“ሁሉን አቀፍ ውይይትና ድርድር ተካሂዶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በሀገራችን በአስቸኳይ ተግባራዊ ይደረግ!”

Wednesday, 14 February 2018 12:05

 


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ባለፈው 26 ዓመታት በሀገራችን የተንሰራፋው የግፍ አገዛዝ ጉልበታችንን አዝሎ፣ ትከሻችንን አጉብጦ ሊጥለን ቢሞክርም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተደረገና እየተደረገ ባለ የነቃ ተሳትፎ የገዢው ብድን ክፉ ምኞት ቅዠት መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ገዢው ቡድን በየቀኑ የሚያደርሱብንን ግፍ እና በደል ከፊት ለፊታችን እንደሻማ እየቀለጡ ጥንካሬያችንን በህመማቸው ለገነቡልን፣ የሥርዓቱን ቅጥ ያጣ አረመኔያዊ ተግባር በአደባባይ ማንም ሳያስገድዳቸው፣ የወገኔ በደል ሊቆም ይገባል በማለት የተጋፈጡ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች የለኮሱት ሻማ የህዝብን ትግል ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ጥግ አነቃንቆ ገዢው ቡድን የሕዝብን ትግል ሊያዳፍኑት ወደማይችሉት፣ ሞክረው ወደማይሳካላቸው ምዕራፍ ተሸጋግሯል‹‹ ሕዝባዊ ትግሉ እየተጋጋመ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያም ወደማይቀረው የለውጥ ጎዳና እየተመመች ትገኛለች።


የሕዝብን አንገት ለማስደፋትና ሕዝባዊ ትግሉን ለመቀየር ያልተማሰ ጉድጓድ፣ ያልተወጣ አቀበት፣ ያልተወረደ ቁልቁለት ባይኖርም ትግሉ ከቀን ወደ ቀን አቅጣጫውን እየቀየረና እየጠነከረ በመምጣቱ የሕዝብን ትግል ፍሬ አፍርቶ፣ የአገዛዙን ሥርዓት እያስጨነቀ፣ ድል የሕዝብ መሆኑ እያረጋገጠ ይገኛል። ሰማያዊ ፓርቲም ይህን የመሰለ በታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን፣ በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ሃገር የሚገኙ የኢትዮጵያውያንን ትግል በእጅጉ ያደንቃል! ከዚህ ቀደም እንደነበረው ወደፊትም በተጠናከረ መልኩ የሕዝብን ትግል በማገዝ ተገቢውን ኃላፊነት ይወጣል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ከደረሰበት ሁለንተናዊ ጫና በመነሳት፣ “የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና መሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦችን ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ከእስር እንደሚፈቱ” ለሕዝብ ቃል መግባቱ የሚታወስ ነው። በይፋ ለሕዝብ የገባውን ቃል ተግባራዊ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቅበት ወቅት፣ አስቀድሞ ያልተገለጸ “በይቅርታ” ወይም የይቅርታ ፎርም/ማመልከቻ ላይ ፈርሙ መባላቸውና ይህንን ፈርማችሁ ካላስገባችሁ ከእስር አልፈታችሁም የሚል አጓጉል ፈሊጥ በማምጣት ቀድሞ የገባውን ቃል በማጠፍ በአደባባይ እየካደ ይገኛል። ክህደት የሥርዓቱ ዋነኛ መገለጫ ባህሪይ መሆኑን በደንብ እንገነዘባለን። አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገዛዙን ክህደት የመሸከም ፍላጎቱ ባበቃበት በዚህ ወሳኝ ወቅት በሕዝብ ላይ ክህደት በመፈፀም የህወሃት መራሹ ገዢው ቡድን የማይወጣው አረንቋ ውስጥ የሚከተው እንጂ ከቶውንም የሚያድነው አይደለም!
በመሆኑም የአገዛዙ ሥርዓት ቀድሞ ለሕዝብ የገባውን ቃል መፈፀሙ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተሸለ ሀገራዊ መግባባትና የተረጋጋ ሰላማዊ የፖለቲካ ሥርዓት በሀገራችን እውን እንዲሆን ከሚያግዙ ነገሮች ውስጥ አንዱ የህሊና እስረኞችን መፍታት ነው። ስለሆነም እነ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ከገዢው ስርዓት በአመለካከት በመለየታቸው ብቻ በግፍ ለእስር የተዳረጉ፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና አባላት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም የእምነት አባቶች በሙሉ ከእስር ተፈተው ሁሉን አቀፍ ውይይትና ድርድር ተካሂዶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በሀገራችን በአስቸኳይ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ ሰማያዊ ፓርቲ በፅኑ ያምናል።


ሰማያዊ ፓርቲ የሕዝቡን ትግል ግንባር ቀደም በመሆን ሲመሩ የቆዩት ጀግኖች! መራራ ፅዋ ተቋቁመው ወደ ህዝብ በመቀላቀላቸው፣ ሕዝብ ትግሉን አይመለከተኝም ወይም ሌላ ምክንያት ሳያቀርብ በፅናት ትግሎ መሪዎችን በማስፈታቱ፣ ህዝቡንና መሪዎችን በማገናኘት ሁለቱም በጋራ ምስጋና የሚሰጣጡበትን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ከታሳሪ ቤተሰቦች፣ ከታዋቂ ግለሰቦች፣ ከምሁራንና ከጠበቆቻቸው ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ ሲሆን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለስኬታማነቱ አስፈላጊውን ትብብራችሁን እንደቀድሞው ሁሉ አሁንም በማድረግ ከእስራት እንደተፈቱ በነቂስ በመውጣት በተለያየ መልኩ በፓርቲው በሚዘጋጁ መድረኮች ላይ በመገኘት መሪዎቹን እንዲቀበል ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል።


በመጨረሻ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዴሞክራሲ፣ የፍትህና የነፃነት ጥያቄ ዋነኛ ትያቄ መሆኑን መሠረት በማድረግ እነዚህ ጥያቄዎችን በሚመለሱበት ደረጃ ሰማያዊ ፓርቲ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የሕዝቡ ትግል ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት ይገልፃል።
“ኢትዮጵያ በነፃነትና በክብር ለዘላለም ትኑር!”
የካቲት 05-2010 ዓ.ም አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
87 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 439 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us