ለ2018የአለም ዋንጫ የሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ብልጫ ወስደዋል

Wednesday, 15 November 2017 13:15

 

በቀጣዩ አመት ሩስያ ለምታስተናግደው የ2018 የፊፋ አለም ዋንጫ መድረክ ለማለፍ በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገሮች የማጣሪያ ጨዋታዎች ተደርገዋል። የአፍሪካ አህጉርን ወክለው ለመሳተፍ ከሚፎካከሩ ሀገሮች መካከልም የሰሜን አፍሪካ ቡድኖች የበላይነት ታይቷል። የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ሀያልነት አሁንም በሰሜን አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች ሆኖ ቀጥሏል። ምስራቅ አፍሪካ ደካማ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ የሚታየበት ቀጠና እንደሆነ ቀጥሏል።

በሳምንቱ መጨረሻ በአፍሪካ የተለያዩ ከተሞች በተከሔዱ የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ሞሮኮና ቱኒዝያ ወደ ሩስያ የሚያስጉዛቸውን ትኬት መቁረጥ ችለዋል። ቀደም ሲል ግብጽ ለአለም ዋንጫው ማለፏን ያረጋገጠች ሀገር መሆኗ ይታወሳል።

በምድብ ሶስት የቅርብ ተፎካካሪ የነበሩት ሞሮኮና አይቮሪኮስት ባደረጉት ጨዋታ በፈረንሳዩ ሐርቨ ሬናልድ የሚመራው ቡድን 2ለ0 አሸንፏል። አሰልጣኙ የቀድሞ ብሔራዊ ቡድናቸው አይቮሪኮስትን ለአፍሪካ ዋንጫ ድል ማብቃታቸው ይታወሳል። በአፍሪካ ምድርም ስኬታማ መሆኑ የቻሉ አውሮፓዊ አሰልጣኝ አድርጓቸዋል። አሰልጣኙ ቀደም ሲል የዛምቢያን ቡድን ይዘው የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳታቸው አይዘነጋም።

ሞሮኮ በምድቧ ባደረገችው ማጣሪያዎች 12 ነጥቦች በመሰብሰብ ቀዳሚ በመሆን ወደ አለም ዋንጫ ያለፈች ሲሆን፤ በምድቡ የሚገኙት አይቮሪኮስት፣ ጋቦንና ማሊ ከምድባቸው ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ቅዳሜ እለት በሜዳዋ ሊቢያን ያስተናገደችው ሌላዋ የሰሜን አፍሪካ ቡድን ቱኒዝያ ወደ ሩስያ የአለም ዋንጫ ያሳለፋትን ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። ቱኒዝያ በእለቱ ከሊቢያ ጋር ያለምንም ግብ የተለያየች ቢሆንም ነጥቧን 14 በማድረስ ከምድቡ አናት ላይ መቀመጥ ችላለች። ወደ ሩስያም ማለፍ የቻለች የሰሜን አፍሪካ ሀገር ሆናለች።

በምድቡ ዲሞክራክ ኮንጎ በመብለጥ ወደ አለም ዋንጫ ያለፈችው ቱኒዝያ በአፍሪካ ምድር ያሳየችውን የበላይነት በመጠቀም በአለም ዋንጫም ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምትሆን ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷታል። በ2018 የአለም ዋንጫ ለአምስተኛ ጊዜ በሚኖራት ተሳትፎ ከምድቧ ከማለፍ በላይ ውጤት እንደምታስመዘግብ የቡድኑ አባላት ተናግረዋል። ቱኒዝያ ለመጨረሻ ጊዜ በአለም ዋንጫ የተሳተፈችው በ2006 የአለም ዋንጫ እንደነበረ ይታወሳል።

ግብጽ ቀደም ሲል ለሩስያው የ2018 የአለም ዋንጫ ማለፋቸውን ካረጋገጡ ሀገሮች መካከል አንዷ መሆኗ ይታወሳል። ባለፈው እሁድ የምድቧን የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ አድርጋ ያለ ምንም ግብ ተለያይታለች። ባላፉት ሶስት የአለም ዋንጫ መድረኮች ላይ በተከታታይ የተሳተፈችው ጋና ከምድቧ ሁለተኛ በመሆን ወደ ሩስያ መሔድ ሳትችል ቀርታለች።

በሌሎች የአለም ዋንጫ ማጠሪያ ጨዋታዎች ሴኔጋልና ናይጄሪያ አፍሪካን የሚወክሉ ሀገሮች መሆናቸውን ያረጋገጡበትን ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። በሳዲዮ ማኔ የሚመራው የሴኔጋል ቡድን ከ1998 በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ ሲመለስ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ጋር ባደረገው የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ከ16 አመት በኋላ ወደ አለም ዋንጫ መድረክ የተመለሰበትን ወሳኝ ውጤት አስመዝግቧል።

ቅዳሜ እለት ከአልጄሪያ ጋር 1ለ1 የተለያው የናይጄሪ ብሔራዊ ቡድን ለሩስያ የአለም ዋንጫ ማለፉ ደጋፊዎቹን አስፈንድቋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
96 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 961 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us