በዘር ግንድ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ስርዓትና ችግሮቹ

Wednesday, 14 June 2017 12:53

 

ከአበባዉ መሐሪ

 

ኢትዮጵያ እየተከተለችዉ ያለዉን ፌደራሊዝም በተመለከተ ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፤ የተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የሲቪክ ማህበራት በተሳተፉበት ከፍተኛና ጠቃሚ ዉይይት ተካሒደል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ሰዶ ከማሳደድ ይልቅ እንደነዚህ ያሉ ስብሰባዎች እንዲዘጋጁ በማድረግ ከሚሰጡ አስተያይቶችና ምክሮች ትምህርት በመዉሰድ የአመራር እርምጃዉን ቢያዘምን በአገራችን ሰላም ይወርዳል፤ እራሱንም ከአደጋ ሊከላከል ይችላል የሚለ እሳቤ አለኝ፡፤


በሒልተን ሆቴል በተደረገዉ ስብሰባ ላይ ተገኝቸ ሦስት የፌደራሊዝም ምሁራን በኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ ያቀረቦቸዉን የጥናት ጽሁፎች በጥሞና ተከታትያለሁ። ከተሳታፊዎችም ሥር የወጉና መሰረታዊ የሆኑ አስተያይቶችና ጥያቄዎች ቀርበዋል። ምሁራኖቹ ያቀረቡት የጥናት ጽሁፍ የኢትዮጵያ ፌደራሊዘም ሰር~ል ወይስ ከሽòል፤ በዚህ ጉዳይ ላይስ ሕዝቡ ምን አስተያይት እየሰጠ ነዉ የሚሉትን ያካትታል ብዬ ጠብቄ የነበረ ቢሆንም የጠናቱ ጽሁፍ አንደነዚህ ያሉትን አንገብጋቢ ጉዳዮች ያካተተ አልነበረም፤ በጉዳዩ ላይ ሕዝቡስ ምን አስተያየት አለዉ የሚል እንè የተካተተበት አልነበረም።


እንደሚታወቀዉ ሁሉ በዓለም ላይ የተለያየ ቅርጽና ይዘት ያላቸዉ የፌደራሊዝም ዓይነቶች እንዳሉ ግልጽ ሲሆን በሁለቱ ዋና ዋና የፌደራሊዝም ዓይነቶች ላይ በተለያየ ጊዜና በተለያዩ ምሁራን ሰፊ ጥናት ተካሒዶባቸዋል። እነዚህ የፌደራሊዘም ዓይነቶችም፡-


1. በዘር ግንድና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዘም (Language and Ethnic based Federalism) ነዉ።
ይህ የፌደራሊዘም ዓይነት በብዙ ሀገራት ተግባራዊ ሆኖ ከጥቅሙ ይልቅ ችግሩ የሰፋ በመሆኑ የተነሳ አገሮቹ ወደማይወጡት ማጥ ዉስጥ ገብተዉ የሚገኙ ሲሆን በፌደራል መንግሥቱ ሥር የሚገኙ አካላት አንድም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ወይም እርስ በእርሳቸዉ በግጭት ዉስጥ ስለሚገቡ የሰባዊና ቁሳዊ ሀብታቸዉ በግጭቱ ይወድማል። በዚህ የተነሳም እድገታቸዉ ቀጭጮ፤ ዜጎቻቸዉ በድህነት አዘቅት ዉስጥ የሚማቅቁ ናቸዉ።


ይህን ዓይነት የፌደራሊዝም ሥርዓት ከሚከተሉ ሀገራት መካከልም፡- የቀደሞዋ ሶቤት ሕብርት፤ ዩጎዘላቢያ፤ በልጂየምና ኢትዮጵያ ይገኙበታል።
በዚህ ዓይነት የፌደራሊዝም ሥርዓት ዉስጥ የሚገኙ ሀገራት የአበዮታዊ ዲሞክራሲን መርህ ስለሚከተሉ ከግለሰብ መብት መከበር ይልቅ ለቡድን መብት መከበር ቅድሚያ ይሰጣሉ። የአገራችንን ሁኔታ እንደምሳሌ ብንወስድ በኢህአዴግ እምነትና መርህ መሠረት የአማራዉን መብት የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን)፤ የኦሮሞን የሰባዊ መብት ኦህዴድ፤ የትግሬዎችን መብት ሕወሓት ወዘተ. ያስከበራል በሚል ያምናል። ይሁን እንጂ እሰከአሁን ድረስ በአለን ተሞክሮ መሠረት እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች የየራሳቸዉን የፖለቲካ አባላት የፖለቲካ፤የኢኮኖሚና የማህበራዊ መብትና ጥቅም እንጂ የሚወክሉትን የአጠቃላይ ሕዝብ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ በቂ ጥረት ሲያደርጉ አልታዩም። በእንደነዚህ ዓይነቶች ችግሮች ምክንያት በአነዚህ አገሮች የሚታየዉ ያልተረጋጋ ፖለቲካ፤ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገትና ዝቅተኛ የአንድነት ስሜት፤ በአጠቃላይ የመበታተን እጣ ፋንታ (unstable politics, low economic development, less integrity and in general fragmentation) ይታይባቸዋል


