ሁለት አፍሪካውያን ለኮከብነት ከ30ዎቹ እጩዎች መካከል ተካተዋል

Wednesday, 11 October 2017 13:50


ለአለም ኮከብ ተጫዋችነት ከተመረጡ 30 የአለማችን እግር ኳስ ተጫዋች መካከል ሁለት አፍሪካውያን ብቻ ይገኛሉ። እነርሱም ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ እና የጋቦኑ ፒየር ኢሜሪክ አቡሜያንግ ናቸው። ክርስቲየኖ ሮናልዶ ዘንድሮም የሽልማቱ አሸናፊ እንደሚሆን ተገምቷል።
ፍራንስ ፉትቦል መጽሔት ከፊፋ ጋር በጥምረት የሚያከናውኑት የአመቱ ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች ሽልማት ባለን ዶ ኦር የመጀመሪያዎቹ 30 ዕጩዎች ዝርዝር ይፋ ሆኗል። ከሰላሳዎቹ እጩዎች መካከልም በጀርመን ቡንደስሊጋ ምርጥ ብቃት እያሳየ የሚገኘው የቦርሲያ ዶርትሙንዱ አጥቂ ፒየር ኢሜሪክ አቡሜያንግ አንደኛው ነው። በሊቨርፑል ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ደግሞ ሁለተኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ነው።


ከሰላሳዎቹ እጩዎች መካከል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱ ስድስት ተጫዋች የሚገኙ ሲሆን፤ እንግሊዛዊው የቶተንሀም ስፐርስ አጥቂ ሀሪ ኬን ይገኝበታል። የ24 አመቱ አጥቂ በ2017 የውድድር ዘመን በ43 ጨዋታዎች 37 ግቦችን በማስቀጠር አድናቆትን ማግኘት ችሏል።
በስፔን ላ ሊጋ እና በፓርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ውጤታማ ጊዜ ያሳለፈው የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለሽልማቱ ከፍተኛ ግምት አግኝቷል። ከባርሴሎናው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ ጋርም እስክ መጨረሻው ዙር ድረስ ፉክክር እንደሚገጥመውም ይጠበቃል።
ሮናልዶ የባሎን ደ ኦር ሽልማትን አራት ጊዜ የማሸነፍ የተሸለመ ሲሆን፤ ዘንድሮ ካሸነፈ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር አምስት ጊዜ በማሸነፍ እኩል ክብረወሰኑን የሚጋራ ይሆናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
95 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1028 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us