ኢትዮጵያ በ2018 የዓለም ዋንጫ በአንድ ተወካይ ትሳተፋለች

Wednesday, 22 November 2017 12:44

 

ሩስያ ለምታስተናግደው የ2018 የአለም ዋንጫ ሀገሮች የሚያደርጉትን የማጣሪያ ጨዋታ ተከትሎ ተሳታፊ ሀገሮች እየታወቁ ነው። አፍሪካ በአምስት ሀገሮች ማለትም በግብጽ፣ በቱኒዝያ፣ በሞሮኮ፣ በናይጄሪያና ሴኔጋል የምትወከል ይሆናል። ኢትጵያ ደግሞ በኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ አማካኝነት ብቻ በአለም ዋንጫው ስሟ ይጠራል።

የአለምአቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፊፋ ሰሞኑን የሩስያውን የአለም ዋንጫ የሚዳኙ ባለሞያዎቹን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ዳኛ በአምላክ ተሰማ ስም ይገኝበታል።

በአምላክ ተሰማ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የእግር ኳስ መድረኮች ላይ በመዳኘት ከፍተኛ ልምድ በማካበት ላይ የሚገኝ ባለሞያ ነው። ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በምስጉን ዳኝነቱ የሚጠቀስም ነው። በአፍሪካ ዋንጫ በክለቦችም ታላላቅ መድረኮች ላይ በመዳኘት ከፍተኛ ብቃቱን ማሳየት የቻለ ሲሆን፤ በቅርቡ ከፍተኛ ጫና የነበረበትን የሞከሮኮው የዋይዳድ ካዛብላንካ እና የአል አህሊን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ የመጀመሪያውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት በብቃት መዳኘቱ ይታወሳል።

ለሩስያው የ2018 የፊፋ አለም ዋንጫ ስድስት አፍሪካውያን የተመረጡ ሲሆን፤ በአምላክ ተሰማ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ በመሆን በታላቁ የእግር ኳስ መድረክ ሀገሩን የሚያስጠራ ይሆናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
99 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 893 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us