የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር መግለጫ

Wednesday, 27 June 2018 13:12

 

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይለይ ኢትዮጵያውያን ተከባብረውና ተሳስበው እንዲኖሩ ምኞቱ ብቻ ሳይሆን የምንግዜውም ጥረቱ ነው።

-  ማኅበራችን አንቱ የተባሉ፤ ለሰላም የታገሉና የሚታገሉ በርካታ ደራስያንን ያፈራ ሲሆን ዛሬም ሆነ ወደፊት ለመላው ሀገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ጠንክሮ ይሰራል።

-  ድርሰት ድንበር የለውም፤ ጤናማ አዕምሮንም ሰው ሰራሽ ወሰን አይገድበውም።

-  ቀደምት ደራሲያን አባቶቻችን ለህዝብ እና ለሃገር ሲታገሉ፣ ለሕዝቦች መብት፣ ነጻነት፣ እኩልነትና ሰላም ሲተጉ መስዋዕትነት ከፍለዋል።

- ዛሬም ማኅበራችን ሰላምን፣ ልማትን፣ ዴሞክራሲንና ፍትህን አጥብቆ ይሻል፤ ይህንንም ባለአዕምሮ ብሩህ ደራስያን ሁሉ በሥራዎቻችን ትኩረት ሰጥተን የምንሠራበት የዘወትር ተግባራችን ነው።

-  ከጥቂት ዓመታት ወዲህ እንኳንስ የመሬት፣ የሃይማኖት ድንበር ተበጅቶ ተመልክተናል፤ የአንድ ሃይማኖት አባቶች ምዕመናን ሲጣሉ በማስታረቅ ፋንታ እነሱው የጠብ ምንጭና ዋና ተዋናይ የሆኑት፤ አንድ የሚያደርጉን ሳይሆን የሚለያዩን ሰበቦች የበዙበት፤ የንግድ ተቋማት ሳይቀሩ ወደ መንደር የወረዱበት፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምርና የዕውቀት ማዕከላት መሆናቸው ቀርቶ ወደ ዕልቂት ጎሬነት ከተቀየሩበት ዘመን ላይ ደርሰናል።

በተለይ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ላይ ስደተኛ የሆኑበትን ምክንያት ስናስብ በሃፍረት አንገታችንን እንደፋለን።

- እንጀራ ፍለጋ ሄደው፣ ወደ ቤተሰባቸው የሚመለሱበትን ቀን ናፍቀው የነበሩ ወጣቶች በሕዝብና ካሜራ ፊት አንገታቸው በሰይፍ ሲቀላ፣ እጅ እግራቸው ታስሮ ጭንቅላታቸውን በጥይት የተደበደቢቡበትን አጋጣሚ በፍጹም ልንረሳው አንችልም።

ጎማ በአንገታቸው ላይ ታስሮ በቁማቸው እሣት የበላቸውን ወገኖቻችንንም በፍጹም መቼም መዘንታት አንችልም።

- በሰበብ አስባቡ በየከርቼሌው እየታጎሩ ይሰቃዩ የነበሩ ዜጎች ህመም ህመማቸው ሆኖ የሰላም ፍቅርና መግባባት ብቸኛ መፍትሄ መሆኑን ያመኑት የወቅቱ የሀገራችን መሪዎች የጀመሩት ጥረት እጅግ የሚያጓጓ ፍሬ ማፍራት ጀምሮ ነበር።

ይህን የሚያጓጓ ጥረት ለመደገፍ በወጣው ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የተፈጸመው ድርጊት በእጅጉ አሳዝኖናል።

በተለይ

- በጠቅላይ ሚኒስትሩ

- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ

- በሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና በሰላም ፈላጊው ሕዝብ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራና ግድያ ሕገወጥ የሀገሪቱን ተስፋ የሚያጨልም ስለሆነ ባጽንዖት እናወግዛለን። መገረፍን፣ መግፈፍና ዜጎችን በሀገራቸው ላይ ስደተኛ እንዲሆኑ የሚያደርግ አሠራርን፣ አመራርን በጥብቅ እንቃወማለን።

- በተለያየ ምክንያት በሀገራቸው መኖር አቅቷቸው ለስደት የተዳረጉ ሁሉ ወደ ሀገራቸው እንዲገቡና በሰላም እንዲኖሩ የተጀመረውን ጥረት እንደግፋለን።¾   

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
56 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 974 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us