የግንቦት 2ዐ ትሩፋቶች እና ተግዳሮቶች

Wednesday, 11 May 2016 12:37

 

ከስንታየሁ  ግርማ

SintayehuGirma 76 @gmail.com

በነፃነት ኮርተን ለዘመናት ኖረናል፡፡ ይሁንና ድኀነትም አንገታችንን አስደፍቶ ቅስማችንን ሰብሮ ቆይቷል፡፡ ዛሬ ግን ምሥጋና ለታታሪው ሕዝባችን እና ልማታዊ መንግሥታችን በገጠርም ሆነ በከተማ በልማታዊ መንገድ ሀብት መፍጠር ዋነኛ ሥራችን ሆኖ የአስከፊው ድህነታችን ታሪክ እየተቀየረ ነው፡፡ የ97 ሚሊዮን ኩሩ ሕዝባችን አገር የሆነችው ኢትዮጵያ በታታሪ ልጆቿ ጥረት ድኀነትን ድል እየነሳች ነው፡፡

 ባለፉት 24 ዓመታት በተለይም ደግሞ ባለፉት 15 ዓመታት ኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት እና በተከታታይ እየደገች መሆኗን ማንም ሊክድ አይችልም፡፡ የሕዝባችን የብልፅግና  ጥያቄም ምላሽ እያገኘ ያለው ኢህአዴግ በነደፋቸው እና በጥብቅ ተግባራዊ ባደረጋቸው ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡

ኢሕአዴግ ሀገሪቱን ከደርግ ነፃ ካወጣ በኋላ ከዓለም ባንክ እና ከአይ ኤም ኤፍ ጋር በመሆን የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በነፃ ገበያ እንዲመራ ለማድረግ ስንቀሳቀስ ድርጅቶቹ የመንግሥትን ሚና ወደ ዜሮ ለማውረድ ያደረጉትን ከፍተኛ ዘመቻዎች በፅናት ተቋቁሟል፡፡ በወቅቱ በዓለም ላይ የኒዮሊብራሊዝም የበላይነት በተግባር የተረጋገጠበት ነበር፡፡ ዘመኑም የኒዮሊብራሊዝም ሊባል የሚችል ነበር የሶቬየት ካምፕ መፈራረስ ከኒዮሊብራሊዝም የተሻለ ርዕዮተዓለም እንደሌለ በተግባር የተረጋገጠበት ነበር፡፡ እንግዲህ በዚህ አላማው ሁኔታ ውስጥ ነው ኢህአዴግ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የነፃ ገበያ መርሆዎችን ተቀብሎ ቢተገብርም የመንግሥትን የዘበኝነት ሚና በጥብቅ የተቃወመው ኢህአዴግ በወቅቱ የኢኮኖሚ ዋና-ዋና ተቋማት (“Commanding Economic Heights”) ለሕዝብ ጥቅም በሚል በመንግሥት ቁጥጥር እንዲቆይ ያደረገው፡፡

ይህንን በማድረጉ ደግሞ ዛሬ አለምን ያስደመመ ዕድገት እና ልማት ለማስመዝገብ የቻልነው፡፡

እ.ኤ.አ. 2008 የተከሰተውን የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ በአብዛኛው ለመቋቋም የቻልነው  በፍትሀዊነቱ የተመሰከረለት ዕድገት እና ልማት ለማስመዘገብ የቻልነው የእኛ ዕድገት እና ልማት ከመጀመሪያውኑ ድሀ ተኮር ስለሆነ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ከእኛ የተለየ ርዕዮተዓለም የሚከተሉት ሳይቀር የመሰከሩት ነው፡፡  “One foot on the ground, One foot in the AIR Ethiopians delivery on an ambitious development agenda.” በሚል ርዕስ Sep.2015 ባወጣው ሪፖርት መሠረት የኢትዮጵያ ዕድገት ድሀ ተኮር በመሆኑ ሀገሪቱ ድኀነትን በከፍተኛ መጠን በመቀነስ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል በሕዝቦች መካከል እንዲኖር በማድረግ ተጠቃሽ ናት ይላል፡፡ የፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ዋና-ዋናዎቹ መመዘኛዎች ትምህርት፣ ጤናና የዕድሜ ጣሪያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ አፈፃፀም አለም አቀፍ ዕውቅና የተቸራቸው ናቸው፡፡ ከፍትሃዊ የሀብት መመዘኛዎች መካከል የዕድሜ ጣሪያን ከ49 ወደ 65 ከፍ ማድረጓ ተረጋግጧል፡፡

