አልማዝ አያና በድጋሚ ለኮከብነት ታጭታለች

Wednesday, 08 November 2017 19:36

 

ባለፈው አመት የአለማችን ምርጥ የሴት አትሌት ተብላ የተሸለመችው አልማዝ አያና ዘንድሮም ለሽልማቱ ከተመረጡ ከመጨረሻዎቹ ሶስት እጩዎች መካከል አንዷ ሆናለች። ከሶስት ሳምንት በኋላ የአመቱ ምርጥ የሴትና የወንድ አትሌት አሸናፊዎች ይታወቃሉ።

 

አለምአቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የ2017 ምርጥ አትሌቶችን ለመለየት ያከናወነው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ውጤትን አሳውቋል። በሴቶች ከአስር እጩዎች መካከል ብቸኛዋ የኢትዮጵያ አትሌት ሆና የቀረበችው አልማዝ አያና ለመጨረሻው ዙር ምርጫ ካለፉ ሶስት አትሌቶች ተርታ ለመሰለፍ ያበቃትን ውጤት አግኝታለች።


የአለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮና አልማዝ አያና በ2017 የውድድር አመት በጉዳት ብታሳልፍም በለንደኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነበር የተወዳደረችው። በመድረኩም በ10.000 ሜትር የወርቅ፤ እና በ5.000 ሜትር የብር ሜዳልያ ማስመዝገቧ ይታወሳል። በ10.000 ሜትር የተለየና ድንቅ አሯሯጥ ክህሎቷ ያስመዘገበችው ድል ደግሞ ከፍተኛ አድናቆትን አሰጥቷል። ለዘንድሮው የአለም ምርጥ አትሌትነትም ከሶስቱ እጩዎች አንዷ እንድትሆን አስችሏታልም።


ባለፈው አመት የ2016 የአመቱ ምርጥ የሴት አትሌት ተብላ የተሸለመችው አልማዝ ዘንድሮ በመጨረሻው ዙር ምርጫ ከጀርመኗ እና ከቤልጂሟ አትሌት ጋር ትፎካከራለች። አሸናፊ ከሆነች ደግሞ ከኢትዮጵያም ሆነ ከአፍሪካ በተከታታይ ለሁለት ጊዜ የአለም ምርጥ የሴት አትሌት በመባል የተሸለመች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ትናለች።


በአለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር የሚሰጠውን የአለም ምርጥ አትሌት ሽልማትን ከዚህ በፊት ከኢትዮጵያ በሴቶች መሰረት ደፋር ብቻ ያሸነፈች ሲሆን፤ በወንዶች ደግሞ የሽልማቱን ክብር አግኝተው የሚያውቁት ሀይሌ ገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለ ናቸው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
96 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1002 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us