“ከኃይል እርምጃ በፊት ውይይት ይቅደም!”

Thursday, 14 July 2016 16:06

“ከኃይል እርምጃ በፊት ውይይት ይቅደም!”

የኢትዮያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

 

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሃና ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ቀርሳ ኮንቶማ በመባል የሚታወቀው ሰፈር ላይ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ህይወትና በአካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። በዚህ መስተዳድሩ ህገወጥ ቤቶችን አፈርሳለሁ በሚል ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በፈጠረው ችግር በሰው ህይወትና በአካል ላይ በደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል። በዚህም ግጭት በሰው ህይወትና በአካል ላይ ከደረሰው ጉዳት ሌላ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች በጅምላ መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል። አስተዳድሩ ህገወጥ ግንባታን የመከላከል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአካባቢው ከሚገኙ አባሎችንና ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በደረሰን ጥቆማ እነዚህ ከተሰሩ አብዛኞቹ ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸውን ቤቶች በሌሎች አማራጮች ከነዋሪው ጋር በመወያየት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በዚህ የክረምት ወቅት ቤቱን ለማፍረስ መንቀሳቀስ ከአስተዳደርም ሆነ ከሞራል አኳያ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በመሆኑ የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ድርጊቱን አጥብቆ ይኮንናል። በተጨማሪም ከ5 ዓመት በላይ የመብራት፣ የውሃና መንገድ የመሳሰሉ መሠረተ ልማቶችን ሲያሟላ የነበረና የነዋሪነት መታወቂያ ሲሰጥ የነበረ አስተዳደር ያለምንም ተጨማሪ ውይይት ወቅቱን ያላገናዘበ ጅምላ እርምጃ ለመውሰድ መንቀሳቀሱ ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት እንደሆነ የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ለመረዳት ችሏል። በተጨማሪም ህብረተሰቡ ህገወጥ ግንባታን መስተዳድሩ የመከላከልና የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዳለበት በመረዳት አስፈላጊውን መረጃ የመስጠትና የመተባበር ግዴታውንም በአግባቡ መወጣት እንዳለበት ኢዴፓ ለማሳሰብ ይወዳል። ስለዚህ፡-

1.  አስተዳድሩ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግ ቅድሚያ በመስጠት ወቅቱን ያልጠበቀ በጅምላ የማፍረስ እርምጃውን በአስቸኳይ እንዲያቆምና የፖሊስ ኃይልም ከኃይል እርምጃና ከጅምላ አፈሳ እንዲቆጠብ፣

2.  የሰው ህይወት ከቀጠፈው ግጭት ጋር ተያይዞ የታሰሩ ነዋሪዎች ግልጽ በሆነ የፍትህ ስርዓት ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ በአስቸኳይ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ፤

3.  ህብረተሰቡም ጉዳዩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች ተቆጥቦ ህጋዊና ሰላማዊ መንገዶችን ብቻ ተጠቅሞ ጉዳዩን ለመፍታት እንዲንቀሳቀስ፣

4. አስተዳድሩም ህገወጥ ግንባታዎችን የመከላከል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በቦታው ላይ የሚመድባቸውን ኃላፊዎች ብቃታቸውን አረጋግጦ በመመደብና ህብረተሰቡ ገንዘቡን፣ ጉልበቱን ህገወጥ ግንባታዎች ላይ ከማዋሉ በፊት አስቀድሞ ሕገ-ወጥ ግንባታዎችን የመከላከል ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ስራ አስፈፃሚው ያሳስባል። በመጨረሻም በአጠቃላይ የከተማው ነዋሪ ገንዘቡን ህገወጥ ተግባሮች ላይ ከማዋሉ አስቀድሞ እንዲጠነቀቅና ካልተፈለገ ኪሳራና ግጭት ራሱን እንዲከላከል በዚህ አጋጣሚ ፓርቲያችን ጥሪውን ያስተላልፋል። በድጋሚ በዚህ ግጭት ህይወት በመጥፋቱ ስራ አስፈፃሚው ከልብ ማዘኑን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
425 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 811 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us