የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ በስፔን ተቋም ይተዳደራል

Thursday, 28 September 2017 14:50

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በደብረዘይት ከተማ ያስገነባው የይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች ማሰልጠኛ አካዳሚን እንዲያስተዳድርለት ሶክሳና የተባለውን የስፔኑን የእግር ኳስ ተቋምን መርጧል። አካዳሚውን ለቀጣይ አምስት አመታት ማስተዳደር የሚቻልበት ሁኔታን ለመተግበርም ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።  

ባለፈው ሐሙስ በሸራተን አዲስ በተካሔደ ስነ ስርአት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀልና የሶክሳና ምክትል ፕሬዝዳንት ፊርማቸውን አኑረዋል። ስምምነቱ ከእግር ኳስ በተጨማሪ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል።

ዋና መቀመጫውን በስፔን ማድሪድ ያደረገው ሶክሳና የእግር ኳስ ማዕከል የተለያዩ ሀገሮች የታዳጊዎች እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከሎችን በመምራትና በማስተዳደር ስራ ይታወቃል። ተቋሙ የሪያል ማድሪድ የታዳጊዎች ማሰልጠኛ ማዕከልንና የክለቡ አጋር የሆነውን የቻይና ኤቨርግራንዴ ማድሪድ የተሰኘውን የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከልን ያስተዳድራል። በሆንግ ኮንግም ቢሮ ከፍቶ እንደሚሰራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። በቀጣይ ጊዜያትም በአፍሪካ የመስራት እቅድ ያለው ሲሆን፤ ኢትዮጵያም የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።

የስፔኑ ተቋም በይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ከሚኖረው ዋነኛ ኃላፊነት መካከል ማዕከሉን የማስተደደር ሰልጣኞችን መመልመልና ማሰልጠን ነው። አካዳሚው ተግባራዊ የሚያደርገውን የስልጠና መመሪያንም በመቅረጽ የሚሰራ ይሆናል። በዚህም መሰረት በመጀመሪያው አመት የስራ ጊዜ የላቀ ተሰጥኦ ያላቸውን ሀምሳ ታዳጊዎች በማዕከሉ እንዲሰለጥኑ ለመመልመል አቅዷል። ለዚህም 359 ሺ ዩሮ የሚመደብ ሲሆን፤ በቀጣዩ አመት ወጪው ወደ679 ሺ ዩሮ ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

የሶክሳና ማዕከል ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ሎፔዝ ኢትዮጵያ የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎች በብዛት የሚገኙባት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ “በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች ሰልጣኞችን የመመልመል ስራ ቀዳሚው ተግባራችን ነው” ብለዋል። ለዚህም ደግሞ ከኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ጋር እንደሚሰሩ ነው ያስታወቁት።

በማዕከሉ የሚሰሩ ባለሞያዎችን በራሱ ምርጫ የሚያስመጣ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎችም የማሰልጠን እድል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከስፔኑ ተቋም ጋር የተፈጸመው ስምምነት ታሪካዊ መሆኑን ገልጸው፤ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የላቀ ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ባለሞያዎችም በአካዳሚው እንዲሰሩ በማድረግ የእውቀት ሽግግር ይደረጋል ብለዋል።

ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የይድነቃቸው እግር ኳስ አካዳሚ መጋቢት ወር ላይ የካፍ ከፍተኛ የስራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል። ማሰልጠኛ ማዕከሉ የእግር ኳስ መጫወቻና ልምምድ መስሪያ ሜዳ፣ የጅምናዚየም መስሪያ፣ የመኝታ ክፍሎች፣ የመመገቢያ አዳራሽ በውስጡ የያዘ ነው። ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የሀገሪቱ ክለቦች ብሎም እንደዚሁም ሀገሮች ክለቦች ተፈላጊ ሊሆኑ የሚችሉ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾችን ለማፍራት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
109 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 989 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us