የኢትዮጵያ ቡድን የቻን እድሉን አጨልሟል

Wednesday, 08 November 2017 19:34

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ 2018 የቻን ዋንጫ የሚመለስበት እድል በድጋሚ ቢያገኝም በሜዳው ከሩዋንዳ ጋር ባደረገው ጨዋታ ደጋፊዎቹን ተስፋ ያስቆረጠ ውጤት አስመዝግቧል። ተደጋጋሚ ሽንፈት እያስተናገዱ የሚገኙት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ህዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል። የአጥቂዎች ችግር ከአቅሜ በላይ ነው ብለዋል።


በየአፍሪካ ሊግ ውስጥ ብቻ የሚጫወቱ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የቻን ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ሆኖ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብጽ አልሳተፍም ማለቷን ተከትሎ በድጋሚ እድል ከሩዋንዳ ጋር ማግኘቱ ይታወቃል። ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በደርሶ መልስ ጨዋታ አሸናፊ ሆነው ወደ ቻን የሚመለሱበትን እድል ካፍ ፈጥሮላቸዋል። የሁለቱ ሀገሮች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖችም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን እሁድ እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም አድርገዋል። በጨዋታውም ባለሜዳው ቡድን ሁለት ጊዜ ግብ አስቆጥሮ እየመራ ቆይቶ ሶስት ግብ አስተናግዶ ሽንፈት ደርሶበታል። በቀጣዩ እሁድ የመልስ ጨዋታ የተሻለ ውጤት እንደማያስመዘግብ በማሰብ ደጋፊው ተስፋ ቆርጧል። በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታው ከመጠናቀቁ በፊት ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል።


በጨዋታው የ2009 የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው ጌታነህ ከበደን ያካተተው ቡድን ተጋጣሚው ላይ ግቦችን ማስቆጠር አልቻለም። ቡድኑ በማጥቃት ብቻ ሳይሆን በመከላከልም እጅግ ደካማ ነበር። ለተቆጠሩበት ግቦችም ተከላካዮቹና ግብ ጠባቂው የፈጠሩት ስህተት የላቀ ድርሻ አለው።


ብሔራዊ ቡድኑን ከተረከቡ ጀምሮ ያልተሳካላቸው አሰልጣኝ አሸናፊ በተጫዋች ምርጫና ከጨዋታ ታክቲክ ጋር በተያያዘ የመረጡት ውሳኔ አሁንም ለሽንፈት ዳርጓቸዋል። በተለይም በቅርቡ የአመቱ ምርጥ የፕሪሚየር ሊጉ ግብ ጠባቂ ተብሎ የተሸለመውን አቤል ማሞን ትተው የኢንተርናሽናል ጨዋታ ልምድ የሌለውን ለአለም ብርሃኑን መምረጣቸው አስገራሚ ውሳኔ ነበር። ግብ ጠባቂው ለአለም ሁለት ጊዜ የተሞከሩበትን ኳሶች በእጁ ከተቆጣጠረ በኋላ በዝንጉነት ለቋቸው ነበር ሩዋንዳዎች ከመረቡ ላይ ያሳረፉበት።


ከጨዋታው በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን አስተያየት የሰጡት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የግብ ጠባቂያቸው ድርጊት አስቂኝ ሆኖባቸዋል። ስለ ግብ ጠባቂው ስህተቶች ሲጠየቁ ሳቃቸውን ከጨረሱ በኋላ ‹‹እሱ የእኔ ጥፋት ነው›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።


በአጠቃላይም ቡድኑ ላስመዘገበው ደካማ ውጤት ኃላፊነት በመውሰድ የኢትዮጵያ ህዝብንም ይቅርታ ጠይቀዋል። በእለቱ ጨዋታ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ማየት ያልቻለው የእግር ኳስ አፍቃሪ ግን ከይቅርታው ይልቅ በመልሱ ጨዋታ ወደ ቻን ዋንጫ ማለፍ የሚችልበትን ውጤት እንዲያስመዘግቡ አጥብቆ ይፈልጋል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ቻን ዋንጫ ለማለፍ የፊታችን እሁድ ከሩዋንዳ ጋር የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ላይ ከሁለት በላይ ግቦችን ማስቆጠር ይኖርበታል።


የ2016 የቻን ዋንጫ አዘጋጅ የነበረችው ሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድኗ ከሜዳው ውጪ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ለሞሮኮው የቻን መድረክ ለማለፍ ሰፊ እድል ነው ያለው። ቡድኑ በመልሱ ጨዋታ ያለግብ አቻ ቢለያይ ወይም 1ለ0 ተሸንፎ እንኳ ማለፍ ይችላል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
83 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1052 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us