ኢትዮጵያዊው በዓለም የጁዶ ውድድር አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

Wednesday, 07 December 2016 15:41

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የወድድር መድረኮች በማትታወቅበትና ውጤትም አስመዝግባ በማትጠራበት አለም አቀፍ የጁዶ ስፖርት ወጣቱ ያሬድ ንጉሴ አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ ችሏል። የጁዶ ተወዳዳሪው ያሬድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም የመጀመሪያ የተባለ ውጤት አስመዝግቧል።

የአለም ጁጂትሱ ውድድር በፖላንድ ሮክላው ከተማ የተካሔደ ሲሆን፤ በ56 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ያሬድ ንጉሴ ለግማሽ ፍጻሜ መድረስ ችሏል። ይህ የያሬድ ውጤት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካም ትልቅ የሚባል ነው።

ያሬድ የብራዚል የጁዶ ስፖርት አይነት በመባል በሚታወቀው ኔዋዛ የውድድር አይነት ተጫውቶ በመጀመሪያው ዙር የተሰናበተ ቢሆንም የኮሎምቢያ ጁዶ በሆነው በጄይሰንሞራፒኔዳ ደግሞ ጀርመናዊውን ተጋጣሚውን በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፍ ችሏል።

ያሬድ በማሽፍ ጻሜ ውድድር መድረስ የቻለበት ውጤት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም የመጀመሪያ አድርጎታል። በግምሽ ፍጻሜውም በውድድሩ መሀል በሰራው ጥፋት ቅጣት ተጥሎበት ውጤቱ በመሰረዙ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ሳይችል ቀረ እንጂ ለፍጻሜ በመድረስም የውጤት ታሪኩን ከፍ የሚያደርግበት እድል ነበረው።

ያሬድ በአለም የጁጂትሱ ሻምፒዮናው ያስመዘገበው ውጤት በአለም ላይ አምስተኛ ደረጃ ላይ ያሰቀመጠው ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ ቁጥር አንድ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አስችሎታል። በውድድሩ ወቅትም ያሳየው የጨዋታ ቴክኒክ፣ ፍጥነትና ማራኪነት በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እንዳተረፈለት ዘገባዎች አመልክተዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
271 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us