የግብጽ ፕሬዝዳንት ለእያንዳንዱ ተጫዋች 85ሺ ዶላር ሸለሙ

Wednesday, 11 October 2017 13:54


በሩስያ ለሚከናወነው የ2018 የአለም ዋንጫ ማለፉን ያረጋገጠው የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ድል የሀገሪቱን ህዝብ እጅጉን አስፈንጥዟል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትም ለእያንዳንዱ ተጫዋች 85 ሺ ዶላር ሽልማት አበርክተዋል።
ለ2018 የሩስያ አለም ዋንጫ አጣብቂኝ ውስጥ የነበረው የግብጽ ብሔራዊ ቡድን እሁድ ዕለት በአስገራሚ ሁኔታ ማለፍ ችሏል። ብሔራዊ ቡድኑ ከኮንጎ ብራዛቪል ጋር ያደረገውን የማጣሪያ ጨዋታ በኮንጐዎች ቀዳሚ ግብ 1ለ0 ሲመራ ቆይቶ በሊቨርፑሉ አጥቂ ሁለት ግቦች አማካኝነት አሸንፏል።


በአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ሄክቶር ኩፐር የሚመራው የግብጽ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለፊፋ የአለም ዋንጫ ከሰላሳ አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መብቃቱ የሀገሪቱን ህዝብ በሙሉ አስፈንድቋል። ግብጻውያን በሀገሪቱ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመውጣት ደስታቸውን በጭፈራ ገልጸዋል። ይህ አስደሳች ውጤት በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ለቆየችው ግብጽ ህዝቦቿ ወደ አንድነት የሚያመጣ መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተነግሯል።


ግብጽ በአለም ዋንጫ መድረክ ከ1990 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማለፏ ያስደሰታቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ለእያንዳንዱ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች 85ሺ ዶላር ጉርሻ ሸልመዋል። ለብሔራዊ ቡድኑ ድል ከፍተኛ ሚና የነበረው መሀመድ ሳላህንም አድንቀዋል።
‹‹በሁሉም የብሑራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች እጅጉን ኮርቻለሁ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ወሳኟን የፍጹም ቅጣት ምት በማስቆጠርም ጭምር ለቡድኑ ውጤት የላቀ ሚና ለተጫወተው መሐመድ ሳላህ አድናቆት አለኝ›› ብለዋል።


የሊቨርፑሉ አጥቂ መሐመድ ሳላህ በበኩሉ ‹‹ግብጽን ከ28 አመት በኋላ ወደ አለም ዋንጫ መድረክ በመምራታችንና ከ100 ሚሊየን በላይ ለሆነው ለግብጽ ህዝብ ኩራት በመሆናችን እጅጉን ተደስቻለሁ›› ብሏል።


አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ሄክቶር ኩፐር ደግሞ ‹‹ውብ እግር ኳስ አልተጫወትንም ነገር ግን በጣም አስፈላጊው ነገር ለአለም ዋንጫው ማለፋችን ነበር። ይህንን በማሳካታችን በጣም ደስ ብሎኛል›› ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
105 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1053 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us