አበሩ ከበደ የበርሊን ማራቶንን ለአራተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ትሮጣለች

Wednesday, 20 September 2017 18:24

በበርሊን ማራቶን ተደጋጋሚ ድሎችን በማስመዝገብ ከሚታወቁ ጥቂት የአለማችን ሯጮች መካከል አንዷ የሆነችው አበሩ ከበደ ዘንድሮም በውድድሩ መድረክ ለአሸናፊነት ትጠበቃለች። አትሌቷ በውድድሩ መድረክ ለአራተኛ ጊዜም በማሸነፍ ስሟን በታሪክ መዝገብ ለማስፈር መዘጋጀቷን አስታውቃለች።

የበርሊን ማራቶን የፊታችን እሁድ የሚካሔድ ሲሆን፤ በሴቶች ኢትጵያዊቷ አትሌት አበሩ ከበደ የአምና ድሏን እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል። አበሩ ያለፈው አመትን ጨምሮ የ2010 እና የ2012 የበርሊን ማራቶን አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል። ዘንድሮም የምታሸንፍ ከሆነ በውድድሩ ታሪክ ለአራት ጊዜ በማሸነፍ ስሟ በደማቅ የድል ቀለም የሚሰፍር ይሆናል።

ከአበሩ በተጨማሪ በውድድሩ መድረክ ከሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆነችው አማኔ በሪሶም ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። አትሌቷ ባለፈው አመት የዱባይ ማራቶንን በሁለተኛነት ማጠናቀቋ ለአሸናፊነት እንድትታጭ አድርጓታል። ከዚህ በተጨማሪም የ2015 የፍራንክፈርት ማራቶን አሸናፊ ጉሉሜ ቶለሳ እና የፓሪስ ማራቶን አሸናፊዋ መሰረት መንግስቴ በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ውጤታማ እንደሚሆኑ ግምት አግኝተዋል።

ከኢትጵያውያን በተጨማሪ ኬንያውያን አትሌቶችም ለአሸናፊነት ይጠበቃሉ። በተለይም ደግሞ የ2015 አሸናፊዋ ግላዲ ቼሬኖ በርቀቱ ያላት ፈጣን ሰአት 2፡21፡25 ከፍተኛ ግምት እንዲሰጣት አድርጓል። ሌላዋ ኬንያዊት ቫለሪ አይቤም ዘንድሮ በፕራግ ማራቶን ማሸነፏ እና በርቀቱ ያላት ምርጥ ሰአት 2፡21፡57 እሁድም ለድል እንድትጠበቅ አድርጓል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
73 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 99 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us