በጩኸትና በጫጫታ ታሪክ አይቀለበስም፤ ሃቅም አይዳፈንም

Thursday, 13 July 2017 14:56

 

ከአራቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰጠ

ወቅታዊ መግለጫ

1.  የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር /ኦነአግ/

2.  የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ /ኦብኮ/

3.  የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር /ኦአነግ/

4.  የኦሮሞ ነፃነት ብሔራዊ ፓርቲ /ኦነብፓ/

ከበርካታ የዓለም ታሪኮች እንደምንረዳው ያለአግባብ የተገፉ ሕዝብ ተሸንፎ አያውቅም፣ ገፊውም አሸንፎ አያውቅም፡፡ ከዛሬ 130 ዓመት በፊት ዓፄ ምኒልክ የሸዋ ኦሮሞዎች አንጡራ ምድር የሆነችውን ፊንፊኔ በወራሪ ሠራዊቱ ሲቆጣጠር ኦሮሞዎቹ ፈጣሪ የፈጠረላቸውንና እትብታቸው የተቀበረበትን መሬት ከማጣት አልፎ በወራሪ በወራሪ ሠራዊቱ የኃይል ርምጃ ወደተለያዩ አካባቢዎች ማለትም ወደ አርሲ፣ ባሌ፣ ሐረርና ወደ ድሮ የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ተሰደዋል።

ዓፄ ምኒልክ የፊንፊኔ ምድርን የሰራዊቱና የመንግስቱ ዋና ማዕከል መሆኑን ከአረጋገጠ በኋላ የወረራ አድማሱን በማስፋት በተለይ በአርሲ ኦሮሞዎች፣ በሐረር ኦሮሞዎችና አደሬዎች ጨለንቆ ላይና በደቡብ በወላይታ ሕዝብ ላይ ያደረገው ጭፍጨፋ ምን ጊዜም በእነዚህ ህዝቦች ዘንድ የማይረሳ የታሪክ ጠባሳ ሆኖ ይኖራል።

ይህን አስከፊ ስርዓት ዛሬ ያሉት የትምክህት ኃይሎችና የሞተ ፈረስ ጋላቢዎች “እምዬ ምኒልክ ምን አጠፋ አገር አቀኑ እንጂ” እያሉ በስላቅ ቢነግሩንም በዚህ አባባላቸው ብቻ በእነርሱና በኦሮሞ ሕዝብ መካከል ዝንተ ዓለም እርቅ ሊመጣ አይችልም።

በዚህ ዓይነት አስከፊ ታሪክ ከኦሮሞ ሕዝበ የተነጠቀው የፊንፊኔ ምድር ዛሬ ስለኦሮሞ ሕዝብና ስለፊንፊኔ ታሪካዊ ትስስር በሰፊው ከመወራት አልፎ የኢህአዴግ መንግስት ለ25 ዓመት ሙሉ አፍኖ ያቆየውን የኦሮሞ ሕዝብ ከፊንፊኔ ያለውን ልዩ መብትና ጥቅም በሚመለከት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል ያሳወጀውን የይስሙላ አዋጅን መነሻ በማድረግ

እነዚህ ከፍ ሲል የጠቀስናቸው ታዳጊ የትምክህተኞች የልጅ ልጆች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፣ የህትመትና ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በጩኸትና በጫጫታ ምድር እያጠበቡ ይገኛሉ። እዚህ ላይ አንድ ነገር ብቻ ልናሳስባቸው እንወዳለን።

ይህም የሀሰት ጫጫታ ጩኸት ምን ያህል ቢበዛም ጠብታ እንጂ ባህር ሊሆኑ እንደማይችሉና እውነት ግን ጠብታም ብትሆን ባህር መሆኑ እንደማይቀር ነው። በመሆኑም ለሚከተሉት ወገኖች ሁሉ ቀጥሎ የተመለከተውን መልዕክት ለማስተላለፍ እንወዳለን።

1.  ለመላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፡- የኦሮሞ ህዝብ ያንተው አካልና አምሳል ነው። ከመሬት የወጣ፣ ከሰማይ የወረደም፣ ከውጪ የመጣ ወራሪ ሃይልም አይደለም። ካንተው ጋር በዚሁ ምድር ተፈጥሮ እንደሐረግ ዘርፍ ተሳስሮ የኖረ ሕዝብ ነው። ይህ ህዝብ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ምንም ቁርሾ የለውም። የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የራሱን መብትና በፊንፊኔ ላይ ያለውን ታሪካዊ ባለቤትነቱን መጠየቅ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግለሰብና ቡድን የሚጋፋ አይደለም።

