በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሳምንታዊ አቋም መግለጫ

Thursday, 07 July 2016 15:24

 

ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም

በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ በሚኖረን ሚና የሀገራችንንና

የአህጉራችንን ጥቅም እናስጠብቃለን!

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ የጀመርናቸው ጥረቶች አበረታች ውጤት እያሳዩ ናቸው። ድህነትን በማሸነፍ የበለፀገ ህዝብና ሀገር ለመፍጠር የጀመርነው ጉዞ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ጭምር ተገቢውን ክብር እያሰጠን ይገኛል።

የአፍሪካ ሀገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ሀገራችን እንድትወክላቸው  የመረጧት በሙሉ ድምፅ ነው። ከ190 የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት መካከልም 185 ያህሉ ሀገራችንን ለፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት መርጠዋታል። ይህ እውነታ በዓለም ማህበረሰብ ፊት ሀገራችን ተገቢ ቦታ እያገኘች የመምጣቷ ማሳያ ነው። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉ።

ሀገራችን በጀመረችው የፀረ ድህነት ትግል ላይ ቁርጠኛና ታማኝ መሆኗን አሳይታለች። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስቀመጠውን የሚሊኒዬም የልማት ግብ አስቀድማ ከማሳካቷም በላይ ለተከታታይ 12 ዓመታት ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች። ዓለም በረሃብና ጉስቁልና የሚያውቃት ሀገር በ50 ዓመታት ውስጥ ገጥሟት የማያውቀውን የከፋ ድርቅ በዋናነት በራሷ አቅም ተቋቁማ ዜጎቿን መታደግ ችላለች።

ባልተረጋጋው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ብትገኝም የራሷን ሠላም አረጋግጣ የጎረቤት ሀገራትን ሠላም ለማስከበር ረጅም ርቀት እየተጓዘች ትገኛለች። የዓለማችንን ንፁሃን ለመታደግ በኮንጎ፣ በላይቤሪያ፣ በቡሩንዲ፣ በሩዋንዳ፣ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳንና በዳርፉር ከ12ሺህ በላይ ሠራዊቷን አሰልፋ ተልዕኮዋን በብቃት እየተወጣች ትገኛለች።

በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚወጡ ህጎችን ተቀብላና ከራሷ ህጎች ጋር አዋህዳ ለዜጎቿ ሠብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ከማዋሏም በተጨማሪ የተቋማቱን ተልዕኮዎች ተቀብላ በብቃት ስትወጣ ቆይታለች።

የዓለም አቀፉ የፀረ ሽብር ዘመቻ አካል በመሆን በራሷና በጎረቤት ሀገራት ውስጥ ውጤታማ ትግል አድርጋለች። ለዜጎቿ ልማትና ሠላም መረጋገጥ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በድርድር የመፍታት ስልትንም እንደዋና መርህ ይዛ ትገኛለች።

የአፍሪካ ሀገራትን በሊግ ኦፍ ኔሽን በብቸኝነት እንደወከለች ሁሉ አሁንም በዓለም አቀፍ መድረክ አፍሪካውያንንና የዓለምን ጭቁን ህዝቦችን በመወከል በመታገል ላይ ትገኛለች።

እነኚህና መሰል የበሰለ የዲፕሎማሲና የፖሊሲ ተግባሮቿ አፍሪካውያንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዕምነት እንዲጥሉባት አድርገዋል። ባለፉት ወራት በተደጋጋሚ እንደታየው የዓለማችን ታላላቅ ሀገራትና ተቋማት መሪዎች በወዳጅነት የሚጎበኟትና የሚጋብዟት ሀገር ለመሆን በቅታለች።

ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት በሁሉም አፍሪካውያንና ሁሉም በሚባሉ የድርጅቱ አባል አገራት መመረጧም የዚህ ዲፕሎማሲ ድሏ ውጤት ነው።

ሀገራችን ከ2009 ዓ.ም ጥር ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና እንድትሰራ በዚህ መልኩ መመረጧ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ታላቅ ክብር፣ ለህዳሴ ጉዟችን ጥረትም ተገቢ ዕውቅና ነው።

ሀገራችን የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በምትሰራባቸው ጊዚያት ለዓለም ህዝብ፣ ለአፍሪካዊያንና ለሀገራችን ጥቅም በፅናት መቆሟን ትቀጥላለች። የኢፌዴሪ መንግስት ባለፉት ዓመታት በተከተልነው ትክክለኛ መስመር ያገኘነው ይህን ዕድል ለኢኮኖሚያችንና ለልማታችን በሚጠቅም መልኩ አሟጦ እንደሚጠቀምበት በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ቃል ይገባል።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
501 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 931 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us