የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መቼ እንደሚጀመር አልታወቀም

Thursday, 28 September 2017 14:48

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2010 ዓ.ም የውድድር መርሀ ግብር ድልድልን ይፋ ቢያደርግም መቼ እንደሚጀመር ግን በትክክል አላሳወቀም። የአየር ንብረት ሁኔታው እየታየ ቀኑ ሊወሰን ይችላል ተብሏል።

ቀደም ሲል የ2010 ዓ.ም. የውድድር መርሀ ግብር ጥቅምት 10 ቀን እንደሚጀምር ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፤ ወደ ጥቅምት 11 ቀን መራዘሙን አስታውቆ ነበር። ይሁንና በድጋሚ የውድድሩ መጀመሪያ ወደ ጥቅምት 27 መራዘሙ ነው የተገለጸው። ይህ ቀንም ትክክለኛው ስለመሆኑ በእርግጠነኝነት አልተነገረም። የእግር ኳስ ሜዳዎችን አስቸጋሪ በማድረግ ጨዋታዎችን ለማካሄድ አያስችልም የተባለው ዝናባማው የአየር ንብረት ከቀጠለ ጊዜውምው ሊራዘም ይችላል ተብሏል።

ሰሞኑን የፕሪሚየር ሊጉ ድልድል ይፋ በሆነበት ወቅት እንደተገለጸውም ጥቅምት 27 እንደሚጀመር የተያዘው መርሀግብር የአየር ንብረቱ እየታየ ጊዜው ሊቀየር እንደሚችል ነው የተገለጸው። የአየር ንብረቱ ሜዳዎችን ለጨዋታ አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል የሚለው ሐሳብ ዋነኛ ምክንያ ሆኖ ተጠቅሷል።

ይሁንና የፕሪሚይር ሊጉ መራዘም በብዙ መልኩ የሚፈጥረው ተጽዕኖ የጎላ ነው። በተለይም የውድድር መርሀ ግብሮች ጊዜያቸውን ጠብቀው አለመከናወናቸው የክለቦችንም አመታዊ እቅድ የሚያዛባ ነው። ይህም ለከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የሚዳርጋቸው ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
62 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us