ለዚህ ደግሞ የእናቶችና የሕፃናት ሞት መቀነስ፣ እንዲሁም ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር መቀነስ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ይሁንና አሁንም ከኢትዮጵያ ሕዝብ  20 በመቶ በድኀነት ወለል ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህ ቁጥር ከፍተኛ ነው፤ ትኩረት ተሰጥቶት መቀየር ይገባዋል፡፡ ዘኢኮኖሚስት እንደሚለው ከሆነ የአፍሪካ ወጣቶች ሶስት ነገሮች ይፈልጋሉ፡፡ የትምህርት ዕድል፣ የሥራ ዕድል እና የኃሳብ ነፃነት ለእነዚህ ወጣቶች በከተማም በገጠርም የሥራ ዕድሎች መፍጠር ቅድሚያ ተሰጥቶት መሠራት ያለበት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል ከፍተኛውን  ይሸፍናል፡፡ ይህ ጥንካሬው ወጣቱ አምራችና እና ሥራ ፈጣሪ ከሆነ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ በማድረግ የኢትዮጵያ ኀዳሴን ለማረጋገጥ ሁነኛ መሣሪያ ነው፡፡ የሥራ ዕድል ካልተፈጠረለት ደግሞ ለማኀበራዊ ቀውስ ዋነኛ መንስኤ ይሆናል፡፡

የቱኒዚያ አብዮት ሲነሳ በድኀነት ወለል ውስጥ ይኖር የነበረው ሕዝብ አምስት በመቶ ነው፤ ከዚህ ልንማር ይገባል፡፡ በድኀነት ወለል ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ በተለይም ወጣቱን የነገው ተስፋ ብሩህ መሆኑን ማሳየት እና ለዚህም መሥራት ይገባል፡፡ 

የኢትዮጵያ የነገ ተስፋ ብሩህ እንደሆነ ደግሞ ብዙዎቹ መስክረውለታል፡፡ ዘንድሮ ያጋጠመን ድርቅ እንኳን የኢትዮጵያ ፈጣን ዕድገት እንዳልተቋረጠ ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተቸራቸው ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው፡፡  “ Ethiopia has been nothing up fastest growth of any African and world economy turning nearly 11% a year, mail and Guardian, 19 march 2016 Ethiopia has the fastest growing economy in the world and has Lifted millions of citizens out of poverty, USA to day march 13, 2016. How ethiopia over come the worst a roughen in 50 years Times.feb 11,2016,

ይህ ሲባል ግን የተከሰተውን ድርቅ ማሳነሴ አይደለም ፤ ምንም እንኳን ድርቅ በማንኛውም ሀገር እና ጊዜ የሚፈጠር ቢሆንም ድርቅ ወደ ረሀብ እንዳይቀየር ማድረግ የመንግሥታት ዋነኛ ሥራ ነው፡፡ ይህንን ማድረጉ መንግስትን ያስመሰግነዋል፡፡ ዛሬ የቴክኖሎጂ ዘመን ስለሆነ የተለያዩ የውኃ አማራጮችን ተጠቅሞ ድርቅንም ማስቀረት ስለሚቻል እየተለወጠ ባለው ገፅታችን ላይ ጥላሸት እየቀባ ያለውን ድርቅ አስቀድመን መከላከል ይኖርብናል፡፡

