ኢትዮጵያ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ትወዳደራለች

Thursday, 01 December 2016 15:30

የአፍሪካ ዋንጫ መስራች ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ በ2025 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት እንደምትወዳደር አስታውቃለች። ውድድሩን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ላይ መገኘቷ የተሻለ ግምት እንዲሰጣት አስችሏል።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.አ.አ. በ1972 ለመጨረሻ ጊዜ ያስተናገችው ኢትዮጵያ ከስምንት ዓመት በኋላ የአህጉሪቱን ትልቁን የእግር ኳስ ውድድር ለማዘጋጀት እንደምትወዳደር አስታውቃለች። ውድድሩን ለማዘጋጀትም የእግር ኳስ ወዳዱ ህዝብና መንግስታት ሙሉ ድጋፍ እንደሚፈልጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የስታዲየም ግንባታዎች በተለያዩ ከተሞች እየተከናወኑ ሲሆን፣ በቅርቡ የተጠናቀቁና በቀጣይ ዓመታትም የሚጠናቀቁ ስታዲየሞች የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት የሚያስችላት ይሆናል። ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የቻሉት የባህር ዳር፣ የሐዋሳ፣ የድሬደዋ ስታዲየሞችን ጨምሮ የመቀሌ፣ የነቀምት፣ የወልዲያ ስታዲየሞች ከአዲስ አበባ ስታዲየም ጋር የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ የሚያስችሉ ናቸው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
323 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us