ማህሬዝ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን ተጎናፀፈ

Wednesday, 11 January 2017 14:47

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴርሽን አመታዊው የሽልማት መድረክ ባለፈው ሳምንት ተካሒዷል። አስራሚ የውድድር ዓመትን ያሳለፈው አልጄሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል። በሴቶች በቅርቡ የአፍሪካ ዋንጫን ከብሔራዊ ቡድኗ ጋር ያሸነፈችው ናይጂሪያዊቷ በኮከብነት ተመርጣለች።

 

እንዲህ ያለውን ትልቅ ሽልማት ማሸነፍ ቀላል አይደለም። በጣም ደስ ብሎኛል። ከሌስተርሲቲ ጋር ያሳለፍነውን አስደናቂ የውድድር ዓመት መቼም የምደግመው አይመስለኝም። እንደኛ ያለ ትንሽ ቡድን ይደግመዋል ብዬ አላስብም” ሲል ማህሬዝ ከሽልማቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።
ናይጄሪያዊው የአርሴናል ተጫዋች አሌክስ ኢዎቢ የአፍሪካ የአመቱ ወጣት ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል።


የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ኡጋዳዊው ዴኒስ ኦንያንጎ በአፍሪካ አህጉር ከሚጫወቱ ተጫዋቾች ኮከብ ተብሎ ተመርጧል። ተጫዋቹ ከደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር የአፍሪካ ቻምፒንስ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳ ማስቻሉ ተሸላሚ አድርጎታል።


ከ39 ዓመት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ መድረክን የተቀላቀለችው የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ዩጋንዳ ስኬታማ ዓመት በማሳለፏ የአመቱ ምርጥ የብሔራዊ ቡድን ሽልማት ተሸልሟል። ማሜሎዲ ሰንውንስ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ የእግር ኳስ ክለብ በመባል ተመርጧል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
264 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us