ሌላው የግንቦት 20 ትሩፋት የኀዳሴው ግድብ ነው፡፡ የኀዳሴው ግድብ የይቻላል መንፈስ የፈጠረ ነው፡፡ የዘመናት ቁጭትንም የመለሰ ነው፤ ኢትዮጵያን ከአድዋ ድል በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ያስተዋወቀ ነው፡፡ ኢህአዲግ ያለፉት መንግሥታት በብዙ ዓመታት ድምር ታሪክ ያልሠሩትን በ25 ዓመታት ገንብቷል፡፡ ምሥስጋና ለባለራዕዩ መሪያችን ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛ ገቢ ስትገባ ሊያጋጥማት የሚችለውን የኃይል እጥረት ግምት ውስጥ በማስገባት እና በተፈጥሮ ሀብት የመጠቀም መብታችን እውን ለማድረግ የኀዳሴው ግድብ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ተጀመረ፡፡ አንድ ችግርን ለመፍታት ሁለት ዓይነት ዘዴዎች አሉ፡፡ የተለመደ እና ፈጠራ የታከለበት በሚል፡፡ የተለመደ ዘዴ ከአሁኑ ሁኔታዎች ይነሳል፤ ራዕይን ግምት ውስጥ አያስገባም፡፡ የችግሩን መንስኤ ጥልቅ ትንታኔ አያደርግም፡፡ ለምሳሌ ዛሬ 100 ሜጋ ዋት የኃይል እጥረት ካለ፤ 100 ሜጋዋት ብቻ ይገነባል፡፡

ሁለተኛው ማለትም ፈጠራ የታከለበት ዘዴ ግን ከራዕይ ይነሳል፡፡ ከዚያም አሁን ያሉትን ሁኔታዎች የትናትና ርዕዩ ላይ ለመድረስ መሠራት ያለባቸውን ይሠራል፡፡ የታላቁ ኀዳሴ ግድብ ከአሁኑ ሁኔታዎች ትንታኔ ብንነሳ ሊሠራ አይችልም፤ የአሁኑ የኃይል እጥረት በመቶ ሜጋ ዋቶች የሚገመት ነው፡፡ የአካባቢው ፖለቲካ ሁኔታ አለ፤ የግብፅ አቋም አለ፤ የውጭ ብድር እና ዕርዳታ ለኀዳሴው ግድብ የሚሰጥ የለም፡፡ ራዕይ ለሌለው መሪ እነዚህ ተስፋ አስቆራጭ ናቸው፡፡ ራዕይ የሌለው ሕዝብ ደግሞ ይጠፋል፡፡ የኀዳሴውን ግድብ ለመገንባት መልካም አጋጣሚ የንጉሡ እና የደርግን ዘመን ነበር፤ በወቅቱ የቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት የተፋፋመበት ወቅት ስለነበር ሁለቱ ጐራዎች በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመሥራት ድጋፍ ቢጠየቁ አይናቸውን አያሹም ነበር፤ ግብፆች የአስዋን ግደብ የሠሩት በሶቬየት ከፍተኛ ድጋፍ ነበር፡፡ የእኛዎቹ መሪዎች ራዕይ ስላልነበራቸው ተግባራዊ አላደረጉትም፡፡

ምስጋና ለታላቁ መሪያችን ይግባና ኢትዮጵያ የዛሬዋን የኃይል ፍላጎት የሚያሳካ እና በመካከለኛ ገቢ ስትደርስ የሚያስፈልጋትን የኃይል ፍላጎት ግምት ውስጥ ያስገባ ራዕይ በመንደፍ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ 5ዐበመቶ አድርሰነዋል፡፡ ታላቁ የኀዳሴ ግድብ የባለራዕዩ መሪ ውጤት ነው፡፡ የታላቁ ኀዳሴ ግደብ በተለመደው ችግርን የመፍታት ዘዴ ቢሆን ኖሮ እውን ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ በዚህ ዘዴ የሚያስፈልገንን 100/200/300 ሜጋዋት ስለሚሆን ኀዳሴውን ግድብ ማለም አይቻልም፡፡

