ጋናዊው አጥቂ አርባ ምንጭን ተቀላቅሏል

Wednesday, 20 September 2017 18:27

የጋና ብሔራዊ ቡድንና የቀድሞው የአሻንቴ ኮቶኮ ክለብ አጥቂ ሰይዱ ባንሴይ ለአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለማጫወት ፊርማውን አኑሯል። ተጨዋቹ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግችን በማስቆጠር ኮከብ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በጋና፣ በግብጽና በቱርክ ክለቦች በመጫወት ልምድ ያካበተው የ27 አመቱ ጋናዊው አጥቂ ሰይዱ ባንሴይ ለኢትዮጵያዊው ክለብ አርባ ምንጭ ከተማ ለመጫወት ተዘጋጅቷል። ተጫዋቹ በጋና ታዋቂ ለሆነው ክለብ ለአሻንቱ ኮቶኮ የተጫወተ ሲሆን፤ በግብጽ ሊግ ስሙሀ ለተባለ ክለብ ለአንድ አመት ተሰልፏል። በ2016 የውድድር አመት ደግሞ ወደ ቱርክ በማምራት ለጋላታሳራይ ተጫውቷል። አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአርባምንጭ ከተማ መለያ የሚሰለፍ ይሆናል።

ሰይዱ ባንሴይ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጫወት አምስተኛው ጋናዊ መሆኑን ጋና ሶከርኔት ዶት ኮም ዘግቧል። ቀደም ባሉት ጊዜያት አብዱላቲፍ ሞሀመድ፣ ማሳላቺ ባባ አዳም፣ ማይክል አኩፉ፣ ኬኔዲ አሺ እና ማክ አናን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተጫወቱ ጋናውያን መሆናቸውን ዘገባው አስታውሷል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
88 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 102 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us