ሮናልዶ የፊፋ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ

Wednesday, 11 January 2017 14:26

የፈረንጆቹ 2016 የውድድር ዓመት ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስኬታማ ዓመት ሆኖለታል። ከሀገሩ ፖርቱጋል ጋር የአውሮፓ ዋንጫን በማንሳት የምንግዜም ህልሙን ማሳካት ችሏል። ከክለቡ ሪያል ማድሪድ ጋርም የቻምፒየንስ ሊጉን እና የፊፋ የአለም ክለቦች ዋንጫ አንስቷል። በዚህም የአመቱ ምርጥ የአለማችን እግር ኳስ ተጫዋች ተብሎ በመመረጥ የባሎን ደ ኦር ሽልማትን ለአራተኛ ጊዜ ወስዷል። 

 

አሁን ደግሞ ፊፋ ከስድስት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍራንስ ፉት ቦል መፅሔት ተነጥሎ ያዘጋጀውን የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን በማሸነፍ የ2016 ዓመትን በድል አጠናቋል።


“የ2016 የውድድር ዓመት በተጫዋችነት ዘመኔ ካሳለፍኩት ሁሉ ምርጡ ጊዜዬ እንደሆነ ነው የምነግራችሁ። በእርግጥ ይህ እውነት ለመሆኑ ጥርጣሬ ነበረኝ። ነገር ግን ይህ ሽልማት ምርጥ ዘመኔ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ሲል ሮናልዶ ከሽልማቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።
የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ሽልማት የተካሔደው ከፍራንስ ፎትቦል መጽሔት ጋር የሚያዘጋጀው የባሎን ደ ኦር ሽልማትን መስጠት በማቆሙ ነው።
በሴቶች አሜሪካዊቷ ካርሊ ሎይድ በኮከብነት ተመርጣለች።


በእግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሌስተር ሲቲ ክለብ ዋንጫ እንዲያነሳ ያስቻሉት ጣሊያናዊው ክላውዲዮ ራኔየሪ የ2016 ምርጥ አሰልጣኝ ተብው ተሸልመዋል። የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርት ሞንድ ደጋፊዎች የዓመቱ ምርጥ ደጋፊዎች ሽልማትን ተጎናጽፈዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
192 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us