ሮናልዶ ሜሲን አሸንፎ ኮከብ ሆኗል

Wednesday, 14 December 2016 14:08

 

የአንድ ዘመን ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የሆኑት ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ዘንድሮም ለባሎን ደኦር ሽልማት በእጩነት ቀርበው ተፎካክረዋል። የሽልማቱ አሸናፊ ደግሞ ፖርቱጋላዊው ፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያ ሮናልዶ ሆኗል። የሪያል ማደሪዱ አጥቂ በአውሮፓ ዋንጫ ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር ዋንጫ ማንሳቱ ለሽልማቱ እንዳበቃው ታምኗል።

 የ31 አመቱ ሮናልዶ የባለንደኦር ሽልማትን ሲያሸንፍ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከቅርብ ተፎካካሪው ሊዮኔል ሜሲ ላይ ለመድረስ አንድጊዜ ሽልማቱን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ሮናልዶ ሽልማቱን ባለፈው አመትም የወሰደ ሲሆን፤ በ2008 እና 2013 ማሸነፉ ይታወሳል።

ሮናልዶ በ2016 የውድድር አመት ሪያል ማድሪድ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳ ከማድረጉ በተጨማሪ ሀገሩ ፖርቱጋል የአውሮፓ ዋንጫን እንድታነሳም አስችሏል። በአውሮፓ ዋንጫው ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ለብሔራዊ ቡድኑ ስኬት አስተዋጽኦ አድርጓል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
311 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us