የኦሮሞ ሕዝብና የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ በፊት ለዘመናት አብሮ እንደኖረ ሁሉ ወደፊትም ይቀጥላል፣ በቪዛ የሚገናኙ ሕዝቦች አይሆኑም፣ ዛሬ በገሃድ ያለው ሃቅ ሲረገጥ ግን ይዋል ይደር እንጂ ወደዚያው መግፋትም አይቀርም። እዚህ ላይ በተዛባ የገዢዎቻችን እይታና አካሄድ የተነሳ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ሁኔታ ማስታወሱ ይበቃል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የኦሮሞ ሕዝብ ከአንተ ጋር ያለው ታሪካዊ ትስስርና የአብሮነት ኑሮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከኦሮሞ ሕዝብ የመብት ጥያቄ ጎን በሐቀኝነት እንድትቆምና ድጋፍ እንድትሰጥ ጥሪአችንን እናቀርባለን።

2.  ለኢህአዴግ መንግስት፡- ከረጅሙ የዓለም ታሪክ እንደምንማረው መሪዎችና መንግስታት ዘለዓለማዊም አይደሉም። ታሪኩንም የመጎተት ወይም የማፋጠን ተፅእኖ ይኖራቸዋል እንጂ የመቀልበስ ሐይል የላቸውም። ኢህአዴግና የኢህአዴግ መንግስት ሌሎችም የፖለቲካ ኃይሎች ያልፋሉ፣ የኦሮሞ ሕዝብና የተቀረው የኢትዮጵያሕዝብ ግን ለዘለዓለም ይኖራሉ። በመሆኑም የኢህአዴግ መንግስት ምንም አዲስ ነገር በሌለበት አዋጅ ምድር ማጣበቡን በመተው የኦሮሞ ሕዝብ የጠየቀውን የፊንፊኔን የባለቤትነት  ጥያቄን የኦሮሞን ሕዝብ ብቻም ሳይሆን የተቀሩትንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ማሳመን በሚችል መልኩ እንዲያስተናግድ ጥሪአችንን እናቀርባለን።

3.  ለትምክህተኛ ኃይሎች፡- የመሰላችሁን ሃሳብ በሚመቻችሁ መንገድ የማቅረብ መብት እንዳላችሁ ብንረዳም ታሪክ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ እንደማይሄድ ተረድታችሁ የታሪክ ጭራ እንዳትሆኑ። እሩቅ ሳትሄዱ የአባቶቻችሁንና የእናቶቻችሁን ታሪክ በደንብ አጥኑ። ዛሬ መጥፎ ታሪካቸውን እንጂ ጥሩ ታሪካቸውን እያስታወስን አይደለም። እስቲ እራሳችሁን ጠይቁ የአፄ ምኒልክና የኃይለ ስላሴ እንዲሁም የመንግስቱ ታሪካቸው የት ነው ያለው ዛሬ? የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ እያደረገው ነው ወይስ እያለያየው ነው?

ወደዳችሁም ጠላችሁም ዛሬ ኢትዮጵያን ህዝብ እያመሰ ያለው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አይደለም። በኢህአዴግ ስርዓት የተፈጠረው ፌዴራሊዝምም አይደለም። አባቶቻችሁና እናቶቻችሁ በእብሪተኛና ትምክህተኛ ጭንቅላታቸው በቀበሩት ፈንጂ ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ እያመሰ ያለው ታሪክ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አይሄድም። የታሪክን እውነታ በኃይልና በጩኸት ጋጋታ የቀለበሰ ማንም ኃይል የለም። ፈጣሪ ልቦና ሰጥቶአችሁ ሕዝብና ሕዝብን ከማጋጨት አእምሮአችሁን ከውሸት ተሪክ ጥንተና ነፃ ያድርግላችሁ እንላለን።

4.  ለኦሮሞ ሕዝብ፡- ከዛሬ 130 ዓመት በፊት በአፄ ምኒልክ ወራሪ ሰራዊት ማንነትህ ተደፍሮ አገርህን ከተቀማህ በኋላ በዚህ አገር ውስጥ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረህ እየኖርክ ቢሆንም ያጣኸውን መብትህንና ማንነትህን በጨዋነት በሰላማዊ መንገድ ከመጠየቅ ውጪ አንድም አብረህ የምትኖረውን የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረትና ሕይወት የሚጎዳ ተግባር ፈፅመህ አታውቅም። ይህ የሚያመለክተው የተፈጥሮ ጨዋነትህንና አርቆ አስተዋይነትህን ነው። በዚህ በቅርብ ዘመናት እንኳን የፊንፊኔን ባለቤትነት መብትህንና ሌሎችንም መብቶች ጨምረህ ጥያቄን በሰላማዊ መንገድ ስታቀርብ ቆይተሃል። በዚህም የተነሳ ብዙ ውድ ልጆችህም ተሰውተዋል። አንተ ግን እየሞትክ ከመታገል ውጭ የወሰድከው መጥፎ የኃይል እርምጃ የለም። ስለሆነም አሁንም እንደዚህ በፊት ሁሉ የፊንፊኔ የባለቤትነት ጥያቄና ሌሎችም ጥያቄዎች በተገቢ መንገድ እስከሚመለሱ ድረስ ጥያቄህን በሰላምና በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንድታቀርብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያለህን ሰላማዊ ግንኙነት አጠንክረህ እንድትቀጥል እንጠይቃለን።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!!!

ሐምሌ 2009

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
241 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1056 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us