የወረቀት ላይ ነብረ-ህግ

Wednesday, 21 June 2017 14:00

 

በመሐሪ በየነ

 

በወሩ መጨረሻ የሚወጣው 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶቸ የብዙሃኑን ቀልብ ስቧል ቢባል የተጋነነ አያስብልም። መጠለያ ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ ፍላጎቶቸ አንደኛውናዋነኛው መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይሆንም። መጠለያ ማረፊያ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ መስተጋብር (social relations) የሚከናወንበት ተደርጎ መወሰዱ አያስደምም።

 

በዚህ ረገድ አዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶቸን በአራቱም አቅጣጫዎች በመገንባት የነዋሪውን የመጠለያ እጦት ለመቅረፍ "ሀ ብላ" ጉዞ ጅምራለቸ። እነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶቸ ከፍተኛ ወጪና ድካም የተገነቡ ሲሆን አስተዋፅአቸውም የትየለዩ ነው ማለት ይቻላል።
ማህበራዊ  ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳው የሚናቅ አይሆንም። በግለሰብ ደረጃም ቤተሰብ ለመመስረትና ትውልድ ለማፍራት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እሙን ነው። ከዚህ በተጓዳኝ ራስን ለመቻልና ለማስተዳደር ምቹ ኩነት ይፈጥራል።


በእነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶቸ የነዋሪውን ፍላጎት ለማሳካት በሚል እሳቤ የኮንዶምኒየሙን ህንፃ ታክከው ከትሟል። ሱቆች፣ የህንፃ መሣሪያ፣ መሸጫ መደብሮች፣ ቁንጅና ማስዋቢያ ማዕከላት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫዎቸ፣   ካፌና ሬስቶራንቶቸ፣ የባልትና ውጤት መሸጫ ሱቆች እንዲሁም አልኮል መጠጥ መሸጫ ኪዎስኮች ይገኛሉ።


በእነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶቸ በጎ ነገሮቸ እንደሚከናወኑ ሁሉ አስነዋሪና ጠያፍ የወንጀል ድርጊቶቸ የሚፈፀሙበት ቦታ እየሆነ እንደሚገኙ የአደባባይ ምስጢር ነው። ዝርፊያ፣ ስርቆት፣ ማጭበርበር፣  ቅጥፈትና ውንብድና እንዲሁም አደንዛዝ ዕፅና  ኢ -ግብረ ገባዊ ዝሙት ተጧጡፏል።
የነገሬ አብይ ጭብጥ የሚያነጣጥረው በእነዚህ መኖሪያ ቤቶቸ የሚገኙ የአልኮል መጠጥ መሸጫ ኪዎስኮቸ ይሆናል።


በነዚህ ኪዎስኮች አፍን በእጅ በአሉታዊ መልኩ የሚያስጭኑ ርኩስና ኢ- ሥነ ምግባራዊ ብሎም ባህላዊ ወጉን የሚጣረሱ ኩነቶቸ በመበራከታቸው ሰላማዊና ጤናማ ትውልድን ለማፍራት እሾኸና አሜኬላ በመሆን ማህበረሰቡ በስጋት፣ በሰቀቀንና በፍረሃት ኑሮውን እየገፉ ይገኛል።
በኪዎስኮቹ በተለይ ሲመሽ ለየቅልናየተዘበራረቀ አላማ ሸክፈው የሚመጡ ግለሰቦች ቤት  ይቁጠራቸው።


ቅጥ ባጣ አለባበስ ወንድም ሆነ ሴቶቸ በመሽቀርቀር የሚፈታተኑ ነዋሪዎቸና ፀጉረ ልውጦቸ ስፍር  ቁጥር የላቸውም። ገሚሱ የሌሎቹ ትኩረት ለመሳብ እንደተዋናይ የሚቅበጠበጥ ሞልቷል። 


ሌሎቹም ደግሞ ለቁሳዊና ለስሜት በሚል ሥነ- ልቦናዊ ብልጣብልጥነትን አጉረው ያነጣጠሩበትን ግለሰብ ትዳርም ያለው የሌለውም ሊሆን ይችላል  እመዳፋቸው ለማስገባት ከኪዎስኮቹ  ባለቤት     አስተናጋጅና አጎብዳቾች እንዲሁም ከሌሎች የመንግስት ሠራተኞቸ  ማለትም ፖሊስ  የወረዳ አመራር አካላትና ሰነድ በመቧጠጥ የተካኑ አንዳንድ የመንግስት ቅጥረኞቸና ደላላዎቸ ጋር በመመሳጠር ሴራ የሚጠነስሱ እንደአሽን ፈልቷል ተብሎ ቢነገር ያፈነገጠ ፅንሰ ሃሳብ አይሆንም።


አስጠያፊና የማንኛውም አካላት ትኩረት የተነፈገው ጉዳይ በኪዎስኮቹ በቤተሰቦቻቸው ግፊት የተነሣ ጡት ጠብተው ያልጨረሱ እንቦቅቅላ ህፃናት መገኘታቸው የህግ ያለህ ያስብላል። ህፃናቱ አይናቸውን በአንፀባራቂው የመብራት ጮራዎች ሲያዪ አንዳች የመርበትበት መንፈስ መላ አካላታቸውን በመውረር በለቅሶ ጩኹታቸውን ሲያሰሙ ይታያል።


የከረፋው የመጠጥ ሽታ እንኳን ለህፃናት ይቅርና ለአዋቂም ይሰነፍጣል። ቅጥ ያጣው የሙዚቃ ድምፅ የህፃናቱን ጆሮ ግንድ ሰርስሮ ገብቶ የወላጆቻቸውን ማባበያ ድምፅ ለመስማት ሲሳናቸው ይታያል። በሙዚቃው ተማርካ እስክስታዋን ያስነካቸው የህፃኑ እናት ሙዚቃው ሲያከትም ላብ ያጠመቀውን ገላዋን ለህፃኑ በማስተላለፍ እንግዳ ለሆነ ጠረን በመዳረጉ አንብቶ በአባቱ እቅፍ ለመውደቅ ይሳሳል።


"ለህፃናት ወተት እንጂ አጥንት አያሻውም። " የሚባለውን የህፃናት አስተዳደግ ህግ በመተላለፍ ወላጆቸ በስካር ጦዘው ለስላሳና ጮማ ሲግቱት ይስተዋላል።
በህጻት ላይ ወሲባዊ ድርጊት መፈፀምና መሰል ኢ ግብረ ገባዊና የህፃናትን መብት የሚጋፋና በሕግን የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት ነው። ወላጆችም የልጆቻቸውን ፍላጎት  ጤናና ማህበራዊ ዋስትና እንዲረጋገጡ በህግ በሚገባ ተደንግጓል። ከዚህሞ አልፎ  ተርፎ ማግኙት የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅምናምቹ የመጫወቻ ሜዳዎቸ እንዲዘጋቸላቸው በማድረግ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሯ ትኔዳለቸ የሚባለውን የነገ የሀገሪቷን ሁለተናዊ እምርታ በህፃናት ላይ ይጥላሉ።


በዚህ መነሾ "ንባብ ይገላል ትርጉም  ያድናል"   የተባለውን አነጋገር በመጋራት ሦስቱ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጪው  ፈፃሚውና ተርጓሚው በጋራ ከመንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ሲቪል ማህበራት ተፅዕኖ ፈጣሪ አካላት (pressure group) እና ብዙሃን መገናኛ በመቀናጅት ለህፃናት ህግ አፈፃፀምና አተገባበር ቀን ከለሊት መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
204 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 107 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us