ፓል ቴርጋት የኬንያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሆኗል

Wednesday, 04 October 2017 12:47

በሩጫ ስፖርት ከኢትዮጵያዊው ኃይሌ ገብረስላሴ ጋር ተደጋጋሚ ፉክክሮችን ማድረግ የሚጠቀሰው ፓል ቴርጋት የኬንያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል። የቀድሞው የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት በዶፒንግ ጋር በተያያዘ የቆሸሸውን የኬንያን ስም ለማጽዳት ማጽዳት ቀዳሚው ተግባሩ መሆኑን አስታውቋል።

የኬንያ የምንግዜም ምርጥ ሯጭ ፓል ቴርፓት ሩጫን ካቆመ በኋላ ከስፖርትና ከማህበራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በማከናወን ላይ ቆይቷል። በየአመቱ የኬንያ ምርጥ ስፖርተኞችን የሚሸልም ተቋም በማቋቋምም የሀገሩን ስፖርተኞች በማበረታታት እየሰራ ነው። አሁን ደግሞ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን በዶፒንግ የቆሸሸው የኬንያን አትሌቲክስ የሚታደግበት ሀላፊነትን መረከብ ችሏል።

የኬንያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ምርጫ ባለፈው ቅዳሜ የተከናወነ ሲሆን፤ ያለ ተፎካካሪ በእጩነት የቀረበው ፓል ቴርጋት በፕሬዝዳንትነት ተመርጧል። የቀድሞው የኦሊምፒክ ከሜቴው ፕሬዝደንት ኪፕ ኬኖ ከሪዮ ኦሊምፒክ በኋላ በሙስና ስማቸው ከጎደፈ በኋላ ሀላፊነታቸው መቀጠል አልፈለጉም።

ቴርጋት በሲድኒ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ከኃይሌ ገብረስላሴ ጋር ያደረገው አስደናቂ ፉክክር የአለማችን አንደኛው አይረሴ ክስተት ሆኖ ሁሌም ይታወሳል። በውድድሩ መጨረሻ ላይ ሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ፉክክር በኢትዮጵያዊው አሸናፊነት ነበር የተጠናቀቀው።

በትራክ ላይ ሩጫዎች በተደጋጋሚ በኃይሌ ገብረስላሴ የሚገጥመው ሽንፈት እንዳያንጻባርቅ ቢያደርገውም ምርጥ አትሌትነቱ የሚያጠራጥር አይደለም። ወደ ማራቶን ሩጨ ካቀና በኋላም ውጤታማ አመታትን ያሳለፈ ሲሆን፤ የርቀቱን የአለም ክብረወሰን ለማስመዝገብ ችሎ ነበር።

ከሩጫ ውጪ ባለው ህይወቱና ተግባሮቹ በሀገሩ ህዝብ አክብሮትን ያተረፈው ቴርጋት፤ ለብዙ ለኬንያውያን ሯጮች በመልካም አርአያነት የሚጠቀስ ነው። በሩጫና ከሩጫ ውጪ ባለው መልካም ስም እና ዝና የኬንያ ስፖርትን እንደሚታደግ ታምኖበታል። ለቀጣይ አራት አመታትም የሀገሪቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በፕሬዝዳትነት እንዲመራ ለመመረጥ ችሏል።

ቴርጋት የኬንያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በፕሬዝዳንትነት መምራት ከባድ ሀላፊነትና ብዙ የቤት ስራዎች ያሉት መሆኑን ነው ከምርጫው በኋላ በሰጠው አስተያየት የተናገረው። ከባዱና የመጀመሪያ ስራው ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ በአለም ዘንድ የቆሸሸውን የኬንያን የአትሌቲክስ ስፖርት መታደግ እንደሆነ ነው ያስታወቀው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1037 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us