መነሻችን ራዕይ ሳይሆን የአሁኑ ሀኔታዎች ቢሆኑ ኑሮ ብዙ መሰናክሎች ስላሉ የኀዳሴው ግድብ አይታሰብም፡፡  ገንዘቡ  ከየት ይመጣል? አካባቢው ያልተረጋጋ ነው፤ የግብፅ ተሰሚነት፣ … ወዘተ የሚሉት ተስፋ ስለሚያስቆርጡ ከአሁኑ ትንታኔዎች ብንነሳ የኀዳሴው ግድብ ዕውን ሊሆን ይቅርና ለታሰብ አይቻልም፡፡

ምሥጋና ለባለራዕዩ መሪያችን የነገ የሀገሪቱን ዕጣፋንታ በማየት ሕዝቡን ከራዕዩ ጋር በማሰለፍ ይኸው የኀዳሴውን ግድብ እውን እያደረገ ነው፡፡ ከዚህ ለመረዳት የሚያለው ሕዝብ በአንድ ራዕይ ዙሪያ ከተሰባሰበ ተአምር መሥራት እንደሚችል ነው፡፡ 

ራዕይ የሌለው ሕዝብ በትንሹ በትልቁ እየተናተረከ እና እየተቆራቆሰ ይጠፋል፡፡ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የይቻላል መንፈስ በመፍጠር ዜጎች በራዕዩ ዙሪያ ማሰባሰብ በመቻል አንድነታችን የበለጠ ሊያጠናክር እንደሚችል ያስተማረ ነው፡፡

ከግንቦት 2ዐ ቱርፋት አንዱ ደግሞ ሀገሪቱን ከብተና ያዳነ መሆኑ ነው፡፡ በ1983 ኢህአዴግ ሀገሪቱን በተቆጣጠረበት ወቅት በዓለም ላይ ያሉ የሶሻሊስት ካምፕ የተሸነፈበት በመሆኑ ርዕዮተዓለሙን የሚከተሉት ሀገሮች ወደ መበታተን በፍጥነት አምርተዋል፡፡ የቀድሞው ሶቬየትኀብረት ወደ 15 የዮጎዝላቪያ ወደ አምስት ሀገሮች ተፈረካክሰዋል፡፡ የተመድ ዕውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ ስለዚህ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ መጣ፡፡ ዓለምአቀፋዊ ልማዳዊ ህግ (International Customer Law)  እየሆነ ነው፡፡ ከሀገራችን ኤርትራ አስቀድማ ነፃነቷን አግኝታ ነበር፡፡ በሀገራችን 17 የታጠቁ ድርጅቶች ነበሩ በቀላሉ የማይገመቱ ማኀበራዊ መሠረት ነበራቸው፡፡

ስለዚህ ከዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ጋር ተደምሮ በወቅቱ የእንገንጠል ጥያቄ በስፋት ይቀርቡ ነበሩ፡፡ ይህንን መልካም አጋጣሚ እንጠቀምበት የሚለው ብዙ ነበር፡፡ ይሁንና ባለራዕይ መሪያችንን በተከተሉት ብስለት የተሞላበት አመራር ሁሉም ብሄር/ብሔረሰቦች እና የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት በመመሥረት እና በኋላም በኀዳር 29/1987 ህገ መንግሥቱ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ዕውቅና በማግኘቱ እና ሕዝቡ በራሱ ቋንቋ መማር፣ መዳኘት እንዲሁም ራሱን በራሱ በማስተዳደሩ የጥገኝነት አባዜ የተጠናወታቸውን ከኀብረተሰቡ በመነጠል ወደ ዳር እንዲወረወሩ አደረጋቸው፡፡  በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው አ/አደሩ ያመረተውን ምርት የሚወስድበት መንግሥት ሳይሆን ያለው ምርት በገበያ በተለይም ደግሞ በዓለም ገበያ መመራት አለበት ብሎ ወደ ዓለም ገበያ ዘልቆ ለመግባት

