ሳይታመሙ ማርጀት

Wednesday, 27 December 2017 12:24

 

በማዕረጉ በዛብህ

 

የአሜሪካ ሳይንቲስቶች በርጅና የሚመጡትን እንደ ካርድዮቫስኩላር የተባለውን (የልብና የደም ማዘዋወሪያ ቧንቧዎችን የማጥበብ ችግር) እንዲሁም ካንሰርንና አልዛይመር የተባለውን የመርሳት በሽታ ጨምሮ የማጥቃት ፍጥነታቸውን ለመቀነስ ወይም ለማዘግየት መድሐኒት ለማግኘት በመሞከር ላይ እንደሆኑ ዎል ስትሪት ጀርናል በተባለው የአሜሪካ ዕለታዊ ጋዜጣ በጤንነትና በደህንነት አምድ በወጣ ጋዜጣዊ ዘገባ ተገልጿል።

 

ሱማቲ ረዲ (Sumati Reddy) የተባሉ የዘገባው አቅራቢ እንደገለጹት ይህ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች “ሳይታመሙ ማርጀት” በሚል አጠራር የሚያደርጉት ጥናት ከሰው ልጅ ዕውቀት አቅም የራቀ ቢመስልም ሳይንቲስቶቹ ግን በእርጅና ምክንያት የሚመጡትን በሽታዎች ጥቃት ለመቀነስ ወይም ለማዘግየትና ሰው በነኚህ በሽታዎች ሳይጠቃ (እድሜ ለማራዘም ሳይሆን እሱም ሊሆን ይችላል) ከዕድሜው የመጨረሻዎቹን 10 ዓመታት ያለበሽታ ኑሮ እንዲሞት የሚያደርግ መድሐኒትን ለማግኘት በሳይንሳዊ ቤተ ፍተሻ (ላብራቶሪ) ክልኒክ ለመሞከር ጥረት እያደረጉ  ናቸው ሲሉ ያስረዳሉ።

 

ይህ የምርምር ሥራ በእንስሳት ላይ በላብራቶሪ ተሞክሮ እንደታየው ውጤታማ የሆኑ የእርጅናን ችግሮች ለመቀነስ የሚያስችሉ ከግማሽ ደርዘን ያላነሱ ወይም ከዚያ የበለጡ መድሐኒቶች በሰው ላይ ቢሞከሩ ውጤታቸው ምን ያህል ስኬታማ ይሆናል የሚለውን ረጅም ጊዜ የፈጀውን የምርምር ስራ አንድ ምዕራፍ ላይ ለማድረስ የታቀደ ነው። እስካሁን በተገኘው ውጤት መሠረት ጥቂቶቹ መድሐኒቶች በእርጅና ምክንያት የሚመጡትን ጨርሶ ሊፈወሱ የማይችሉት (chronic) በሽታዎች የሚያስከትሉትን ጥቃት መጠንና የአመጣጣቸውን ፍጥነት ለመቀነስ እንደሚያስችሉ ለማወቅ ተችሏል ይላሉ ዘጋቢው ረዲ።

 

የልብ በሽታ፣ ካንሰር፣ የስኳር በሽታ (ዲያቢትስ) እና አልዛይመር የተባሉት ሁሉ በእርጅና ምክንያት ብዙውን ጊዜ የሚከሰቱ ዋናዎቹ አደገኛ በሽታዎች መሆናቸውን በኒውዮርክ ሲቲ በሚገኘው የአልበርት አይንስታይን የህክምና ኮሌጅ ውስጥ የእርጅና ጥናት ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትና ስለ እርጅና ለማጥናት እየተካሄደ ያለውን ፕሮጀክት የሚመሩት ዶ/ር ኒር ባርዚላይ (Barzilai) ያስረዳሉ።

 

“እርጅናን ለመቆጣጠር እርጅናን አደገኛ የሚያደርጉትን ሁኔታዎች መከታተል ማለት ከላይ የተጠቃቀሱትን የእርጅና በሽታዎች ማጥናትና መመራመር በጣም አስፈላጊ ነው” ይላሉ ዶ/ር ባርዚላይ።

ይህን የእርጅና ጥናት ፕሮጀክት ወደ ተሳካ የጥናትና ምርምር ውጤት ደረጃ ለማድረስ በክሊኒክ ውስጥ ለሚደረግ ጥናትና ክትትል 1000 በሽምግልና ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት ለሚፈጅ ጊዜ በብዙ የጥናት ማዕከሎች ተገኝተው የጥናቱ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ ዶ/ር ባርዚላይ። የጥናቱ ፕሮጀክት አሁን በአፍላ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሥራውን በዘለቄታ ለማካሄድ የሚያስችለው የገንዘብ ምደባ/ ባጀት አልተደረገለትም። እስካሁን ለተሠራው የጥናት ዕቅድና ምርምር ሥራ ገንዘብ የተገኘው ከአሜሪካ የእርጅና ጥናትና ምርምር ፌዴሬሽን ሲሆን ዶ/ር ባርዚላይ የፌዴሬሽኑ ሳይንሳዊ ዘርፍ ምክትል ዲሬክተር ናቸው።

