ከአምስት የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

Wednesday, 06 April 2016 12:38

 

በአሁኑ ሰዓት በክልላችን ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምንም እንኳን ረገብ ያለ ቢመስልም አሁንም በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ቀጥሎበታል።

ይህ ለበርካታ ዓመታት ተጠራቅሞ የፈነዳ የህዝብ ብሶት መንግስት በሥርዓቱ ጆሮውን ሰጥቶ ከሥር መሰረቱ ጥያቄዎቹን በውል በመረዳት በምላሹ ካልተንቀሳቀሰ ለሥርዓቱም ይሁን ለህዝባችን የሚበጁ እንዳልሆነ በተለያዩ ጊዜ ስናሳውቅ ቆይተናል። በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት በቅርቡ የሰጠው ምላሽ በተለይም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚ/ር መንግስታቸውን ተጠያቂ ማድረጋቸው የዘገየ ፍትህ እንደፍትህ አይቆጠርም እንደሚባለው ቢሆንም ችግሮቹ በተከሰቱበት ሰዓት በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ተቋማት ላይ ከማሳበብ ይልቅ ውለው አድረው የወሰዱትን እርምጃና አቋም በወቅቱ ቢወስድ ኖሮ ብዙ ጥፋቶች ሳይደርሱ መግታት ይቻል እንደነበር ፓርቲዎቹ በጋራ ገምግመናል።

ይሁን እንጂ ውለው አድረው የወሰዱትም እርምጃም ቢሆን ከአንገት ሳይሆን ከአንጀት ከሆነ የሚደገፍ ተግባር ነው እንላለን።

በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አብዛኛው በሚባል ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የህዝቡ ልማት ተቋርጧል። ቀበሌዎች ከሥራ ውጭ በመሆናቸው አገልግሎት ተቋርጧል። ይህም በራሱ በአገራቱና በህዝቡ ላይ የሚያመጣው ችግር ዘርፈ ብዙ እንደሆነ እናምናለን። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች እየተሰጡ አይደሉም፤ ይህንን ፓርቲዎች ከተለያዩ አካባቢዎች መረጃን ለመሰብሰብ ችለናል።

ሌላው አሁንም በሰበብ አስባቡ በፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ቤተሰቦቻቸው እንግልት ይደርስባቸዋል፤ ከመቶዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት ታጉረዋ፤ ሌሎች አካባቢያቸው ሸሽተው የደረሱበት አይታወቅም፤ ይህም ዋኛው የችግሮቹ አባባሽ እንጂ የመፍትሄ አካል እንዳሆነ እናምናለን።

መንግስት ጥፋተኞች ለፍርድ እንደሚቀርቡና በዚህ ሳቢያ ቤተሰብ ለሞቱባቸው ካሳ እንደሚከፍሉ ቢገልጽም በተግባር እስከአሁን ምንም ነገር ወደ መሬት የወረደ ነገር የለም። ከእስር የተፈታ የፖለቲካ ፓርቲ አባል አንድም አልተገኘም።

መንግስት ችግሩ የኔ ነው እስካለ ድረስ ተጠያቂው የራሱ ባስልጣናትና ታጣቂ እንጂ እንዴት ሌላ አካል ሊሆን እንደሚችል ግራ የሚያጋባ ሆኗል። በአንድ በኩል ረሃብ ከፍተኛ ስጋታችን ሆኖ እያለ በርካታ ዜጎችን በማሰር እና ከሥራ ውጭ አድርገው ቤተሰቦቻቸውን በረሃብና ለችግር ማጋለጥ ተገቢ አይደለም እንላለን።

በመሆኑም እኛ የኦሮሚያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሆንን ከዚህ እንደሚከተለው አስቸኳይ መፍትሄ ለህዝባችን እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

ከፌዴራል መንግስት የሚጠበቁ

1.  የፌዴራል መንግስት ያለ ሕግና ሕገ መንግስቱን በመጻረር በክልሎች ጣልቃ በመግባት የሚያደርገውን አፈናና ጫና እንዲያቆም እንጠይቃለን።

