የምርጫው ጉዳይ ያለየለት የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 30 ቀን ይካሔዳል

Wednesday, 08 November 2017 19:33

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 30 ቀን በአዲስ አበባ ለማካሔድ የያዘውን መርሀግብር ሊራዘም እንደሚችል ሲነገር ቢቆይም ፌዴሬሽኑ ጉባኤው በተያዘለት ቀን ይከናወናል ብሏል። የስራ የአመራሮች ምርጫ ጉዳይ ግን እስካሁን በይፋ አለየለትም። ምርጫውን በተመለከተ ጠቅላላ ጉባኤው ሊወስን እንደሚችል ይጠበቃል።


የአለምአቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) ሰሞኑን በላከው ደብዳቤ ላይ በአቶ ጁነዲን ባሻ የሚመራው ፌዴሬሽን በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሊያካሒድ ያሰበው ምርጫ ትክክለኛውን የምርጫ ሒደት ያልተከተለ መሆኑን ጠቅሶ ምርጫውን እንዲያራዝም አሳስቧል። ለዚህም ደግሞ ፌዴሬሽኑ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ገለልተኛ የሆነ አስመራጭ ኮሚቴ ሳይቋቋምና እጩዎች ከአንድ ወር በፊት በይፋ ሳይተዋወቁ ለውድድር መቅረባቸው፤ ፌዴሬሽኑ ለፕሬዝዳንትና ስራ አስፈጻሚነት አንድ አንድ ተወካይ ብቻ ላኩ ማለቱ የምርጫውን ፍትሀዊነት ጥያቄ ውስጥ ከከተቱት እግሮች መካከል ይጠቀሳሉ።


ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለማስተካከልም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ የምርጫው ጊዜ እንዲራዘም ነው ፊፋ ያሳሰበው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደግሞ የፊታችን ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ሊያካሒድ ያሰበው ጠቅላላ ጉባኤ ለሌላ ጊዜ እንደማይዛወር አስታውቋል። ጠቅላላ ጉባኤው እንደሚካሔድና ጉባኤው የስራ አመራሮች ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ነው የሚጠበቀው። ስለዚህም ምርጫው በእርግጥም የሚካሔድ ስለመሆኑ ከወዲሁ መናገር አልተቻለም። ምርጫው ቢካሔድም ባይካሔድም ጠቅላላ ጉባኤውና ውሳኔዎቹ በቀጣይ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ለውዝግብ የሚዳርገው ውጤት እንደሚያስከትልም መገመት ይቻላል።


ፌዴሬሽኑን በፕዝዳንትነት ለመምራት አምስት ክልሎች ተወካዮቻቸውን ማሳወቃቸው ይታወቃል። ባለፉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ጁነዲን ባሻ በድጋሚ ድሬደዋን ወክለው ይወዳደራሉ። የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተካ አስፋው ከአማራ ክልል፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከደቡብ ክልል፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች አንተነህ ተስፋዬ ከኦሮሚያ እንዲሁም አቶ ዳግም ሞላሽን ከጋምቤላ ለፕሬዝዳንትነት ይፈካከራሉ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
56 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1060 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us