አስመራጭ ኮሚቴ ሳይመርጥ የተጠናቀቀው ጉባኤ

Wednesday, 15 November 2017 13:21

 

በርካታ ውዝግቦችን ሲያስተናግድ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 10ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባለፈው ጥቅምት 30 እና ህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተካሒዷል። ጉባኤው የስራ አመራሮች ምርጫን ለሌላ ጊዜ ሲያስተላልፍ፤ ወሳኝ የሆኑ አጀንዳዎች ላይ ሳይወያይና ውሳኔ ሳያሳልፍ መጠናቀቁ ለትችት ዳርጎታል።

ለውስን የመገናኛ ብዙሀን ብቻ በሩን ከፍቶ የተጀመረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ለአንድ ቀን ከግማሽ ተከናውኗል። በእለቱ ጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ ከሰጠባቸው ግዙፍ ጉዳዮች መካከል አንደኛው የስራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ጉዳይ ላይ ነበር። ምርጫው በእለቱ ይካሔድ አይካሔድ በሚሉ ወገኖች መካከል ክርክር ተካሒዷል። በመጨረሻም ጉባኤው ውሳኔ እንዲያስተላልፍ የተደረገ ሲሆን፤ አብዛኛው ድምጽ እንዲራዘም የሚፈለግ ሆኖ ተገኝቷል። ከ45 ቀናት በኋላም በአፋር ክልል እንዲከናወን ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

የፌዴሬሽኑ የስራ አመራሮች ምርጫ እንዲራዘም ካደረጉ ምክንያቶች መካከል የአስመራጭ ኮሚቴ አለመቋቋሙና የዕጩዎች አቀራረብም ህግን የተከተለ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በፊፋ መመሪያ መሰረት የአባል ሀገራት የስራ አመራሮች ምርጫ በሚከናወንበት ጊዜ ገለልተኛ የሆነ አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋም ይኖርበታል። ከሚቴው በጠቅላላ ጉባኤ እውቅና ሲሰጠው ስራዎችን የሚያከናውን ነው።

ለአስመራጭ ኮሚቴውም ከምርጫው ቀናት በፊት እጩዎች ዝርዝር ግለ ታሪክ የሚቀርብ ሲሆን፤ ትክክለኛ እጩ ናቸው ብሎ ሲያምን ለውድድር እንዲያልፉ ያደርጋል። በመሆኑም ይህንን ገለልተኛ አስመራጭ ኮሚቴ ለማቋቋም ሰፊ ቀናትን የሚጠይቅ በመሆኑ ምርጫው እንዲራዘም ተደርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም ለፕሬዝዳንትነትና ስራ አስፈጻሚ አባልነት ክልሎች አንድ አንድ ተወካይ እንዲልኩ በፌዴሬሽኑ የተላከው ደብዳቤ ስህተት በመሆኑ ለምርጫው መራዘም ሌላኛው ምክንያት ሆኗል። በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እጩዎችን የሚያቀርቡ ክልሎች ምን አይነት ገደብ አልተጣለባቸውም። ከአንድ በላይ እጩዎችን መቅረብ የሚችሉበት አማራጭ አላቸው። ይህንን መሰረት በማድረግ በቀጣይ ክልሎች የሚልኳቸው እጩዎችን ቁጥርና ግለሰብ ላይ ለውጥ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አቶ ተካ አስፋው ከአማራ፣ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ከደቡብ፣ የቀድሞው እግር ኳስ ተጨዋች አንተነህ ፈለቀ ከኦሮምያ፣ አቶ ዳግም ሞላሸን ከጋምቤላ እና አቶ ጁነዲን ባሻ ከድሬደዋ ክልል መወከላቸው ይታወሳል።

የስራ አመራሮቹ ምርጫ እንዲራዘም ከፍተኛ ፍላጎት ካሳዩት መካከል አቶ ጁነዲን ባሻ እና አቶ ተካ አስፋው ጠቅላላ ጉባኤው ትክክለኛ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል። ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባልተቋቋመበት ሁኔታ ምርጫ ማካሔድ ተገቢ ስላልሆነ ምርጫው እንዲራዘም መደረጉ ተገቢ እንደሆነ ነው ያስረዱት።

በአንጻሩ ደግሞ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጠቅላላ ጉባኤው ምርጫው እንዲራዘም የወሰነበት ሒደት ደንቡን የጣሰ እንደሆነ ተናግረዋል። መተዳደሪያ ደንቡ በአራት አመት የሚሰበሰበው ጠቅላላ ጉባኤ ፌዴሬሽኑን የሚመሩትን ስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ያከናውናል የሚለው ደንብ በአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤ ተግባራዊ አለመሆኑን ነው የሚጠቅሱት። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
91 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 940 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us