ከዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) የተሰጠ መግለጫ

Wednesday, 29 June 2016 12:38

 

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ሰኔ 11 ቀን 2008 ዓ.ም በሶዶ ከተማ አካሂዷል።

በዚህ ጉባዔ የግንባሩ የሥራ ሪፖርት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ፣ በሰነድነት እንዲያዝ ተደርጓል።

ጉባዔው ተሻሽለው የቀረቡ የግንባሩ ፖለቲካ ፕሮግራምንና መተዳዳሪያ ደንብን በማስመልከት በሰፊው በመወያየት አፅድቋል።

ከሕዝብ ቁጥር ዕድገት ጋር ተጣጥሞ ሊሄድ ካልቻለ ከግብርና ኢኮኖሚ በተፋጠነ ሁኔታ መለቀቅ የሚቻልበት የአሠራር ሥልት ምን መሆን ይገባል በማለት የተነሳ ነጥብ የጉባዔውን ልዩ ትኩረት የሳበ ሆኖ ውሏል።

   -    ዎላይታ ያላትን ጥሩ መልካም - ምድራዊ አቀማመጥን፤

   -    በስድስት በር ለተመጋጋቢ ዕድገት በሚያመቺ መልኩ፤ ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያገናኝ መንገድን

   -    ከሁሉም ባልተናነሰ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ ያለውን የትራንስፖርትና መገናኛ አገልግሎትን

   -    ከበቂ በላይ ሆኖ የሚገኝ የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃን

   -    ለየተፈላጊ የሥራ እንቅስቃሴ ተስማሚ የሆነውን የደጋ፣ የወይናደጋና የቆላማ አየር ጠባይን በመጠቀም በክልሱ ውስጥ ንግድና ኢንዱስትሪ በተፋጠነ ሂደት እንዲስፋፋና እንዲበረክት ማድረግ አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን የጉባኤው አባላት የበለጠ አጠንክረው መገንዘብ ችለዋል።

ሁሉም የሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለጉዳዩ ከመቼውም የተለየ ትኩረት እንዲሰጡ፣ በተለይም በሁለተኛ ዙር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በከፍተኛ ግምት እንዲካተት እንዲደረግ፣ ነዋሪ ሕዝብም በየተሰማራበት መስክ የኢኮኖሚ አርበኛ ሆኖ እንዲያበረክት የሚጠበቅበት ድርሻ የላቀ በመሆኑ በጋለ ተነሳሽነት እንዲንቀሳቀስ ጉባዔው ጥሪ አድርጓል።

በአሁኑ ጊዜ በአካባቢው በአንዳንድ ሥፍራዎች የሚንፀባረቁ የሰላም እጥረቶችና የመልካም አስተዳደር ጉደሉቶችም ጨርሶ እንዲወገዱ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላትና የነዋሪ ሕዝብ አስተዋፅኦ መጓደል እንደሌለበት ጉባኤው አሳስቧል።

የግንባሩ ድርጅታዊ ጥንካሬ የሚጎለብትንና በቀጣይ ምርጫዎች ወቅት መደረጉ የሚገባቸውን በማስመልከትም ጉባኤው በዝርዝር ተመልክቷል።

በመጨረሻም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የማዕከላዊ ም/ቤት አባላትንና የልዩ ልዩ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ አካሂዷል።

  1.  አቶ ተክሌ ቦረና              ሊቀመንበር

  2.  አቶ ዮስፍ ዳረቦ              ም/ሊቀመንበር

  3.  መ/አ ኃይለሚካኤል ግዛው      ዋና ፀሐፊ

  4.  አቶ ዘብዲዮስ ጎበና            ም/ዋና ፀሐፊ

  5.  አቶ በረከት ገ/ማርያም         ሒሳብ ሹም

  6.  ወ/ሮ አሰለፈች ባንጫ          ገንዘብ ያዥ

  7.  አቶ ዓለማየሁ አዴ           ድርጅት ጉዳይ ኃለፊ

  8.  አቶ ጴጥሮጥ ጵልጦ          ዕቅድና ክትትል ጉዳይ ኃላፊ

  9.  አቶ ሥላሴ አይመሎ          የሕግና ደንብ ጉዳይ ኃላፊ

 10.አቶ ዋርካሼ ዋኤ             የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሁነው እንዲያገለግሉ ተመድበው ጉባዔው ተጠናቋል።

 

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር

(ዎሕዴግ)

ሰኔ 17 ቀን 20085 ዓ.ም

አዲስ አበባ¢

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
572 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 978 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us