የትግራይ ክልል ፌዴሬሽን ተወካዩን ማንሳቱን አስታወቀ

Wednesday, 15 November 2017 13:19

 

የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለፉት አራት አመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ያገለገሉትና በቀጣዩ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የተዘጋጁትን የአቶ ተክለወይኒ አሰፋን ውክልና ማንሳቱን በይፋ አስታወቀ። አቶ ተክለወይኒ ያልተገባ ንግግር በማድረጋቸው ለፈጸሙት ጥፋት ይቅርታ ጠይቀዋል።

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ምርጫ ጋር ተያይዞ በአወዛጋቢ አስተያየቶቻቸው የሚጠቀሱት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ፤ በፌዴሬሽኑ ውስጥ የነበራቸውን የክልላቸውን ውክልና አጥተዋል። የእሳቸው ሚና ቁልፍ በነበረበት የምርጫ ሒደት ላይም ለውጦች እንደሚፈጠሩ ይጠበቃል።

ባለፈው ሰኞ በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለአቶ ተክለወይኒ አሰፋ የሰጠውን ውክልና ማንሳቱን አስታውቋል። ለዚህም ደግሞ ዋንኛ ምክንያት ግለሰቡ በሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሀንና በጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሰጧቸው አስተያየቶች ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው።

አቶ ተክለወይኒ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ጣቢያ የስርፖርት ፕሮግራም ላይ በነበራቸው የሥልክ ቃለ ምልልስ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ስፖርት የሰጡት አስተያየትን በመቃረን ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። ምላሻቸው ላይም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ክብር የሚነኩ ያልተገቡ ቃላቶቸን መጠቀማቸው ለትችት ዳርጓቸዋል። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻን በተመለከተም ንቀት የተሞላበትና ዘለፋም የታከለበት አስተያየት መስጠታቸው ለተጨማሪ ወቀሳ ተዳርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሰሞኑን የጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተናሩት ንግግር የሴቶችን ክብር በተለይም የመጡበትን የትግራይ ክልል ሴቶችን ሰብዕና የሚያቀል መሆኑ አቶ ተክለወይኒ ውክልናቸውን እንዲያጡ አድርጓቸዋል።

አቶ ተክለወይኒም የቀረበባቸውን ቅሬታና ወቀሳ ተከትሎ ሀሳበቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ያልተገባ ንግግር በመናገራቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ውክልናውን ማንሳቱን በጸጋ እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
86 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 97 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us