2.  የፌዴራል መንግስቱ በሕገ መንግስቱ በተቀመጠው አኳኋንና በተሰጠው ሥልጣን ብቻ ተወስኖ ሥራውን እንዲያከናውን እንጠይቃለን።

3.  በየሀገሪቱ የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሥራውን ለክልሉ ፖሊስ በማስረከብ ወደ ዋና ተግባሩና ድንበራችንን በማስከበር ሥራውን እንዲያከናውን እንጠይቃለን።

4.  የመከላከያ ሰራዊቱ በመበታተኑ ምክንያት የሚያስከትለው ሁኔታ አደገኛ በመሆኑ ለችግሮቹ መንግስት አፋጣኝ እልባት ሰጥቶ ወደ ካምፕና ድንበር ጥበቃ እንዲመለሱ እንጠይቃለን።

5.  መንግስት ጥፋተኛነቱን ቢያምንም እንኳን በአፋጣኝ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን አቋቁሞ የጥፋቱ መጠንና የተገደሉትን ቁጥር ለህዝቡ ተገልፆ ለቤተሰቦቻቸው ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን።

6.  የፌዴራል መንግስት ገለልተኛ ሽማግሌዎችን ከምሁራን፣ በሲቪክ ማህበራት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከታዋቂ ግለሰቦችና ከሀገር ወዳድ ግለሰቦች ጋር በችግሩ መነሻና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ተነጋግሮ ብሔራዊ መንግስትና እርቅ ሰላም እንዲወርድ እንጠይቃለን።

7.  ጠ/ሚ/ሩ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ አመቻችቶ እንዲያወያዩ እንጠይቃለን።

ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚጠበቁ

1.  በአሁኑ ሰዓት በስብሰባ ምክንያትና ለተፈጠረው ህዝባዊ አመፅ ምክንያት የቀበሌዎች መስተዳድሮች ሥራ ያቆሙ በብዛት የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን ቀበሌዎች መልሰው በማደራጀት ስም በህዝቡ ላይ የሚደርሰው እስራትና ግርፋት እንዲቆም እንጠይቃለን።

2.  የተቋረጡ ማህበራዊ አገልግሎቶች ማለትም የህክምና ተቋማትና የት/ቤቶች አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲቀጥሉ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

3.  ያለፍርድ የታሰሩ ዜጎች እንዲለቀቁ እንጠይቃለን።

4.  ሕዝቡን የበደሉ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ባለሥልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

5.  በረሃብ የተጎዱ ወገኖች እርዳታ በአግባቡ እንዲደርስና በቀጣዩም ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ እንጠይቃለን።

6.  የጋራ ም/ቤቱ በኦህዴድ ምክንያት መደበኛ ስብሰባው እየተዘለለ በመምጣቱ ገዢው ፓርቲና የክልሉ መንግስት ትኩረት እንዲሰጡና በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችና የፖለቲካ ምስቅልቅሎች ላይ ውይይት እንዲደረግና የመፍትሔ አቅጣጫ ተቀምጦ ለህዝብ እንዲገለጽ እንጠይቃለን።

7.  የክልሉ ፕሬዝዳት በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠረው ህዝባዊ አመፅና ቀውስ ከሥሩ ለመፍታት እንዲቻል ከባለድርሻ አካላቱ በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት በሙሉ በጋራ የሚገናኙበት መድረክ ተመቻችቶ ውይይት እንዲካሄድ፣ እኛ በኦሮሚያ ክልል የምንንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም

1.  የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፤

2.  የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር (ኦአነግ)፣

3.  የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ (ገስአፓ)፤

4.  የኦሮሚያ ነፃነት ብሔራዊ ፓርቲ (ኦነብፓ)

5.  የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር (ኦነአግ)

ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት የመፍትሄ ቁልፍ ነው ብለን ስለምናስብ በአስቸኳይ መንግስት ተግባራዊ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

                           መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም

                             ፊንፊኔ/ አዲስ አበባ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
608 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 924 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us