አሳዛኙ የጣሊያንና የቡፎን ስንብት

Wednesday, 15 November 2017 13:12

 

ያልተጠበቁ ክስተቶች የሚስተናገዱበት የእግር ኳሱ መድረክ በሳምንቱ መጨረሻ ለጣሊያን ብሔራዊ ቡድንና ደጋፊዎች አሳዛኝ የሆነ ዜና የተፈጠረበት ነበር። የአለም ዋንጫ አንደኛዋ ቀለም ሆና የዘለቀችው ጣሊያን በቀጣዩ አመት በሩስያ በሚካሔደው የአለም ዋንጫ መድረክ መቅረቷ እርግጥ ሆኗል። የብሔራዊ ቡድኑ ማገር ሆኖ ለሀያ አመታት ያገለገለው ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ቡፎንም በጣሊያን መለያ የማናየው ተጨዋች መሆኑ ታውቋል።

ጣሊያን ሰኞ እለት ከስዊድን ጋር በአደረገቸው የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ ከአለም ዋንጫው መቅረቷን ያረጋገጠ ውጤት አስመዝገባለች። የእለቱ ጨዋታ ያግብ የተጠናቀቀ ቢሆንም ቀደም ሲል ስዊድን ያስመዘገበችው የ1ለ0 ድል ወደ አለም ዋንጫ እንድታልፍ አስችሏታል።

በአለም ዋንጫ መድረኮች ተደጋጋሚ የተሳትፎ ታሪክ ያላት ጣሊያን እ.ኤ.አ. ከ1958 በኋላ ከመድረኩ ስትርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በአለም ዋንጫ የተሳትፎ ታሪኳ ደግሞ ለውድድሩ ማለፍ ሳትችል የቀረችው ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ቀደም ሲል ለአለም ዋንጫ ማለፍ ያልቻለችበት አጋጣሚ የተፈጠረው እ.አ.አ. በ1930 የመጀመሪያው አለም ዋንጫ መድረክ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ።

በሳንሲሮ ስታዲየም የተደረገው የጣሊያንና ስዊድን ጨዋታ ያለ ግብ ከተጠናቀቀ በኋላ ሁሉም የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ሜዳ ውስጥ ተንበርክከው ሲያለቅሱ ታይተዋል። በስታዲየሙ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋዎቻቸውም ፊተቸው በእንባ ታጥቦ ነበር። ቅስም የሚሰብረው ይህ ውጤትም የወቅቱ የእግር ኳሱ መነጋገሪያ ሆኗል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን የረጅም ጊዜ ግብ ጠባቂ የሆነው ጂያንሉጂ ቡፎን ከኢንተርናሽናል ጨዋታ ማግለሉን ይፋ አድርጓል። ቡፎን ጣሊያን ከአለም ዋንጫ መቅረቷን ተከትሎ ሜዳ ውስጥ ሲያነባ ነበር።

አንጋፋው ግብ ጠባቂ የሳንሲሮ ሜዳን ብቻ ሳይሆን የጣሊያን ቡድንንም ነበር በእንባ የተሰናበተው። ከእንግዲህም የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን መለያን ለብሶ ለሀገሩ እንደማይጫወት በይፋ ተናግሯል። የውድድር አመቱ ሲጠናቀቅም የእግር ኳስ ህይወቱ የሚያበቃ መሆኑንም ጨምሮ አስታውቋል።

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት ሲመራ የቆየው የ39 አመቱ ግብ ጠባቂ ለሀገሩ ላለፉት 20 አመታት በ175 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ችሏል። ጣሊያን የ2006 የአለም ዋንጫን ስታነሳም ወሳኝ ከነበሩ ተጫዋቾች መከከል አንዱ ነበር።


 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
76 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 98 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us