2ኛ. ሁለተኛዉ የፌደራሊዝም ዓይነት ደግሞ በጂኦግራፊ፤ በኢኮኖሚና፤ በማህበራዊ ትስስር ላይ የተመሠረተ ነዉ/ That based on Geography, Economic and social ties)። ይህን ዓይነት የፌደራሊዝም ሥርዓት ከሚከተሉ ሀገራት መካከልም፡ ዩስ አሜሪካ፤ጀርመን፤ ብራዚል፤ ታላቋ ብሪታኒያ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካና ናይጀሪያ ይገኙበታል። እነዚህ ሀገራት የሊቨራል ዲሞከራሲን መርህ ስለሚከተሉ በመጀመሪያዉ ረድፍ ከተጠቀሱት በተቃራኒ ከቡድን መብት ይልቅ ለግል መብትና ጥቅም ቅድሚያ ስለሚሰጡ ሰላም፤ የተረጋጋ ፖለቲካና የኢኮኖሚ እድገትን የሚያጣጥሙ ከመሆናቸዉ በተጨማሪ አንድና ጠንካራ ሀገር ያላቸዉ ናቸዉ። ለምሳሌ ብራዚል ይህን ዓይነት የፖለቲካ መስመር በመከተላ ምክንያት ዛሬ ከድህነት ወጥታ ለዓለም ሀገራት የምግብና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቀረብና ፈጣን የሆነ ኢኮኖሚ በመገምባት ላይ ትገኛለች።


ከዚህ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበትና ሕዘባችን የተሳተፈበት ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ የትኛዉ ፌደራሊዝም ነዉ ለኢትዮጵያ የሚጠቅመዉ? የሚለዉ ነዉ። በአኔ አስተያየት የዜጎች ባህል፤ ቋንቋ፤ ማንነትና የሰባዊ መብት ተከብሮ፤ የማእከላዊ መንግሥትም የአካባቢ መስተዳድሮችን ሥልጣን ሳይሸራርፍ እንዲያከብር ሆኖ ፤ እንዲሁም የሊቨራል ዲሞክራሲ- መሠረቱ የአያንዳንዱ ዜጋ መብትና ድምጽ ተከብሮ የመንግሥት ሥልጣን ብቸኛዉ ባለቤት ሕዝብ መሆኑን መቀበል ነዉ። በዚሁም መሠረት የዜጎች ማለትም የግለሰቦች የመጻፍ፤ የመናገር፤የመደራጀት፤ መሪዉን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመምረጥና የመመረጥ፤የእምነት ነጻነት፤ ንብረት የማፍራት ነጻነትና የሌሎችንም የሲቪክና የፖቲካ ነጻነት ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ዋስትና መሥጠት ነዉ። ይህን የምልበት ምክንያትም ዛሬ የኢትዮጵያ ፈደራሊዝም የዜጎችን ከቦታ ቦታ ተዘዋዉሮ የመሥራት መብትን ገድቧል፤ በፌደራል መንግሥቱና በአንዳንድ ክልሎች መካከል እንዲሁም በየክልሎች መካከል የእርስ በእርስ ግጭትን በመፍጠር የዜጎች ሕይወትና የአገሪቱ ንብረት እንዲወድም አድረጓል እንዲሁም አገሪቱ የተረጋጋች እንዳትሆን ከፍተኛ ምክንያት ሆኖባታል።ለምሳሌ- በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶሚሌ፤ በኮንሶና በአሪ፤በጉጂና በቦረና እንዲሁም በአፋርና በአማራ …. መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭትን በመፍጠር ዜጎች በማይጠቅም ጉዳይ እንዲጋደሉና ብዙ ንብረትም እንዲወድም አድረጓል እያደረገም ይገኛል።በሌላ በኩል ዜጎች በአካባቢያቸዉ መዳኘትና ፍትህ ማግኘት ሲገባቸዉ የዘር ግንዳቸዉን በመቁጠር በዙ ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ለፍትህ ፍለጋ ሲነገላቱና ሲቸገሩ ይታያሉ። ለምሳሌ የምንጃር ወረዳ ሕዝብ በ20 ኪሎ ሜትር ከሚገኘዉ ከአዳማ ፍትህ ማግኘት ሲኖርበት የዘር ግንዱን ፈልጎ በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሚገኘዉ ባህርዳር ድረስ እንዲሔድ ያስገደደዉ ይህ ዓይነቱ ፌደራሊዝም መሆኑ ነዉ።


