የቅዱስ ጊዮርጊስ አዲሱ አሰልጣኝ

Wednesday, 20 September 2017 18:32

ከሆላንዳዊው ማርት ኖይ ጋር የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ፖርቱጋላዊ አሰልጣኝ ቀጥሯል። አሰልጣኙ በአፍሪካ እግር ኳስ ያላቸው እውቀትና ልምድ ኢትዮጵያዊውን ክለብ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው ተገምቷል።

አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሙሉ ስም ካርሎስ ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ ሲሆን፤ የ43 አመት ጎልማሳ ናቸው። በእግር ኳስ አሰልጣኝነት የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ኤ ላይሰንስ አላቸው።

አሰልጣኙ በአፍሪካ እግር ኳስ በአንጎላ ካላ እና ሪከሬቲቮ ደ ሊቦሎ ከተሰኙ ክለቦች ጋር ቆይታ ነበራቸው። ከዚህ በተጨማሪም በሀገራቱ የወጣቶች ቡድንን በማሰልጠንም ልምድ እንዳላቸው የግል ማህደራቸው ላይ የሰፈረው መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በርካታ ዋንጫዎችን በመውሰድ ክብረወሰኑን የያዘው ቅዱስ ጊዮርጊስን በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ የእግር ኳስ መድረክም ውጤታማ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በአሰልጣኝ ማርት ኖይ እየተመራ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ዋንጫ ለ14ኛ ጊዜ ያነሳ ሲሆን፤ በአፍሪካ ቻፒየንስ ሊግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ምድብ ፉክክር ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። የአሁኑ የክለቡ አሰልጣኝም ከዚህ የተሻለ የውጤት ታሪክ የማስመዝገብ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
119 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 101 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us