ጥሩነሽ ዲባባ በቺካጎ ማራቶን የ100ሺ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች

Wednesday, 11 October 2017 13:56

 

የአለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ጥሩነሽ ዲባባ በቺካጎ ማራቶን የ100ሺ ዶለር ሽልማት አግኝታለች። በወንዶች አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ ማሸነፉ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ባለፈው እሁድ በአሜሪካኗ ከተማ ቺካጎ የተካሔደውን የማራቶን ፉክክክር በሴቶች ያሸነፈችው ጥሩነሽ ዲባባ የ100 ሺ ዶላር ሽልማት አግኝታለች። ከገንዘቡ በላይም ውድድሩን ማሸነፏ ለቀጣይ የጎዳና ሩጫ ሽግግሯ እጅግ አስፈላጊ ውጤት መሆኑን ተናግራለች። በወንዶች ደግሞ ያልተጠበቀው አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ አሸናፊ መሆኑ መነጋገሪያ ሆኗል።


አመታዊው የቺካጎ ማራቶን እሁድ እለት በከፍተኛ የጸጥታ ሀይሎች ታጅቦ በድምቀት ተካሂዷል። በሴቶች መካከል የተካሔደውን ፉክክርም ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ጥሩነሽ ዲባባ አሸንፋለች። ርቀቱንም 2፡18፡31 በሆነ ሰአት ነው ያጠናቀቀችው።
ከጥሩነሽ በተጨማሪ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷት የነበረችውና የውድድሩ የሁለት ጊዜ አሸናፊ ኬንያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት አቋርጣ ወጥታለች። ሌላዋ ኬንያዊት አትሌት ብሪጊድ ኮስጌ ከጥሩነሽ ሰአት ከሁለት ደቂቃ በላይ ዘግይታ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ስታገኝ፤ አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሀሴይ ሶስተኛ ሆና መግባቷ አድናቆት አሰጥቷታል።


ከ2017 የለንደን የአለም ሻምፒዮና መልስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወዳደረችው ጥሩነሽ ውድድሩን ያሸነፈችበት ብቃት አድናቆት የሚያሰጣት ነው። በተለይም የመጨረሻዎቹን አምስት ኪሎ ሜትሮች ብቻዋን እየመራች በመሮጥ ነው ያጠናቀቀችው። በውድድሩ የቅርብ ተፎካካሪዋ ሆና የቆየችው ብሪጊድ ኮስጌን ለመቅደም የትራክ ላይ የረጅም ጊዜ ሯጭነቷ ጠቅሟታል።


ጥሩነሽ ለሶስተኛ ጊዜ በተወዳደረችበት የማራቶን ርቀት ያስመዘገበችው የአሸናፊነት ውጤት በቀጣይም በርቀቱ ውጤታማ ልትሆን እንደምትችል የሚያስረዳ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን የተወዳደረችው በ2014 የለንደን ማራቶን ሲሆን፤ በወቅቱም ርቀቱን 2፡20፡35 በማጠናቀቅ የሁለተኛነት ደረጃን ማግኘቷ ይታወሳል።


ሁለተኛው የማራቶን ፉክክሯ ደግሞ በ2017 የለንደን ማራቶን ሲሆን፤ በወቅቱም ሁለተኛ ሆና ነበር ያጠናቀቀችው። ርቀቱን የጨረሰችበት 2፡17፡01 ሰአትም የኢትዮጵያ ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።


እሁድ እለት ለሶስተኛ ጊዜ በተፎካከረችበት የማራቶን ፉክክር ያለ አሯሯጭ አሸናፊ መሆኗ እጅጉን እንዳስደሰታት ጥሩነሽ በሰጠችው አስተያየት ተናግራለች። ውጤታማ እንድትሆን ከፍተኛ እገዛ ላደረጉለት ለቤተሰቦቿና ለውድድሩ አዘጋጆች ምስጋናዋንም አቅርባለች።


በተመሳሳይ መድረክ በወንዶች የተካሔደውን ፉክክር አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ ማሸነፉ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ኬንያውያን ለአሸናፊነት በሚጠበቁበት ውድድር በዶፒንግ ተጠርጥረው ምርመራ ላይ በሚገኙት አሜሪካዊው አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የሚሰለጥነው ጋለን ሩፕ ርቀቱን 2፡09፡20 በማጠናቀቅ ማሸነፍ ችሏል። አትሌቱ ውድድሩን ማሸነፉ የአልቤርቶ ሳላዛርሀ የዶፒንግ ተጠርጣሪነት ጉዳይ እንደገና የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
108 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 99 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us