ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ፌዴሬሽን 10ሺ ዶላር ካሳ ይሰጣታል

Wednesday, 22 November 2017 12:42

 

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በጅቡቲና በጋቦን ላይ ቅጣት አስተላልፏል። ሁለቱ ሀገሮች ከቀጣዩ የ2020 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ እንዲሆኑም የታገዱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ 10ሺ ዶላር ካሳ እንደምታገኝ ታውቋል።

ጅቡቲና ጋቦን ራሳቸውን ከ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ በማድረጋቸው ነው ቅጣት የተጣለባቸው። ጅቡቲ በአለም ዋንጫው ከኢትዮጵያ ጋር በአደረገችው ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ በመጀመሪያው ጨዋታ በሜዳዋ 5ለ1 መሸነፏ ይታወሳል። የመልሱን ጨዋታ ሳታደርግ የውስጥ ውድድሬን አጠናክራለሁ በማለት ራሷን ከማጣሪያው ውጭ ማድረጓን አሳውቃ ነበር። የኢትዮጵያ ቡድንም ወደ ቀጣዩ ዙር  በፎርፌ እንዲያልፍ መደረጉ ይታወሳል።

ካፍ ሰሞኑን ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረትም ጅቡቲ ከኢትተጵያ ጋር የነበራትን የመልስ ጨዋታ በመሰረዟ የ10ሺ ዶላር ቅጣት ተጥሎባታል። ገንዘቡም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ካሳ እንዲሆን የሚሰጥ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ጅቡቲ በቀጣይ የቻን ማጣሪያ ላይም እንዳትሳፍ እገዳ ተጥሎባታል።

በተመሳሳይ ጋቦንም በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ጋር የነበራትን ጨዋታ በመሰረዝ ከማጣሪያው መውጣቷን በማሳወቋ የ10ሺ ዶላር ቅጣትና በቀጣዩ የ2020 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እንዳትሳተፍ እገዳ ተጥሎባታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
84 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 96 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us