በአዲስ አበባ ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ተመሠረተ

Wednesday, 11 January 2017 14:55

በተለያዩ ባለሙያዎችና ባለሃብቶች የተዋቀረው የአዲስ አበባ ኢትዮ-ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ባሳለፍነው ታህሳስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በዋሽንግተን ሆቴል በይፋ ተመሠረተ። የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ የሆነው የቴኳንዶ ስፖርት ፌዴሬሽን በፕሬዝዳንትነት አቶ በቀለ በዳዳን ሲይዝ፤ አቶ በሽር እድሪስ፣ አቶ ግርማ ጥሩነህ፣ ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን፣ ወ/ሮ ልዩ ደምሰው፣ አቶ መንገሻ ግርማ እና አቶ ረመዳን አንበሴን ያካተተ ሰባት አባላት ያሉት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተዋቅሮለታል።

 

በምስረታ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ከ30 ዓመታት በላይ በቴኳንዶ ስፖርት አሰልጣኝነት የሰሩት ሲኒየር ማስተር አብዱ ከድር የተገኙ ሲሆን፤ በፌዴሬሽኑ መመስረት የተሰማቸውንም ደስታ እንባ በተቀላቀለበት ስሜት ሲገልፁ አስተውለናል። በዕለቱ የኮሪያ ኤምባሲ ተወካዮችም የተገኙ ሲሆን፤ የቴኳንዶ ስፖርትን ለማሳደግ ተባብረው እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

 

 

ከአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ባለሙያዎች የተገኙበት የምስረታው ፕሮግራም፤ የጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳን በማቅረብ ውይይትም አድርጓል። የቴኳንዶ ስፖርትን ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተባብረው ለመስራት በአዲስ መንፈስ ቃልም ገብተዋል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
225 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us