አልማዝ አያና ለ2017 የዓለም ምርጥ አትሌትነት ታጭታለች

Wednesday, 04 October 2017 13:00

የአለም እና የኦሊምፒክ አሸናፊዋ አልማዝ አያና ለ2017 የአለም ምርጥ የሴት አትሌትነት ከተመረጡ አስር እጩዎች መካከል አንዷ ሀናለች። ሽልማቱን ለሁለተኛ ጊዜ ለመውሰድ ከቻለች የመጀመሪያዋ ሴት ኢትጵያዊ ትሆናለች።

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር የ2017 የአለም ምርጥ አትሌቶች ምርጫን ለማከናወን በሁለቱም ጾታዎች የመጀመሪያዎቹን አስር አስር አትሌቶች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። አልማዝ አያና ከአስሩ ዕጩዎች መካከል ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆና ተመርጣች። ኬንያ በአንድ የወንድ እና አንድ የሴት አትሌት በእጩነት ቀርበውላታል።

በ2016 የሪዮ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር አስደናቂ ብቃት በማሳየት የአለም ከብረወሰንን አሻሽላ ማሸነፍ የቻለችው አልማዝ አያና በዳይመንድ ሊግ መድረኮችም ድል አድርጋ ተሸላሚ መሆኗ አይዘነጋም። በውድድር አመቱ ያሳየችው ድንቅ አቋምና ውጤትም የ2016 የአለም ምርጥ የሴት አትሌት በመባል እንድትሸለም አድርጓታል።

በ2017 የውድድር አመት ግን አልማዝ ተመሳሳይ አቋም ሳታሳይ በጉዳት የተነሳ ጠፍታ ነበር የቆየችው። ይሁንና ከአንድ ወር በፊት በለንደን በተካሔደው የ2017 የአለም ሻምፒዮና በተመሳሳይ የ10,000 ሜትር ርቀቱን በድንቅ ብቃት አሸንፋ የወርቅ ሜዳልያ መውሰድ ችላለች። በ5,000 ሜትርም ተወዳድራ የብር ሜዳልያ መውሰዷ ይታወሳል።

አልማዝ በለንደኑ የአለም ሻምፒዮና ባስመዘገበችው ውጤት ብቻ ለአለም ምርጥ አትሌትነት ከመጀመሪያዎቹ አስር የሴት አትሌቶች ጋር መመረጧ ለአትሌቷ መልካም የሚባል ዜና ነው። ከእርሷ ጋርም ኬንያዊቷ የ5000ሜ ሻምፒዮን ሔለን ኦቢሪ ትገኛለች። ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰመንያም ተመርጣለች።

በወንዶች በቅርቡ ሩጫም ያቆመው ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ንጉስ ዩሴን ቦልት ከምርጥ አስር የአመቱ አትሌቶች ውስጥ አለመገኘቱ ትኩረት ስቧል። አትሌቱ በለንደኑ የአለም ሻምፒዮና በ100 ሜትር የነሐስ ሜዳልያ ሲያገኝ፤ 4በ100 ሜትር የዱላ ቅብብል ውድድሩ ላይ በገጠመው ጉዳት ሩጫውን ማቋረጡ ይታወሳል።

ከቦልት የበለጠ ደግሞ አሜሪካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ጀስቲን ጋትሊን በመጀመሪያዎቹ አስር ምርጥ የአለማችን የወንድ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ አለመካተቱ አስገራሚ ሆኗል። ጋትሊን በለንደኑ የአለም ሻምፒዮና ባልተጠበቀ ሁኔታ ዩሴን ቦልትን በማሸነፍ የመነጋጋሪያ ርዕስ እንደነበር ይታወሳል። ደቡብ አፍሪካዊው የ400ሜትር ሯጭ ዋይዴ ቫን ኑክሩክ፣ እንግሊዛዊው ሞሀመድ ፋራህ፤ ኬንያዊው ኤልጃህ ማናንጎይ እና አሜሪካዊው ክርስቲያን ቴይለር ከአስሩ አትሌቶችመካከል ይገኙበታል።

የመጨረሻ ሶስት እጩዎችን ለመምረጥ ሶስት አካላት የሚሰጡት ድምጽ ከግምት ውስጥ ይገባል። ይኸውም የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ካውንስል 50 በመቶ፤ የማህበሩ ቤተሰብ የሚባሉት አባል ፌዴሬሽኖችና የኮሚቴ አባላት 25 በመቶ፤ የህዝብ ምርጫ 25 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል። የህዝብ ድምጽ መስጠት በዚህ ሳምንት በማህበሩ ድረ ገጽ በኦንላይን ማህበራዊ ገጾች አማካኝነት ነው።

ድምጽ የሚሰጥበት ቀን ኦክቶበር 16 ያበቃል። በቀጣይም በሁለቱም ጾታ የመጨረሻ ሶስት እጩዎች ኦክቶበር 16 የሚታወቁ ይሆናል። የ2017 የአመቱ ምርጥ የሴት እና የወንድ አትሌት አሸናፊም ኖቬምበር 24 የአትሌቲክስ ማህበሩ በሚያዘጋጀው የሽልማት መድረክ ላይ የሚታወቅ ይሆናል።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
134 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 959 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us