የ2010 ዓ. ም. ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጀምሯል

Wednesday, 08 November 2017 19:32

የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2010 ዓ.ም. መርሀ ግብር ቅዳሜ እለት ተጀምሯል። አንዷለም ንጉሴ የመጀመሪያዋን የሊገጉ ግብ ለወልዲያ ያስቆጠረ ተጨዋች ሆኗል። 

 

ሶስት አዳዲስ ክለቦችን ጨምሮ አስራ ስድስት ክለቦች የሚሳተፉበት የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀግብር ቅዳሜ እለት በተለያዩ የክልል ስታዲየሞች በተካሔዱ ጨዋታዎች ተጀምሯል።


የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታዎች በክልል ስታዲየሞች የተካሔዱ ሲሆን፤ አዳማ ከተማን ያስተናገደው ወልዲያ ከነማ 2ለ0 አሸንፏል። አንዷለም ንጉሴ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ የመጀመሪያዋ የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያዋ ግብ ሆና ተመዝግባለች።
ሌላው በሜዳው ድል የቀናው የሊጉ አዲስ ክለብ ጅማ አባጅፋር ነው። ጅማ አባጅፋር ሐዋሳ ከተማን ሁለት ለዜሮ ማሸነፍ ችሏል።


በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የትግራይ ክልል ሁለት ተወካዮች ያገኘ ሲሆን፤ ሁለቱም ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸው አቻ በመለያየት ነው የጀመሩት። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከፋሲል ከነማ ሁለት ለሁለት፤ መቀሌ ከተማ ደግሞ በሜዳው ከአርባምንጭ ከተማ ያለግብ ተለያይተዋል።


ፕሪሚየር ሊጉ ሰኞ እለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ደደቢትና ወላይታ ዲቻ ባደረጉት ጨዋታ ቀጥሎ የተካሔደ ሲሆን፤ ያለምንም ግብ ነው የተጠናቀቀው። እሁድ እለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ የተጫወተው አጥቂው ጌታነህ ከበደ በማግስቱም ለደደቢት በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ተካቶ ተጫውቷል።

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 98 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us