 

ሊደረጉ ከታሰቡት የጥናትና ምርምር የቅድሚያ ሥራዎች አንዱ ሆኖ የታቀደው ሜትፎርሚን (Metformin) የተባለው ለሁለተኛ ደረጃ የስኳር በሽታ/ዲያቤቲክስ የሚሰጠው መድሐኒት ሌሎችን በሕክምና ሊድኑ የማይችሉ/chronic በእርጅና  ምክንያት የሚከሰቱ በሽታዎችን ለማዘግየት ወይም ጨርሶ ለመከላከል ያስችል እንደሆነ ለመሞከር ነው። ስለሆነም የፕሮጀክቱ ስም በእርጅና ላይ በሜትፎርሚን ማተኮርና መግራት/Targeting/ Taming Aging with Metforming (TAME) ነው። ሜትፎርሚን ከሌሎች ዕድሜን ለማራዘምና በእርጅና ምክንያት የሚከሰቱትን የማይድኑ (Chronic) በሽታዎች አደጋ ለመቀነስ እንደሚያስችሉ ተስፋ እየታየባቸው ካሉት መድሐኒቶች ሁሉ የተሻለ ውጤት በማሳየቱ ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ መነሻ ሆኖ የተመረጠው ይህ መድሐኒት በጥቅም ላይ ከዋለ ከ60 ዓመት በላይ ከመሆኑም በላይ የጎንዮሽ ችግሮች (Side effect) የማያመጣና ዋጋውም ቀላል ስለሆነ ነው። TAME በሚገባ የታቀደና የተዘጋጀ ሰፊ ጥናትና ምርምር ፕሮጀክት ከሆነ የአሜሪካ የምግብና የመድሐኒት ባለሥልጣን መስሪያ ቤት የእርጅና ህመሞችን በመድሐኒት አማካይነት ማስወገድ አለዚያም ማዘግየት የሚቻል መሆኑን መቀበል ሊኖርበት ነው። መድሐኒት አምራቾችም ይህን ዕውነት ከግንዛቤ በማስገባት እርጅናን የሚያባብሱ መድሐኒቶችን እንዳያመርቱ መጠንቀቅ ሊያስፈልግ ነው። በዚህ ሳይታመሙ ማርጀት በሚለው ርዕስ በቀረበው ሳይንሳዊ ዘገባ የሚከተሉት የጥናት ውጤቶች ተጠቅሰዋል።

·  በአሜሪካ የወንዶች አማካይ የመጨረሻ ዕድሜ (አ.የ.ዕ) 76 ዓመት ሲሆን የሴቶች አማካይ የመጨረሻ ዕድሜ ግን 81 እንደሆነ በተደረገ ጥናት ሊታወቅ ተችሏል። ሌላው ከጥናቱ የተገኘው ዕውቀት የካንሰር በሽተኛውን ሳይገድል በ3 ዓመት ተኩል ማዘግየት ከተቻለ የበሽተኛው እድሜ ሊራዘም እንደሚችልና እንዲሁም የስኳር በሽተኛን በ4 ዓመት ተኩል ማዘግየት ከተቻለ ጠቅላላ ዕድሜውን ማራዘም እንደሚቻል ነው። በተጨማሪም በእርጅና ምክንያት የሚመጡትን ሁሉን በሽታዎች ማለት የልብ ሕመም፣ ካንሰር፣ እስትሮክና የስኳር በሽታን መቆጣጠር ከተቻለ የበሽተኛው ዕድሜ ከ10-15 ዓመት ሊራዘም እንደሚችል ጥናቱ ያመለክታል።

ዶ/ር አሊሸያ አርባጀ የተባሉ በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እርጅናን በተመለከተ ምርምር የሚያደርጉ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ከላይ በተደረገው ጥናት መሠረት በእርጅና የሚመጡትን በሽታዎች የሚያደርሱትን ጉዳት ትንሽ ለመቀነስ የሚደረገው ጥናት ጠቃሚነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በእርጅና ምክንያት የሚደርሱትን ጉዳቶች ለመቀነሰ ወይም ለመዘግየት የሚረዱ ዘዴዎች እንዳሉ ማወቅ ተችሏል። እነርሱም የተመጣጠነ አመጋገብ፣ የማህበራዊ ሕይወትን እንቅስቃሴ ማሳደግ፣ ጭንቀት የሚያመጡ ሁኔታዎችን መቀነስና በቂና ምቹ እንቅልፍ ማግኘት ናቸው።

·  የዘገባው አቅራቢ ሱማቲ ሬዲ (Sumathi Reddy)

·  ትርጉም፡- ማዕረጉ በዛብህ፤

·  ምንጭ፡- ዘዎል ስትሪት ጀርናል THE WALL STREET JOURNAL የጤንነትና ደህንነት አምድ፣ March 17/ 2015

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
101 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 89 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us