ስለዚህ የኢትዮጵያ አንድነትና መረጋጋት የሕዝበም እድገትና ብልጽግና ይሰምር ዘንድ ከላይ በተጠቀሱ የሊቨራል ዲሞክራሲ መርሆዎች ላይ በመመርኮዝ በዘር ግንድና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራለዝም ሳይሆን በጂኦገራፊ፤ በኢኮኖሚና በባህል ትስስር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ መተኪያ የሌለዉና ጠቃሚ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝባን ይባርክ

 

ፌደራሊዝም/Fedralis
1. በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ፌደራሊዝም አሉ/ There are two kinds of Fedralism.
1.1 አንደኛዉ በጂኦግራፊ፤ በኢኮኖሚና ፤ በማህበራዊ ትስስር ላይ የተመሠረተ/ That based on Geography, Economic and social ties:-


America, German, Brazil and UK and Nigeria
-Peace and Stable politics, Economic development, one and strong country


2. በዘርና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ/ That Ethnic and language based:


2.1. Russia, Ugozlavia, Ethiopia……


unstable politics, low economic development, less integrity and in general fragmentation


ከዚህ ላይ የትኛዉ ፌደራሊዝም ነዉ ለኢትዮጵያ የሚጠቅመዉ ይህ ነዉ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ
በአኔ አስተያየት የዜጎች ባህል፤ ቋንቋ፤ ማንነትና የሰባዊ መብት ተከብሮ እንዲሁም የማእከላዊ ምንግሥት የአካባቢ መስተዳድሮችን ሥልጣን ሳይሸራርፍ እንዲያከብር ሆኖ ፤ በአንደኛዉ ላይ እንደተጠቀሰዉ በኢኮኖሚ፤በጂኦገራፊና በባህል ትስስር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ነዉ ብየ አምናለሁ


ይህን የምልበት ምክንያት ዛሬ በዘር ግንድና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የኢትዮጵያ ፈደራሊዘም የዜጎችን ከቦታ ቦታ ተዘዋዉሮ የመሥራት መብት ገድቧል፤ክልሎች በግጭት ዉስጥ እንዲገቡ በማድረጉ የተነሳ አገሪቱ የተረጋጋች እንዳትሆን አድርጓታል፤


ለምሳሌ- በኦሮሚያና በሶሚሊያ፤ በኮንሶና በአሪ፤ በጉጂና በቦረና እንዲሁም በአፋርና በአማራ መካከል…. ከፍተኛ ግጭት በመፍጠር ዜጎች በማይጠቅም ነገር እንዲጋደሉና በዙ ንብረትም እንዲወድም አድረጓል።


የሊቨራል ዲሞክራሲ- መሠረቱ የአያንዳንዱ ዜጋ መብትና ድምጽ ተከብሮ የመንግሥት ሥልጣን ብቸኛዉ ባለቤት ሕዝብ መሆኑን መቀበል ነዉ። በዚሁም መሠረት የዜጎች ማለትም የግለሰቦች የመጻፍ፤ የመናገር፤የመደራጀት፤ መሪዉን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመምረጥና የመመረጥ፤ የእምነት ነጻነት፤ በየትኛዉም ክልል ንብረት የማፍራት ነጻነትና የሌሎችንም የሲቪክና የፖቲካ ነጻነት ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ዋስትና መሥጠት፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
465 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 92 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us