ከኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ /ኮንግረስ/ የተሰጠ መግለጫ

Wednesday, 27 June 2018 13:15

 

ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 40 ዓመታት ባልተቋረጠ ሁኔታ አንዳንዴ በውጪ፣ ሌላ ጊዜ በውስጥ ጦርነት፣ እንደዚሁም በዜጎች፣ በብሔር ብሔረሰቦች የእርስ በርስ ፀብና ግጭት ስትታመስ ሰላም አጥታ ኖራለች። በዚህ ወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት በተጠጋ ጊዜ ውስጥ በነበረው ጦርነት፣ ፀብና ግጭት እና ይህን ተከትሎ በሚመጣ መፈናቀል፣ ስደት፣ ርሃብ፣ በሽታ፣ ግድያና ሞት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሲቃይና መከራ ሲዳረጉ ቆይተዋል። በዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት ኢትዮጵያ ሰላሟ ጠፍቶ፣ አንድነቷ ተናግቶ፣ በውስጧ በነበረው ሀገራዊና ሕዝባዊነት አቋም፣ አስተሳሰብ፣ እምነትና ተስፋ ከስሞና በኖ አስፈሪ የሆነ የውድቀት አፋፍና የመበታተን ጫፍ ላይ ደርሳ ነበር።

በዚህ በመላው የሀገሪቱ ክፍል ሲከሰት በኖረው ችግር ምክንያት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና አንድነት ርቆት፣ በመላው ሀገሪቱ ጥላቻና በቀል ነግሶ ግጭት፣ በመፈናቀል፣ መሰደድ፣ ግድያና ሞት የዘወትር ተግባር ወደ መሆን ደረጃ ደርሷል። ይህ ብቻ ሳይሆን በቀጣይም በሀገሪቱና በሕዝቡ መሀከል ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር እንዳይኖር የሚያደርግ የበቀልና የጥላቻ ዘር ተዘርቶ እልቂትና ፍጅት እየተሰደደ የነበረበት ደረጃ ደርሶ ነበር።

ይህን በኢትዮጵያና በህዝቡ ላይ የደረሰውንና ማቆሚያ ያጣውን ችግር በኃይልና በጉልበት መንገድ ሳይሆን በመግባባት፣ በመቻቻል፣ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት መንገድ እንመልስ፣ ሰላም ፍቅርና አንድነትን በጋራ እናወድስ፣ እንዘምር የሚል አመራርና መሪ ማግኘትና ማየት በራሱ ለሀገሪቱም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማይጨበጥ ህልም ሆኖ ነበር። ይህ ህልም ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ አደባባይ በመውጣት ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን እንዲያወድስና እንዲዘምር ያደረገው። በዚህ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን በማወደስና በመዘመር ወደ አደባባይ በወጣው ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ያልታሰበና ያልተጠበቀ ጥቃት ተፈፅሟል። ድርጊቱ በየትኛውም መመዘኛና መስፈርት ፍፁም አረመኔያዊና እኩይ የሆነ የጭካኔ ድርጊት ነው። ስለሆነም፡-

1.  የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ (ኮንግረስ) ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን በማወደስና በመዘመር የተሰለፈው ሰላማዊ ሕዝብ ላይ አረመኔያዊ የጭካኔ ተግባር የፈፀሙ ክፍሎችንና ድርጊታቸውን በጥብቅ ያወግዛል።

2.  በዚህ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ በደረሰው ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፣ ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት እንዲያኖር፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመድ ወገኖቻቸው መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

3.  በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ከባድና ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ፈጣሪ ምህረትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

4.  ይህንን እኩይና አረመኔያዊ ድርጊት የፈፀሙ ወንጀለኞች መንግስት ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ (ኮንግረስ) ጽ/ቤት

      ሰኔ 17 ቀን 2010 ዓ.ም

            አዲስ አበባ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
51 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1018 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us