ፋሲል ከነማ በአፍሪካውያን ተጨዋቾች ቡድኑን እያጠናከረ ነው

Wednesday, 20 September 2017 18:31

Sport3ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የተቀላቀለው ፋሲል ከነማ ቡድኑን በአዳዲስ ተጫዋቾች በማዋቀር ላይ ነው። በተለይም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ልምድ ካላቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ በሌሎች አፍሪካውያን ተጫዋቾችም ቡድኑን ማጠናከርን መርጧል።

የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት ከሆኑ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ፋሲል ከነማ በዘንድሮው ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከዋንጫ ተፎካካሪዎች ተርታ የሚገመት ሆኗል። ቡድኑ ባለፈው አመት ፕሪሚየር ሊጉን ከተቀላቀለ በኋላ እንደብዙዎቹ እንግዳ ክለቦች ላለመውረድ የሚጫወት አልነበረም። ይልቁንም ታላላቅ ለሚባሉ የሀገሪቱ ክለቦች ፈታኝ የሆነበት አቋሙን በማሳየት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ሊጉን ማጠናቀቁ ይታወሳል። ዘንድሮም የተሻለ አቋም ከማሳየት ባሻገር ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በማስፈረም ከወዲሁ የዋንጫ ተፎካካሪ እንደሚሆን እያስመሰከረ ነው። በቅርቡም ሁለት ኡጋንዳውያን ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ታውቋል።

ለፋሲል ከነማ የፈረሙት ዩጋንዳውያን ተጫዋቾች ያሰር ሙገርዋ እና ሮበርት ሴንቶንጎ ናቸው። ሴንቶንጎ ከዩጋንዳ ኬሲሲኤ ከተባለ የሀገሩ ክለብ በነጻ ዝውውር የጎንደሩን ክለብ መቀላቀሉ ተነግሯል። ሙገርዋ ደግሞ ቀደም ሲል በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በመጫወት ልምድ አለው።

የ29 አመቱ ሮበርት ሴንቶንጎ በዩጋንዳ እንደ ሲምባ እና ኤኤስ ቪላ ለተባሉ ታዋቂ ክለቦች የተጫወተ ልምድ ያለው ተጫዋች ነው። ከ2012 እስከ 2014 በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ተጫውቷል። ተጫዋቹ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በመጫወት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የሚውያውቅ በመሆኑ አዲሱ ክለቡ ውጤታማ ለመሆን እንደማይቸገር ይገመታል።

የ23 አመቱ ያሰር ሙገርዋ ደግሞ የአማካይ መስመር ተጫዋች ሲሆን፤ ባለፈው አመት ለደቡብ አፍሪካው ለኦርላንዶ ፓይሬትስ በመፈረም በሊጉ የአጭር ጊዜ ቆይታ አድርጓል። ከሁለት አመት በፊትም በሰርያዊው አሰልጣኝ ሚቾ አማካይነት ለዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በመመረጥ መሰለፍ ችሏል። በፋሲል ከነማ ብቃቱን እንደሚያሳይ ይጠበቃል።

ፋሲል ከነማ ከሁለቱ ዩጋንዳውያን በተጨማሪ የግብ አዳኙ ፊሊፕ ዳውዝን ማስፈረሙ ይታወቃል። የማሊውን ግብ ጠባቂ ማይክል ማማዱ ሳማኪን አስፈርሟል። ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና መብራት ሀይል አማካይ ዳዊት እስጢፋኖስን፣ ራምኬል ሎክን ከቅዱስ ጊዮርስ፣ ቢንያም ሀብታሙን ከድሬደዋ ከተማ፣ አይናለም ሀይሉን ከደደቢት ማስፈረሙ ይታወሳል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 100 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us