በመቻሉ የአገራችን አ/አደሮች የዋጋ መወደቅ ሥጋት ሲያስጨንቃቸው ያለማቋረጥ ምርታማነታቸውን በማሳደግ ለመጠቀም የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ምርት ለማሳደግ የሚያገለግል የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ጥያቄዎችም ያለማቋረጥ እየጨመረ ሄዷል፡፡ አርሶ አደሩ የምርት ነፃ ተጠቃሚ በመሆኑና ምርታማነቱም እየተሻሻለ በመሄዱ አብዛኛው የአገራችን ሕዝብ ከልማቱ ፖሊሲው ተጠቃሚ እየሆነ ነው፡፡ በተጨማሪም በገጠር የተመሠረተ የጤና ተቋማት የንፁህ መጠጥ ውኃ የመንገድ፣ የስልክና የኤሌትሪክ አገልግሎት መስፋፋት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ እያጠናከረው በመሆኑ አርሶ አደሩ እራሱን በራሱ የማስተዳደር ህልሙ እውን በመሆኑ ለፅንፈኞች ህልም ማኀበራዊ እና ፖለቲካዊ መሠረት ሊሆን አይችልም፡፡ አርሶ አደሩ እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር በመደረጉ በየጊዜው የዲሞክራሲ ባህሉ እየጎለበተ ከመምጣቱም በላይ በየጊዜው እያደገ የሚሄድ የተለያዩ ፍላጎቶቹን እንዲሟላለት በተደራጀ መልኩ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በመሠረቱ የእኛ ዕድገት በዋናነነት በአርሶ አደሩ ጉልበት ላይ  የተመሠረተ ነው፤ ጉልበቱን ሳይቆጥብ ምርትና ምርታማነት ላይ እንዲያውል ዲሞክራሲ ያስፈልገዋል፡፡ የራሱ ኃሳብ እንዲሰማለት ይፈልጋል፡፡ በመረጠው ሰው መተዳደር ይሻል፡፡ ሳይፈልግ የመሻር መብት እንዲጠበቅለት ይፈልጋል፡፡

በራሱ ቋንቋ ሊማርና ሊዳኝ ይገባል ፡፡ ይህም በመሆኑ ማለትም ዲሞክራሲያዊ መብት ስለተረጋገጠለት እና ተግባራዊ ስለተደረገለት ነው፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብቱ በህገ መንግስቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በአንድነቱ ውስጥ መኖር ካስፈለገ የመገንጠል መብቱ በህገ መንግስቱ እውቅና አግኝቶበታል፡፡ ይህ ተግባር በአለም ብቸኛ ያደርግለታል፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ህገ-መንግስታዊ እውቅና ማግኘትና ማገዝ ይሰጠዋል፡፡ መብቱ አርሶአደሩ ተረጋግቶ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ላይ እንዲያተኩረ ይረዳዋል፡፡ ከህጉ መንግስቱ እውቅና በተጨማሪ ዋናው በተግባር የብሄር የብሄረሰቦች መብት ያለ ገደብ ማክበር ነው፡፡ እንግሊዝ በህገ-መንግስቱ (ያልታቀፈ ቢሆንም) ባይፈቅድም መገጠል እውቅና  ሰጥቶ ለስኮትላንድ ህዝብ ውሳኔ ፈቅዳለች፡፡ ጠ/ሚ/ር ዴቪድ ካሜሩን የስኮትላንድ ህዝብ ውሳኔ ህጋዊ መሠረት ባይኖረውም ዲሞክራት ለመሆን ህዝብ ውሳኔው ፈቅጃለሁ ብለዋል፡፡ ከስፔን ካታሎናዊያን አቻ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀግንና ለፌዴራል መንግስት የምንሰጠው ገንዘብ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የራሳችን መንግስት የመመስረት ውሣኔ ሊከበርልን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ እየጠየቁ ነው፡፡

