የኢትዮጵያ የሴካፋ ቡድን ኮከቦቹን አላካተተም

Wednesday, 22 November 2017 12:47

 

በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሔደው የ2017 የሴካፋ ዋንጫ ኢትጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ይፋ ሆኗል። በቡድኑ ውስጥ ኮከብ የሚባሉ ተጨዋቾች አለመካተታቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዳይቋረጥ ይመስላል አሰልጣኙ ከሁለት በላይ ተጫዋቾችን ከክለቦች አልመረጡም። ከአንድ ክለብ ተመሳሳይ ሚና ያላቸውን ሁለት ተጫዋቾች መምረጣቸውም ለትችት ዳርጓቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለሴካፋው ዋንጫ ከፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የመረጧቸውን 27 ተጨዋቾች ያሳወቁ ሲሆን፤ እንደ ጌታነህ ከበደና ሳላዲን ሰኢድ የመሳሰሉ ኮከብና ስመጥር የፕሪሚየር ሊጉን ተጫዋቾችን አላካተቱም።

በግብ ጠባቂነት ታሪክ ጌትነት ከደደቢት፣ በረከት አማረ ከወልዋሎ እና ተክለማርያም ሻንቆ ከሐዋሳ ከነማ ተመርጠዋል።

በተከላካይ መስመር ቴዎድሮስ መቀለ ከመከላከያ፣ አበበ ጥላሁን ከሲዳማ ቡና፣ አበባው ቡጣኮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አናጋው ባደግ ድሬደዋ ከተማ፣ ግርማ በቀለ ከኢትዮ ኤሌትሪክ፣ አምሳሉ ጥላሁን ከፋሲለ ከተማ፣ ተመስገን ካስትሮ ከአርባምንጭ እና ሔኖክ አዱኛ ከጅማ አባጅፋር ተጠርተዋል።

አማካይ ተጫዋቾች ደግሞ ሳምሶን ጥላን ከኢትዮጵያ ቡና፣ ተስፋዬ አለባቸው ከወልዲያ፣ ከነአን ማርክነህ ከአዳማ፣ እንዳለ ከበደ ከአርባ ምንጭ፣ በሀይሉ ተሻገር ከኢትዮ ኤሌትሪክ፣ ብሩክ ቃርቦሬ ከወልዲያ፣ መስኡድ መሐመድ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ዮናስ ገረመው ከጅማ አባጅፋር እና ፍሬው ሰለሞን ከሐዋሳ ከነማ ናቸው።

በአጥቂ መስመር አቡበከር ሳኒ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አብዱረህማን ሙባረክ ከፋሲል፣ አዲስ ግደይ ከሲዳማ ቡና፣ ዳዋ ሆቴሳ አዳማ ከተማ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቀሌ ከተማ፣ አቤል ያለው ከደደቢት እና ጸጋዬ ብርሀኑ ከወላይታ ዲቻ ተመርጠዋል።

የሴካፋ ዋንጫ ከዲሴምበር 3 እስከ 17 ድረስ የሚካሔድ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከሻምፒየኗ ዩጋንዳ፣ ተጋባዧ ዙምባብዌ፣ ከብሩንዲና ደቡብ ሱዳን ጋር ተመድባለች። በሁለተኛው ምድብ ደግሞ ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ዛንዚባርና ተጋባዧ ሊቢያ ይገኛሉ።

በሀገር ውስጥ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ዙምባብዌ እና ሊቢያ በምስራቅና መካከለኛው ሀገሮች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተጋባዥነት እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
106 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 896 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us