ጥሩነሽ ዲባባ በቺካጎ ማራቶን ትጠበቃለች

Wednesday, 04 October 2017 12:59

ኢትዮጵዊቷ የትራክ ላይ ንግስት የምትባለው ኢትዮጵዊቷ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በነገው የቺካጉ ማራቶን ለድል ትጠበቃለች።

ከ40ሺ በላይ ተሳታፊዎች የሚሮጡበትና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ በአካል ይከታተለዋል ተብሎ የሚጠበቀው አመታዊው የቺካጎ ማራቶን ነገ ከከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ጋር ይካሔዳል። ከላስ ቬጋስ ጥቃት በኋላ ለወድድሩ ከፍተኛ ጥበቃ እንደሚያደርጉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

በውድድሩ መድረክም በሴቶች መካከል በሚካሔደው ፉክክር ከለንደን የአለም ሻምፒዮና በኋላ ለውድድሩ ስትዘጋጅ የቆየችው ጥሩነሽ ዲባባ ለአሸናፊነት ታጭታለች። ኬንያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋትም የጥሩነሽ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምትሆን ይጠበቃል።

በለንደኑ የአለም አትቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች የ10.000ሜትር ፉክክር አልማዝ አያናን ተከትላ በመግባት ያገኘችው የብር ሜዳልያ አድናቆትን አሰጥቷታል። አትሌቷ በትራክ ላይ የመሮጥ ብቃቷን የለካችበትም ነበር። ከሻምፒዮናው በኋላም ለቺካጎው ማራቶን ዝግጅት ነው ያመራችው

በ2002 በፓውላ ራድክሊፍ የተመዘገበው ሰአት 2፡17፡18 አሁንም ድረስ የውድድሩ ክብረወሰን ሆኖ ቆይቷል። በተመሳሳይ የመሮጫ መድረክ በተካሔደው የ2017 የለንደን ማራቶን በርቀቱ የመጀመሪያዋን ፉክክር ያደረገችው ጥሩነሽ ዲባባ፤ ውድድሩን በሁለተኛነት ስታጠናቅቅ ያስመዘገበችው ሰአት 2፡17፡56 ነበር። ይህም ሰአት የኢትዮጵያ ክብረወሰንና የግሏ ፈጣን ሰአት ሆኖ ተመዝግቦላታል።

ጥሩነሽ በነገው የቺካጎ ማራቶን የዛሬ 15 አመት በእንግሊዛዊቷ የተመዘገበውን የውድድሩን ክብረወሰን እንደምታሻሽለው አዘጋጆቹ ተስፋ አድርገዋል። እርሷም የምትችለውን ሁሉ በማድረግ እንደምትሮጥ ነው የተናገረችው።

‹‹በትራክ ላይ ያዳበርኩትን የ10ሺ ሜትር ፈጣን የአጨራረስ ብቃት በቺካጎው ማራቶን ፉክክር ላይም በመጠቀም አሸንፌ አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ እፈልጋለሁ። ብላለች።

ከጥሩነሽ ዲባባ በተጨማሪ አምና የውድድሩ አሸናፊ የነበረችው ኬንያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። አትሌቷ ነገ ድል ከቀናት በመድረኩ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ በማሸነፍ በልዩነት የምትጠራ ይሆናል። በ2014 ደግሞ ሁለተኛ ሆና ነበር የገባችው።

በወንዶች ደግሞ ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ለአሸናፊነት ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል አንዱ ነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
137 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 896 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us