መሰረት ደፋር ወደ አሸናፊነት ተመልሳለች

Wednesday, 20 September 2017 18:33

Sportየአለምና የኦሊምፒክ አሸናፊዋ መሰረት ደፋር ለረጅም ጊዜ ከውድድር መድረክ ርቃ ከቆየች በኋላ በድጋሚ ወደ በአሸናፊነት ተመልሳለች። ውጤቱ በቀጣይ የጎዳና ሩጫ ላይም ስኬታማ መሆን እንደምትችል በማመላከቱ አድናቆት አሰጥቷታል።

ላለፉት ሁለት አመታት የሪዮ ኦሊምፒክና የለንደን የአለም ሻምፒዮናን ጨምሮ በበርካታ አለምአቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ በጉዳት ርቃ የቆየችው አትሌት መሰረት ደፋር በድጋሚ ወደ ፉክክር ተመልሳለች። አትሌቷ በትራክ ሩጫ ላይ የምትታወቅበትን አሸናፊነት ማስመዝገብ ችላለች።

ባለፈው እሁድ በአሜሪካን ፊላደልፊያ የግማሽ ማራቶን ሩጫ በሴቶች መካከል በተካሔደው ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ መሰረት ደፋር የቅርብ ተፎካካሪዋን ሮቲችን  ከአንድ ደቂቃ በላይ በመቅደም ድል አድርጋለች። ርቀቱንም በ1፡08፡46 በሆነ ሰአት ነው ያጠናቀቀችው። ኬንያዊቷ ካሮሊን ሮቲች እና አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሃሴይ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ገብተዋል። ሌላዊቷ ብዙነሽ ዳባ አራተኛ ደረጃ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች።

መሰረት ደፋር ከረጅም ጊዜ ከውድድር መድረክ ከጠፋች በኋላ ያስመዘገበችው ውጤት በቀጣይ በተለይ በጎዳና ሩጫ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናት ይታመናል።

በተመሳሳይ መድረክ በወንዶች መካከል በተደረገው ፉፉክር አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ ድል አድርጓል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
128 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 963 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us