በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ ተገምታለች

Thursday, 01 December 2016 15:32

 

በካሜሮን አስተናጋጅነት እየተካሔደ የሚገኘው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ናይጄሪያ በፍጻሜ ጨዋታው ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት አግኝታለች። በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከናይጄሪያና ካሜሮን በተጨማሪ ጋናና ደቡብ አፍሪካ ያልተጠበቀ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ስምንት ሀገሮችን የሚያሳትፈው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ በካሜሮን እየተካሔደ ይገኛል። ናይጄሪያ፣ ካሜሮን፣ ጋናና ደቡብ አፍሪካ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በአህጉሪቱ የሴቶች እግር ኳስ ሀያልነቷን ያረጋገጠችው ናይጄሪያ ዘንድሮም ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷታል።

በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታው ናይጄሪያ እና ካሜሮን ተጋጣሚያቸው ጋናና ደቡብ አፍሪካን ማሸነፍ ከቻሉ ለፍጻሜ የሚቀርቡ ሲሆን፣ በፍጻሜውም ናይጄሪያ ዋንጫ የምትጠበቅ ሀገር ሆናለች። ጋናና ደቡብ አፍሪካም ለዋንጫ ለማለፍ መዘጋጀታቸውን ነው ያስታወቁት። ጋና ከአስተናጋጇ ሀገር ከካሜሮን የሚያደርጉት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚስተዋልበት ይጠበቃል። ናይጄሪያ ደቡብ አፍሪካን በቀላሉ በማሸነፍ ወደ ፍጻሜ እንደምታልፍ ተገምቷል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳና ሊዲያ ታፈሰ ከኢትዮጵያ የተመረጠች ብቸኛ ዳኛ ናት።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
271 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us