የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ወደ ሞሮኮ ገብቷል

Wednesday, 08 November 2017 19:29

 

ባለፉት አመታት የግብጽና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ክለቦች እየተፈራረቁ ሲቀባበሉት የነበረው የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ወደ ሞሮኮ ገብቷል። 2.5 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ የሚያደርገውን የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ የሞሮኮው ዋይዳድ ካሳብላንካ ማንሳት ችሏል። ውጤቱ ሞሮኮ ለ2018 የአለም ዋንጫ ቅዳሜ ከኮትዲቯር ጋር የምታደርገውን ጨዋታ እንድታሸንፍ የሚያነሳሳ ሆኗል።


የካፍ ቻምፒየንስ ሊጉ ፍጻሜ ሁለቱን የሰሜን አፍሪካ ክለቦች የግብጹን አል አህሊ እና የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካን ያገናኘ ነበር። በመድረኩ ከፍተኛ የአሸናፊነት ልምድና ታሪክ ያለው አል አህሊ ለስምንተኛ ጊዜ ያሸንፋል ተብሎ የተሰጠው ግምት ሳይሰምር ቀርቷል። በመጀመሪያው ጨዋታ 1ለ1 ተለያይተው የነበረ ሲሆን፤ እሁድ እለት በሁለተኛው የፍጻሜ ጨዋታ ካሳብላንካ በሜዳው 1ለ0 አሸንፎ በድምሩ 2ለ1 በሆነ የደርሶ መልስ ውጤት በውድድሩ የተሳተፎ ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።


የቻምፒየንስ ሊጉ ዋንጫ በካሳብላንካ አማካይነት ወደ ሞሮኮው ክለብ ሲያመራ ከ25 አመት በኋላ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት በ1999 እ.አ.አ. የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ያነሳው የሞሮኮ ክለብ ራጃ ካሳብላንካ የተባለው ነበር።


ሞሮኮና ዲሞክራቲክ ኮንጎ እኩል ስድስት ጊዜ የቻምፒየንስ ሊጉ ዋንጫ ወደቤታቸው በማስገባት ታሪክ ተጋርተዋል። ግብጽ 14 ጊዜ ዋንጫው ያረፈባት ሀገር በመሆን ክብረወሰኑን ይዛለች።


ዋይዳድ ካሳብላንካ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ በመሆኑ ከአንድ ወር በኋላ በዩናይትድ አረብ ኢምሬት በሚካሔደው የፊፋ የአለም የክለቦች ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ ይወዳደራል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
77 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 896 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us