰራንና ሰፊ ሽፋን እያገኘን ሲሆን እሴት ሳይጨምሩ ፕሮጀክት ብቻ በመቅረጽ የመንግሥትና የህዝቡን ገንዘብ ለግል ለመጠቀም  ከሚንቀሳቀሱት ጋር አለመስራት “አንድም ሚዲያ እንዳይደርስ?” ተደርጓል አያስብልም።

§  የታተሙ የመጽሐፍት ስርጭትን በተመለከተ በህጋዊ መንገድ ለተጠቃሚዎች መድረስ ሲገባው ህዝቡ ሳያውቀው በድብቅ በአቋራጭ ለመጠቀም የተደረገው ሙከራ እንዲከሽፍ ተደርጎ ከክልሉ ጋር በመነጋገር አላማውን ለማሳካት በመስራት ላይ እንገኛለን።

§  በማእከሉ በርካታ ታታሪ እና ሀቀኛ ሠራተኞች እንዳሉ የማይካድ ሀቅ ነው። ነገር ግን  በጣት የሚቆጠሩ እና ያሰቡትን ያልተገባ ጥቅም ማግኘት ያልቻሉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ጥያቄዎችን ለተለያዩ አካላት ቢያቀርቡም ጥያቄያቸው ከእውነት የራቀ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም።

§  ማዕከሉ የተቋቋመበትን ተልዕኮ ለመወጣት የሚሰራው በማዕከሉ የስራ ቦታ ውስጥ ተቀምጦ ሳይሆን ብሔር ብሔረሰቦቹ ወደሚገኙበት ክልል፣ ዞንና ወረዳ ተደራሽ መሆንን የሚጠይቅ ሲሆን በዚሁ አግባብም በርካታ ሥራዎች የተሰሩ በመሆናቸው  ያስገኘውን ፋይዳ ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንተወው። ነገር ግን ጥቅሙ በአንዳንድ ባለሙያዎች ኪስ የሚገባ ባለመሆኑ ይህንን አልመው የነበሩ ጥቂቶቹ ቅሬታ ቢያሰሙ የሚደንቅ አይሆንም።

§  መኪናን በተመለከተ መንግሥት ባስቀመጠው አሰራር እና ደንብ መሰረት የምንጠቀም መሆኑን እና ከትምህርት ማስረጃ ጋርም በተያያዘም የተፃፈውመንግሥት ያለበቂ ማስረጃ ሰዎችን እንደሚሾም በማስመሰል ሕዝብንና መንግሥትን ለማራራቅ የታሰበ ካልሆነ በስተቀር ህጋዊ የትምህርት ማስረጃ ከተወሰደ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ስለመሆኑ ማጣራት ለሚፈልግ ሁሉ ቢሮአችን ክፍት ነው።

§  በአጠቃላይ ማዕከሉ የተቋሙ ኃላፊ ከመሾማቸው በፊት አዳራሽ ከማከራየት በዘለለ ሚዛን የሚደፉ ተግባራትን የማያከናውን እንደነበረ እና ዛሬ የኢትዮጵያን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባህል እና የባህል እሴቶች ለማበልፀግ በለውጥ ጎዳና ላይ ያለ ስለመሆኑ ማንኛውም አካል መጥቶ እውነታውን መገንዘብ የሚችል ሲሆን መንግስት እና ህዝብ የኪራይ ሰብሳቢነትን ምንጮች ለማድረቅ ቁርጠኛ አቋም በያዙበት በአሁኑ ወቅት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሀሰት ቃላቶችን በመደርደር ትግሉን ለማደናቀፍ ማሸማቀቅ ይቻላል ተብሎ ከሆነ የታሰበው የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

§  ሀሳብን በነፃነት መግለፅ ዲሞክራሲያዊ መብት ቢሆንም ያልተደረገን ነገር ተደረገ ብሎ የሰዎችን ስብእና የሚነኩ ቃላት መጠቀም እና ስም ማጥፋት በህግም የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠንቅቀን ልንገነዘብ ይገባል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
839 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 93 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us