“ኢትዮጵያ የ2018 የቻን ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ አቅርባለች”

Wednesday, 04 October 2017 12:55

“ኢትዮጵያ የ2018 የቻን ዋንጫን ለማዘጋጀት

ጥያቄ አቅርባለች”

ካፍ

“ውድድሩን ለማስተናገድ ጥያቄ አላቀረብንም”

አቶ ጁነዲን ባሻ የኢ.እ.ፌ. ፕሬዝዳንት

 

ኬንያ የተነጠቀችውን የ2018 የአፍሪካ ሀገሮች እግር ኳስ ውድድር (ቻን) ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ ካቀረቡ ሶስት ሀገሮች ጋር ኢትዮጵያ አንደኛዋ ሆና ተጠቅሳለች። ኢትዮጵያ ግን ውድድሩን ለማስተናገድ ጥያቄውን እንዳላቀረበች ነው ያስታወቀችው።

በየሁለት አመቱ የሚካሔደውና በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ አፍሪካውያን ተጫዋቾችን ብቻ ያካተቱ ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳፉበት የቻን ዋንጫ በ2018 በኬንያ ለመካሔድ የነበረው እቅድ ሳይሰምር ቀርቷል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ገምጋሚ ቡድን ሶስት ጊዜ የኬንያን ዝግጀት ከጎበኘ በኋላ ሀገሪቱ ውድድሩን የማዘጋጀት አቅም የላትም ብሏል። ባለፈው ቅዳሜ እለትም ኬንያ የ2018 የቻን አዘጋጅነት መነጠቋን በይፋ ከገለጸ በኋላም ሶስት ሀገሮች ውድድሩን ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረባቸውን በድረ ገጹ ባሰራጨው መረጃ ላይ አስታውቋል። የካፍን መረጃ ተከትለውም በርካታ የአለም መገናኘ ብዙሀን ኢትዮጵያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሞሮኮ የ2018 የቻን ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረባቸውንም እየዘገቡት ነው።

የሀገር ውስጥ ውደድሮችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማከናወን የተቸገረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 16 ሀገሮች የሚሳተፉበትን አህጉራዊ ውድድር በአጭር ጊዜ ዝግጅት ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቡ የስፖርት ቤተሰቡን አስገርሟል። ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሔድ በአዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ በሚወጠርበት ወቅት ላይም የቻን ውድድርን ለማዘጋጀት መፈለጉ ከፍተኛ ትችት አሰንዝሮበታል። 

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁይነዲን ባሻ ግን የካፍ ድረ ገጽን ዋቢ በማድረግ ብዙዎች እየተቀባበሉት ስላለው መረጃ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ የቻን ውድድርን ለማዘጋጀት ጠይቃለች የሚለው መረጃ እንዴትና በየት በኩል ይፋ እንደሆነም እናጣራለን ብለዋል።

"የ2018 የቻን ውድድርን ለማስተናገድ ቀደም ብለን ጥያቄ አቅርበን የነበረ ቢሆንም ካፍ ኬንያን ነበር የመረጠው። አሁን ኬንያ አዘጋጅነቷን ከተነጠቀች በኋላ ግን በምትኳ የቻን ውድድርን ለማስተናገድ ጥያቄውን ለካፍ አላቀረብንም›› ሲሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገጽ ምላሽ የሰጡት አቶ ጁይነዲን ባሻ፤ ‹‹መረጃው ለካፍ የደረሰበትን ሁኔታንም ሆነ የተፈጠረ የመረጃ ክፍተት ስለመኖሩ እናጣራለን›› ብለዋል።

የ2018 የቻን ዋንጫ ከጃንዋሪ 12 እስከ ፌብሩዋሪ 4 ቀን እንደሚከናወን የወጣው መርሀግብር ያመለክታል። የውድድሩ አዘጋጅ የነበረችው ኬንያን በመተካት የሚያስተናግደውን ሀገር በቀጣዩ ሳምንት ካፍ ይፋ እደሚያደርግ አስታውቋል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያን በመተካት ውድድሩን ለማዘጋጀት ጥያቄ አቅርበዋል የተባሉት ሞሮኮና ኢኳቶሪያል ጊኒ አንዳቸው እንደሚመረጡ ነው የሚጠበቀው። ሞሮኮ ለቻን ውድድር ማለፏን ያረጋገጠች ሀገር ስትሆን፤ ውድድሩን የማዘጋጀት ሰፊ እድል እንዳላት ይታመናል።

ሌላዋ ሀገር ኢኳቶሪያል ጊኒ የ2018 የቻን ውድድርን በብቃት የማስተናገድ አቅም እንዳላት የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት ተሞክሮዋ ይመሰክራል። ሀገሪቱ በኬንያ ቦታ የ2018 የቻን ዋንጫን የማዘጋጀት እድሉን ካገኘች በማጣሪያው የወደቀው ብሔራዊ ቡድኗ የመሳተፍ እድል የሚያገኝ ይሆናል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 891 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us