የዓለም ክብረወሰን የሚጠበቅበት የበርሊን ማራቶን እሁድ ይካሔዳል

Wednesday, 20 September 2017 18:27

Sport2መታዊው የበርሊን ማራቶን የፊታችን እሁድ ይካሔዳል። ከወትሮው በተለየ መልኩ በወንዶች ሶስት የአለማችን ፈጣን ሯጮች የሚፎካከሩበት ይሆናል። የርቀቱ የአለም ክብረወሰንም እንደሚሻሻል ይጠበቃል። ኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ ከኬንያውያኑ ኢውድ ኪፕቾጌ እና ዊልሰን ኪፕሳንግ ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቀዋል።

የአለም የማራቶን ክብረወሰን እንደሚሰበርበት የሚጠበቀው ይኸው ማራቶን ውድድር በመድረኩም የርቀቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤቶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ኢውድ ኪፕቾጌ እና ዊልሰን ኪፕሳንግ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ቀነኒሳ በቀለ ርቀቱን ከ2 ሰአት ከ02 በታች ለመሮጥ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የበርሊን ማራቶን መድረክ የአለም ክብረወሰን በተደጋጋሚ ከሚሻሻልባቸው የማራቶን መድረኮች አንደኛው ነው። በዚህ መድረክ ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ንጉስ ሀይሌ ገብረስላሴ ሁለት ጊዜ የርቀቱን የአለም ክብረወሰንን መስበሩ ይታወሳል። ቀነኒሳ በቀለም የሀይሌን ታሪክ ለመድገም ተዘጋጅቷል።

ከቀነኒሳ በተጨማሪ በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ኬንያውያኑ ኢውድ ኪፕቾጌ እና ዊልሰን ኪፕሳንግም ክብረወሰን የማስመዝገብ ብቃት ላይ የሚገኙ አትሌቶች ናቸው። በዚህም የተነሳ ውድድሩ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል።

የውድድሩ አዘጋጆች ከፍተኛ ዝግጅት ያደረጉበት መድረክ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ሶስቱን አትሌቶች በአንድ መድረክ ማገናኘት መቻል በቀላሉ የማይሳካ ትልቅ እድል ነው ብለዋል።

ቀነኒሳ በቀለ ባለፈው አመት የበርሊን ማራቶን አሸናፊ የነበረ ሲሆን፤ ርቀቱን ያጠናቀቀበት 2፤03፤03 የአለም ሁለተኛው ፈጣን ሰአት ነው። የርቀቱ የአለም ክብረወሰን 2፡02፡57 ከሶስት አመት በፊት በኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ የተመዘገበ ነው። ቀነኒሳ የአለም ክብረወሰንን ለማሻሻል ስድስት ሰከንዶች ብቻ የቀሩት መሆኑ እጅግ የሚያስቆጭ አጋጣሚ እንደነበር በወቅቱ አትሌቱ ተናግሮ ነበር።

በዘንድሮው የበርሊን ማራቶን መድረክ ግን የርቀቱን ክብረወሰንን ለማሻሻል መዘጋጀቱን ቀነኒሳ በቀለ አስታውቋል። ርቀቱንም ከ2፡02 በታች መግባት እንደሚችል ነው የተናገረው። ለእሁዱ ፉክክርም ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

የቀነኒሳ የቅርብ ተፎካካሪዎች ኢውድ ኪፕቾጌ እና ዊልሰን ኪፕሳንግም የማራቶን ክበረወሰንን ለማስመዘግብ እንደሚሮጡ ነው የገለጹት። ኪፕቾጌ በቅርቡ ማራቶንን ከሁለት ሰአት በታች ለመሮጥ በተዘጋጀው ልዩ ፉክክር ላይ ያስመዘገበው ፈጣን ሰአት እውቅና ባይሰጠውም ለእሁዱ መድረክ እገዛ እንደሚያደርግለት ተናግሯል። ክብረወሰኑን ለማሻሻልም ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

ቀደም ሲል ለማራቶን የአለም ክብረወሰን ባለቤት የነበረው ዊልሰን ኪፕሳንግም በበርሊን ማራቶን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጣን ሰአት እንደሚያስመዘግብ ተስፋ አድርጓል። አትሌቱ በ2013 የማራቶን ክብረወሰንን 2፡03፡23 በሆነ ሰዓት በስሙ ማስዝገቡ ይታወሳል። የፊታችን እሁድም ለሁለተኛ ጊዜ የአለም የማራቶን ክብረወሰንን ለማስመዝገብ እንደሚሮጥ አስታውቋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 767 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us