ስለዚህ የማንነት ይከበር የሚል ጥያቄ በህገ-መንግስት ቢጻፍም ባይፃፍም በተግባር ካልተተገበረ ጥያቄው እንደሚነሳ ከስኮትላንድና ከካተሎናውያን ልምድ መረዳት ይቻላል፡፡ የህዝቡ ውሳኔ ስለተከበረ አለምን ያስደመመው ዕድገት ሊመዘገብ የቻለው፡፡ ይሁንና ምንም እንኳን የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት በሕገ መንግሥቱ ቢረጋገጥ ተግባራዊ ቢደረግም አሁንም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች አሉ፡፡ ጠባብነትና ትምክህት እና የሀይማኖት አክራሪነት በልማት እና በዲሞክራሲ የተጓዘውን ጉዞ ያህል በመልካም አስተዳደር አልተጓዝንም፡፡ አሁንም ቢሆን አንዳንዴ የመንግሥት አገልግሎት በብሄር፣ በሀይማኖት፣ በጥቅም በመስጠት ሕዝቡን ወደ ምሬት እየከተቱት ነው፡፡ በብሔር፣ በሀይማኖት፣ በገንዘብ ምክንያት አገልግሎት እየተከለከልኩ ነው ብሎ የሚምረው የሕ/ሰብ ክፍል እየበዛ ከመጣ ለኀዳሴው ጉዞ ተግዳሮት መሆኑ አይቀርም፡፡

በመሠረቱ ጥገኞች ብሄር/ሃይማኖት/ የላቸውም ለሰው ልጅ በሙሉ ጥሩ አመለካከት የሌለው ለብሔሩ፣ ለሀይማኖቱ ጥሩ አመለካከት ሊኖረው አይችልም፡፡ ብሔር ለጥገኛ ዓላማ ኔትዎርክ ለማደራጀት የሚጠቀሙበት ነው፡፡ የሌሎችን ብሔር አጥቅቶ ከጨረሰ በኋላ ጅብ የራሱን ሥጋ እንደሚባለው ሁሉ ወደ እነሱ ብሔር መዞሩ አይቀርም፡፡ ስለዚህ አሠላለፉ ሁሉም ዲሞክራቲክ ብሔሮች በአንድ በኩል ሌላው በሁሉም ብሔር የሚገኝ ጥገኛ በአንድ በኩል መሆን አለበት፡፡ ፍልሚያውም በኪራይ ሰብሳቢነትና በልማታዊ ኃይሎች እንጂ በብሄር/በሃይማኖት ሊሆን አይገባም፡፡  ስለዚህ አሁን የተጀመረው የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ይህ ትግል የሕልውና ትግል ነውና ፍልሚያው ቀላል አይደለም፡፡ መልካም አስተዳደር የማስፈን ጉዳይ እንደ ቅዳሜ እሑድ የክት ልብስ አይደለም፡፡ ከፍተኛ መሥዋዕትነትና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡  በትግሉ ኪራይ ሰብሳቢው በዘረጋው ኔትዎርክ እና በተዋቡና በተሰደሩ ቃላቶች መንግሥትን ለማስመድመድ የሞት ሽረት ትግል ማድረጉ አይቀርም።

ይሁንና ልማታዊ ኃይሎች በተደራጀ መልኩ በመረጃ ላይ በተመሠረተ ትግልና እንቅስቃሴ ከሁሉም በላይ ተስፋ ባለመቁረጥ እና በከፍተኛ ቁርጠኝነት (ከግንቦት 20 መስዋዕትነትና ፅናት በመማር) የመልካም አስተዳደር ትግሉን ከዳር እስከ ዳር ለማድረስ የሚከፈለውን መሥዋዕትነት በመክፈል የኢትዮጵያን ሕዳሴ እውን ማድረግ ይገባናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
600 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 828 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us