ቻይና ለሮናልዶ 300 ሚሊዮን ፓውንድ አቀረበች

Wednesday, 04 January 2017 14:50

 

-    ካርሎስ ቴቬዝ የአለማችን ውድ ተከፋይ ሆኗል

የቻይና እግር ኳስ የአለምን ትኩረት መሳቡን ቀጥሏል። ወደ ቻይና የእግርኳስ ሊግ የተጫዋቾች ዝውውር ገበያው ደርቷል። ስመጥር ተጫዋቾች የጡረታ ዘመን ሲደርስ ማረፊያቸው ወደ እስያዋ ሀገር ሆኗል።

ሰሞኑን አርጀንቲናዊው ካርሎስ ቴቬዝን የአለማችን ከፍተኛው ተከፋይ ባደረጉበት ስምምነት ወደ ሊጋቸው በማዛወር የአለም መነጋገሪያ የሆኑት ቻይናዎች አሁን ደግሞ የአለም ኮከብ ተጫዋቹን ክርስቲያ ሮናልዶን ለመውሰድ ጠይቀዋል። አንድ ስሙ በይፋ ያልተገለጸ የቻይና ክለብ ሮናልዶን ለሪያል ማድሪድ 300 ሚሊዮን ፓውንድ ማቅረባቸው ተዘግቧል። ከዝውውር ክፍያው በተጨማሪም ለሮናልዶ በየአመቱ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ፈቃደኛ ሆነዋል። የተጫዋቹ ወኪል ዮርግ ሜንዴስ ግን ሮናልዶ የአለማችን ውድ ተጨዋች የሚያደርግ የዝውውር ገንዘብ ቢቀርብለትም ተጫዋቹ የተጫዋችነት ዘመኑን በስፔኑ ክለብ ለማጠናቀቅ የሚፈልግ መሆኑን ተናግሯል።

“ገንዘብ ለሮናልዶ ምንም ማለት አይደለም። ሪያል ማድሪድ የእሱ ህይወት ነው። ሮናልዶ በማድሪድ በጣም ደስተኛ በመሆኑ ወደ ቻይና የመሔዱ ነገር ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው። የቻይና እግር ኳስ ገበያ በእርግጥ ደርቷል። ገንዘባቸው የትኛውንም ተጫዋች ማዛወር እንደሚችሉ እያሳዩን ነው። ሮናዶን ግን በየትኛውም ዋጋ ማዛወር አይችሉም። ክርስቲያ ሮናልዶኮ የአለማችን ምርጥ ተጫዋች ነው።

ካርሎስ ቴቬዝ የቻይናውን ሻንጋይ ግሪንላንድ ሽንዋ ለተባለው ክለብ ለመጫወት የተስማማ ሲሆን፤ የቀረበለት የደሞዝ መጠንም የአለማችን ውዱ ተከፋይ ተጫዋች ያደርገዋል። ከክለቡ ቦካ ጁኒየርስ በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የሁለት አመት ስምምነት የፈረመው የ32 አመቱ አጥቂ በሳምንት 512 ሺ ፓውንድ እንደሚከፈለው ተወርቷል።

ቴቬዝ በቻይናው ክለብ ከቀድሞ የኒውካስል አጥቂዎች ዴምባ ባ እና ኦባፋሚን ማርቲንስ ጋር የሚቀላቀል ይሆናል። በቀድውሞ የቶተንሀም ሆትስፐርና ቼልሲ አሰልጣኝ ጉስ ፖዬት የሚሰለጥነው አዲሱ ክለቡ ሻንጋይ ግሪንላድ ሽንዋን ውጤታማ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
220 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us