የብሔራዊ ቡድኑ ሽንፈት በወዳጅነት ጨዋታም ቀጥሏል

Wednesday, 11 October 2017 13:44


ከ2018 የቻን ውድድር ውጭ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሞሮኮ ተጉዞ ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 4ለ0 መሸነፉ ተነግሯል። የወዳጅነት ጨዋታው ለኢትዮጵያ ምንም የሚሰጠው ጥቅም ባለመኖሩ ቅሬታዎች ፈጥሯል።
በአፍሪካ ሊግ ውስጥ ብቻ የሚጫወቱ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ብቻ የሚገኙበት ብሔራዊ በድኖች የሚወዳደሩበት የአፍሪካ ሀገሮች ዋንጫ (ቻን) የ2018 የውድድር መርሀ ግብር ከሶስት ወሮች በኋላ እንደሚካሔድ ይጠበቃል። ለውድድሩ ማለፍ የተሳነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ የሚፈልጉት ሆኗል። ለውድድሩ ያለፈው የሞሮኮ የቻን ቡድንም የአትዮጵያ ቡድንን በወዳጅነት ጨዋታ ገጥሞ 4ለ0 አሸንፏል።


ከኢትዮጰያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ራሳቸውን ለማግለል ማመልከቻ አስገብተዋል የተባሉት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በወዳጅነት ጨዋታም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል። ማክሰኞ እለት ከሞሮኮ ጋር ይካሔዳል ተበሎ በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ሰኞ እለት ተከናውኖ 4ለ0 መሸነፋቸው ነው የተሰማው። የአሰልጣኙ የመጨረሻዎቹ ቆይታ ሳያምር ብሔራዊ ቡድኑም አንድም ተስፋ ሰጪ ነገር ሳያሳይ ቀርቷል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከየትኛውም አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ውድድሮች ውጭ በሆነበት ወቅት ላይ ለወዳጅነት ጨዋታ በተጠራበት ቦታ ሁሉ እየሔደ ሽንፈት የሚከናነብ ብሔራዊ ቡድን መሆኑ የስፖርት ቤተሰቡን አስቆጥቷል። ከሞሮኮው ጨዋታ በፊትም በቅርቡ ለቦትስዋና የነጻነት ቀን ከሐገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታም እንዲሁ መሸነፉ የሚታወስ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
80 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 100 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us